ማክሰኞ ፣23 ኦክቶበር 2012

ላያቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሐድሶ የሆኑ መጻህፍት(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዓመት በወርሀ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር እንደቆየ የምናስታውሰው ነው ፤ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡


በጊዜው የተወገዙት ሰባቱ  ድርጅቶች ውስጥ  ከሣቴ ብርሃን ፤ ማኅበረ ሰላማ ፤  የምሥራች አገልግሎት ፤ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር ፤  አንቀጸ ብርሃን (ከድርጅቱ ጋራ አሸናፊ መኰንንና ዳንኤል ተሾመ) ፤ የእውነት ቃል አገልግሎት ፤ ማኅበር በኵርና የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት ይገኙበታል ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ከተወገዙት 16 ሰዎች  የክህነትና የክብር ማዕርጋቸው ተሽሮ የበፊቱ አቶ የሚለው ስም ከተመለሰላቸው ውስጥ በግንባር ቀደምነት  አቶ አሸናፊ መኰንን ይገኝበታል፡፡

ይህ ሰው ለዘመናት ኦርቶዶክሳዊ በመምሰል የእኛ ያልሆነ ትምህርት ኑፋቄ የተቀላቀለበት መጽሃፍቶችን በመጻፍ በርካታ ብሮችን መሰብሰብ ከመቻሉም በተጨማሪ ምንፍቅናውን በበርካታ መጽሃፍቶች መዝራት ችሏል ፤ አሁን ግን ይህ ሰው ስራው ታውቆበት ከቤተክርስትያን ከተባረረም በኋላ የመጽሀፍት ነጋዴዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ መጽሀፍቶቹ ከትክክለኛ መጽሀፍቶች ጋር በመደባለቅ በገበያ ላይ ይዘዋቸው  ይገኛሉ ፤ ስለዚህ ምዕመናን የዚህን ሰው ትምህርት እና መንገድ ቤተክርስትያን ስላወገዘች መጽሀፍቶቹን እና ትምህርቱን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንዲሉ “አንድ አድርገን” መልዕክቷን ታተላልፋለች፡፡ ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ መጽሀፎቹን ላያቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሐድሶ የሆኑ መጻህፍት የፊት ሽፋን በመውሰድ በቀላሉ መለየት እንድትችሉ በዚህ መልክ አቅርበንላችኋል፡፡”የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” የማቴዎስ ወንጌል 7፤15እነዚህ ሁሉ መጻህፍት በአቶ አሸናፊ የተጻፉ ናቸው ፤ ስለዚህ የምንሰማው ስብከት እና የምናነባቸው መንፈሳዊ መጻህፍት የእነማን እንደሆኑ ለይተን ማወቅ መቻል አለብን ፡፡


 

እነዚህ በጣም ጥቂቶች ናቸው..ሌሎቹን በሌላ ጊዜ እናቀርባለን
 

26 አስተያየቶች:

 1. egzabehar yestachu ebakachu endzhe aynet negerochen beygizaw negerun....egzabehar betakersetyanene yetbek!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 2. Egzabher yestile tiru melekt new wendmoch bertu Leule Egzabher yagelgelot zemnachehun yebezalchehu LEULE EGZABHER ETHIOPIAN YEBARK AMEN!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. It is so important information to all truly Orthodox adherents! God Bless you!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. How did you know that it is 'so important' before reading the books? Are you small children who are victims of allegations and misinformation? What does 'truly Orthodox' mean to you? Hulun memar ena memermaer, gegown mewsed is expected from any adult. If you are in the 3rd grade, I cannot blame you. Cheers!!!

   ሰርዝ
  2. What do you mean? Sinodosu eko new yawegezew. My brother you don't have to be a supporter of a person even if he is your brother you have to stand up for the truth ok.

   ሰርዝ
  3. what di you know abuot sinodos it wasa good job for thosepeople to read the book and ask ashenafi about it .but Jesus wasalso accuised by the so called yeahihud kesawset like these edays dont wonder.God bless you Diakon Ashenafi

   ሰርዝ
 4. አንድ አድርገኖች ምነው የሚምርባችሁን ብትጽፉ አንድመቶ ጊዜ እየተሻሻላችሁ ብትፈጠሩም እንደ ዲ/ን አሸናፊ መጻፍ አትችሉም፡፡ መጽሀፎቹ ችግር አለባቸው በማለት ባዶ ወሬ ከማውራት ችግሮቹን ማሳየት ይበጅ ነበር፡፡ ምንም ችግር ስለማታገኙባቸው ግን በወሬ ትተረማመሳላችሁ፡፡ ማፈሪያዎች

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. Egziabher yebarek wondem, mech yemiseran sew kemetechet endemeneweta ayegebagnm

   ሰርዝ
 5. በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።እ/ር ማስተዋል ይስጣችው
  አንተስ ኦረቶዶክስ ነህ???????????

