ረቡዕ, 4 ጁን 2014

ይህን ይጠቀሙ 

አቡነ ማትያስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረቡት ተግሳጽ ፤ ምክር፤ አቤቱታ እና ጩህት

  • የእግዚአብሔር ባለ አደራ መሆን ቀላል ስላይደለ እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ፤ በታሪክና በሃይማኖት በምንመራቸው ምዕመናን ዘንድ በኃላፊነት እንጠየቃለን፡፡
  • ፓትርያርኩ በተቃራኒ መንገድ በመጓዝ ምን አይነት ጥቅምና የኅሊና ደስታ እንደሚሰጣቸው በፍጹም ሊገባን አልቻለም፡፡
  •  ቆቡ እንደው አንድ ጊዜ ከተሰቀለ በኋላ በቀላሉ የሚወርድ ወይም የሚሻሻል አይደለም፡፡ “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” (የጳጳሳትን ሹመትን በተመለከት ለቅዱስ ሲኖዶስ ያሳሰቡት)
  •  በስመ ሲኖዶስ  የሚጠቀሙት ባለስልጣኖች ሲኖዶሱን ባያሰድቡ መልካም ነው፡፡
(አንድ አድርገን ግንቦት 12 2006 ዓ.ም)፡-  በአሁኑ ሰዓት ስድስተኛ ፓትርያርክ አድርጋ ቤተክርስቲያን የሾመቻቸው አባት ከአመታት በፊት የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡ ከ14 ዓመት በፊት በርካታ አስተዳደራዊ ግድፈቶችን ተመልክተው ማለፍ ያልቻሉት አቡነ ማትያት ለቅዱስ ሲኖዶስ የሚደርስ 20 ገጽ ደብዳቤዎችን ከበርካታ አባሪ ማስረጃ ደብዳቤዎች ጋር ለወቅቱ የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሀፊ ለብጹዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ጥቅምት 12 1992 ዓ.ም አድርገው ልከው ነበር፡፡ ይህ የተላከው ሰነድ ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጋግሮበት ውሳኔ እንዲሰጥበት መሆኑን አቡነ ማትያስ በመልዕክታቸው ይገልጻሉ ፡፡ ነገር ግን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያገኙት መልስ ቢኖር አልደረሰንም የሚል ነበር፡፡ ይህ በሴራ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እንዳይቀርብ የተደረገው ደብዳቤ የግል ጋዜጦች እንዲያወጡትን በቀድሞ ፓትርያርኩ እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች  እያደረጉት ያለውን ነገር ህዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ በአስቸኳይ የፖስታ አገልግሎት በወቅቱ ህትመት ላይ ለነበረው “ኢትኦጵ” መጽሄት ዋና አዘጋጅ ለአቶ ተስፋዬ ተገኝ ከተላከው ሰነድ እና በጊዜው ለህትመት ከበቃው ጋዜጣ ላይ መለስ ብለን ምን አይነት ስሞታዎችንና ቅሬታዎችን ለቅዱ ሲኖዶስ እንዳቀረቡ ለማየት እንሞክራለን፡፡

ሰኞ, 19 ሜይ 2014

ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚመደብ የሚገልጽ የሕግ ረቂቅ ለውይይት ቀረበ


  • ‹‹የፓትርያርኩን ሥልጣን ይገድባል›› በሚል ተተችቷል
  • ‹‹አመራራቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ነው›› /የሕግ ረቂቁ/
  • ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚያስተላልፉት በብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ይኾናል
(አዲስ አድማስ ቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም)፡-       የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ፓትርያርኩን የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽና የፓትርያርኩን ሓላፊነትና ተጠያቂነት በጉልሕ የሚያሳዩ አንቀጾችን ባካተተ የሕግ ረቂቅ ላይ እየተወያየ እንደኾነ ተገለጸ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ 1991 .. ያወጣችውን ሕግ ከሌሎች ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማጣጣም፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዕድገትና ነባራዊ ኹኔታዎች ጋራ በማገናዘብ ያሻሽላል የተባለው የሕግ ረቂቁ ለውይይት የቀረበው፣ ባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶሱ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጎች ኹሉ የበላይ ነው የተባለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቁ÷ ርእሰ አበውና ለካህናቷና ለምእመናንዋ ኹሉ መንፈሳዊ አባት ለኾኑት ለፓትርያርኩ እንደራሴ እንደሚሾም በአንቀጽ 24 ላይ ማስፈሩ ተመልክቷል፡፡ እንደራሴው ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን የተጣለበትን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንዲችል የሚያግዝ›› መኾኑ በሕግ ማሻሻያ ረቂቁ ተገልጧል፡

መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመስራት ላይ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከቻይና መንግሥት የገንዘብ ብድር አገኝ

(አንድ አድርገን ግንቦት 3 2006 .)- መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ 32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ  አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኋላ በሀገሪቱ የተጀመሩት 10 የሥኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገነባው መሆኑ ይታወቃል፡፡  ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከሚቆጣጠራቸው ፕሮጀክቶቹ ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠርና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡  ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው በማንሳት መንግሥት 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መክፈሉ ይታወቃል፡፡ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራውም የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት አብያተ ክርስቲያናት ቅድመ የማግባባት ስራ በአካባቢ አስተዳደር በኩል እንዲሰራ ትዕዛዝ መውረዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብረ ሰዶማውያንን ሕግ አላላ


  •  ይቅርታ የሚያስከለክሉ በሚል በረቂቅ የይቅርታ ሕጉ የተዘረዘሩት ወንጀሎች ተሰረዙ ከተሰረዙት መካከል ‹‹ግብረ ሰዶም›› ይገኝበታል፡፡በሕጉ መሰረት መንግሥት ወደፊት ግብረሰዶም ፍርደኞችን በይቅርታ ሊፈታ ይችላል፡፡  
  •  ‹‹ግብረ ሰዶም ወንጀል ይቅርታ የማያሰጥ ተደርጎ መግባቱ ከሕገ መንግሥቱና ከሕዝብ ሞራል አንፃር ትክክል ነበር፤›› የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
  •  ‹‹የተዘረዘሩት ይቅርታ የማያሰጡ ወንጀሎች እንዲወጡ የተደረገው ይቅርታ የማያሰጡ በማለት ዝርዝር ከተጀመረ መቆሚያ ስለማይኖረው ነው››  የፓርላማው የሕግ፣ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍትሕ አስተዳደር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ  አቶ አስመላሸ ወልደ ሥላሴ
(አንድ አድርገን ግንቦት 3 2006 ዓ.ም)፡- የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ይቅርታ የማያሰጡ የወንጀል ዓይነቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽ ሙሉ በሙሉ በሕግ አውጪው አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰረዙ ተሰማ፡፡ ሌሎች ማስተካከያዎች የተካተቱበት ይህ የይቅርታ አዋጅ ባለፈው ሳምንት ፀድቋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ ክፍል ሦስት አንቀጽ 14 ንዑስ 1 በሕገ መንግሥቱ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ተብለው ከተቀመጡት ወንጀሎች በተጨማሪ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ወይም የማይጠየቅባቸው በማለት አሥር በላይ ወንጀሎችን ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡ ከእነዚህ መካከል ግብረ ሰዶም፣ ሙስና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብርተኝነት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል የይቅርታ ዓላማን የተመለከተው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡ ‹‹የይቅርታ ዋና ዓላማ፣ የመንግሥትና የታራሚዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል መንግሥት ጥፋተኞች በጥፋታቸው የተፀፀቱና የታረሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለው አምራች ዜጋ እንደሆኑ ማድረግ ነው፤›› በሚል ተተክቶ አዋጁ ጸድቋል፡፡
 

በዚህ መሰረት ወደፊት በአዲስ ዓመት ዋዜማም ሆነ በተለያዬ ሕዝባዊ በዓላት ወቅት መንግሥት ይቅርታ ከሚያደርግላቸው ፍርደኞች መካከል ግብረ ሰዶማውያን ፍርዳቸው እንደ ተራ ወንጀል በመቁጠር ሊለቀቁና ይቅርታም የሚደረግበት የሕግ አግባብ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ ይህ መንግሥት በግብረሰዶም ወንጀል ላይ የያዘውን አቋም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያመላክታል፡፡

ምንጭ ፡- ሪፖርተር