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 6. የቀድሞዉ ዲያቆን መጻሕፍት የተዋህዶ ሃይማኖታችንን የሚፃረሩ መሆናቸዉን አንብበን መረዳት፤ መፈተሽና የሚያሳስቱበትን ነጥቦች ይዘን መወያየት አለብን የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ። ከርቀት ከመሸሽ ክፉዉንና ደጉን አዉቀን መተዉ ስላለብን አታንበቡ ማለት መፍትሔ አይደለም። እንዲያዉም ምዕመናን እንዲያነቡትና ምንነቱን እንዲያዉቁት ማድረግ ብቻ ነዉ ዘላቂ መፍትሔዉ። እኔም መፃህፍቶቹን ለመግዛት ብዬ ርዕሶቹን በመያዝ አንዳንድ መፃህፍት መሸጫ ሱቆች በስልክ ስጠይቅ የለንም ብለዋል፤ አንዳንድ ቦታ ደግሞ ነበረን አሁን ግን አልቋ አሉኝ። የት እንደሚገኙ ”አንድ አድርገን″ ቢጠቁመኝ እጅግ አመሰግናለሁ። ስለጥቆማዉ በእግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ።
  o ይመስገን ከበደ ከንፋስ ስልክ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. እባክዎን ስጋ ከአፈር ወድቆ ኣፈር ሳይነካው ሊነሳ ይችላል

   ሰርዝ
 7. I am extremely saddened by the way you engage in defamation and persecution of Christian brothers. You know very well that Diakon Ashenafi was unfairly rated and is a victim of MK’s hatred for preachers of the Gospel. The name Jesus is frightening to our enemy Satan, so is His name to MK and supporters. May God help you to quit ‘wendimochin masaded’ and give you the heart to love Jesus, the name above all names!!!! I sincerely invite you to read the Diakon’s books. Believe me, you will be gratified by the messages.
  By the way, whether you call him Diakon or Ato or simply Ashenafi, it really does not matter. After all he does not want any decoration except being happy to be God’s slave, the God who called him “My son”!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. I do appreciate all the the writer Yibeltal and on anonymous from Nifas Silk. Ene yemilew, metshaf hulu menafik minamin eyale kaltesadebe yekirstianoch aydelem malet new?

   ሰርዝ
 8. ኢየሩሳሌም ነ ገ ደ25 ኦክቶበር 2012 11:25 ጥዋት

  ለ Yibletal Tameruቃለ ህይወት ያሰማልኝ፣ ዲያቆን አሸናፊን ዉግዘት በተመለከተ እኔም እንደ ኦርቶዶክስነቴ ተቀብዬ ነበር። በኋላ ግን የእርሱን አሳዛኝ ማመልከቻ አንብቤ በቅዱስ ሲኖዶሱ ላይ ጥያቄ መጣብኝ፣ መልስ ይሰጠዋል ብዬ ብጠብቅ ጭጭ አሉ፣ ስለዚህ ዲያቆኑ የተወገዘዉ በአሉባልታ ነዉ ብዬ ዲቁናዉን ላከብርለት ወሰንኩ። አሁንም ሲኖዶሱ መልስ እስካልሰጠበት ድረስ ዲያቆን ብዮ ከመጥራት አላቆምም።
  በነገራችን ላይ በ ሀ ቲዩብ የተላለፋትን ስብከቶቹን ሳዳምጥ እንደዚህ ያለ ሰባኪ ባገራችን በተለይም በቤተክርስቲያናችን እያለ ነዉ ወይ የወንጌል ድርቅ የሚመታን ብዬ በእጅጉ አዘንኩ። ዲያቆን አሸናፊ ዬት ነዉ የተደበቅኸዉ? እባክህን በአካል ዬት እናግኝህ?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 9. ″አንድ አድርገን″ ሆይ የትኛዉ የአሸናፊ መጽሐፍ፣ በየትኛዉ ርዕስና ገጽ ነዉ ምንፍቅና የታየዉ? እኔ እንደ ዕድል ሆኖ ቢያንስ ቢያንስ አሥር ያህል መፃሕፍቶቹን አንብቤአለሁ። በሚገርም ሁኔታ ተለዉጬ ያለፈዉን ሕይወቴን እያስታወስኩ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ እገኛለሁ። ይህንን ስናገር ማን እንደምትሉኝ ይገባኛል፣ ግን እዉነት ስለሆነ አላፍርበትም። ይልቁኑ በስማ በለዉ ከሚሆን እናንተም የማንበብ ልምድ ካላችሁ እስቲ አንብቡትና ፍረዱ። የምፈራዉ ልምዱ ስለሌለ በቅብብሎሽ ስም የማጥፋት ዘመቻ ላይ ተሰማርታችሁ እንዳይሆን ነዉ። አንድ የጠላሁባችሁ ነገር አለ፣ ለምን ስለንግድ አነሳችሁ? አሸናፊ ገንዘብ አገኘ የሚል ሰይጣናዊ ሀሳብ የገባችሁ ይመስለኛል፣ ይህቺ ደግሞ ቆሻሻ ናት። የአሸናፊ መፃሕፍትና ስብከቶች ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እንድትወጡና ፍጹም ክርስቲያን እንድትሆኑ ያደርጋልና በክርስቶስ ስም ልጋብዛችሁና አንብባችሁና አዳምጣችሁ ከዚያ በኋላ ታዘቡኝ፣ ዉቀሱኝ። አትፍሩት !! አሸናፊ በአንዱ የስብከት ካሴቱ ላይ “ክርስትና በእዉቀት ላይ የተመሰረተ እምነት ነዉ” ያለዉ ሁሌም ልቤን ይነካዋል።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. yalefew hiwetih min neber ahunis min ? man yawukal tefitehim yihonal
   dinehim yihonal erasih gin sile rasih memesiker atichilim,m/tum
   befit orthodox neberhu ahun gin begeta dignalehu eyalu orthodox getan yematawuk yemimesilachew silalu antem kenesu wusit kehonih ............alikebelihim endene?

   ሰርዝ
 10. and adergenoch tekekel kalhonu sinodosum tekekel aydelem malet new. ato ashenafi yetewegezew ketsafachew metsehaft tenesto selehone and adergenoch tekekel nachew beye amnalew

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. I also think that the Holy Synod had made a mistake, may be misguided by some agents of evil doers. silezih, lehulachinim NISEHA yasfeligal. I have a question to the above commentator. Eynihin newu weiys jorohin newu yemitaminew? Why are you afraid to read the book and judge for yourself. The Holy Synod was not interested in reading the books but to condemn the young preacher, Diakon Ashenafi. Tsegawu yebezalet sebaki silehone saitan qento newu enantenim yemiyasasitachihu. May God bless you with the wisdom of understanding the Truth.

   ሰርዝ
 11.  ሕይወት ተፈራ ከ4 ኪሎ26 ኦክቶበር 2012 9:54 ከሰዓት

  ዲያቆን አሸናፊ በ26 ዓመቱ ባሳተመዉ በሚባለዉ መጽሃፉ «…ምድሪቱ ፈዉስ እንድታገኝ የሀዘን ማቋን እንድታወልቅ በምድሪቱ ላይ ብሔራዊ ንሰሀና ይቅርታ ያስፈልጋል:: ይህንን ንስሃና ይቅርታ ቤተክርስቲያን በተሰበረ ልብ ተቀብላ ለህዝብና ለመንግስት ካልገለጠች ከቤቱ የሚጀምረዉ የእግዚአብሔር ቁጣ ፈጥኖ ያገኛታል::» ብሏል::
  ይህ ወጣት አገልጋይ የአገሩ: የቤተክርስቲያኑ: የናንተም ጉዳይ ይገደዋል:: ገና በልጅነቱ ሙሉ ህይወቱን ለጌታችን የሰጠዉ ይህ ወጣት (የከተማ መናኝ) ዘወትር ስለእናንተ ይጸልያልና ቆም ብላችሁ አስቡ:: እሱ እንዳለዉ በንሰሃዉ በርቱ:: እሱን የሚያስጨንቀዉ እኛ ስንራኮት ጌታችን ከተፍ እንዳይል ነዉ:: ከዚህ ይሰዉረን! አሜን::

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 12. የሚገርም ነው ወይ ጠላት አሁንስ በጣም አበዛችሁት እንደው ክርስትያኑን ጭራሽ የማያስተውል አደረጋችሁት ሥጋዊ ቅናት ውስጣችሁን አንገበገባችሁ እስኪ በሽፋን ከምታውሩ 20 መጻህፍትን አቅርባችሁአል እንደው እስኪ ከ20ው መጻህፍት ላይ አንድ አንድ ህፀፅ አሳዩን ወሬ ብቻ ምን ያደርጋል እናንተ ጽሁፋችሁ ክስ አሉባልታ ብጥብጥ የመሳሰሉት ናቸው የዲ/ን አሸናፊ መኮንን ግን ወንጌል ነው ፍቅር ነው ፀሎት ነው ትዕግስት ነው ምክር ነው እንደው አሁን እራሳችሁን ደብቃችሁ ስም ማጥፋት ተያይዛችሁታል እናንተ እራሱ የቤተ ክርስትያን ልጆች እንደሆናችሁ ማስረጃችን ምንድነው ሀይማኖተኞች ከሆናችሁ ማንነታችሁን ግልጽ አድርጋችሁ በግልጥ እንደው ሰማእትነትም ከመጣ ለመቀበል ስለ ቤተክርስትያናችን አውሩ ካለበለዚያ ግን ቤተ ክርስትያንን አትወክሉም ይህንን ስል አናውቃችሁም ማለት አይደለም ግን አያንፅም የሚነበብባችሁ ሥጋዊ ቅናት ነው የ እናንተ ማንነት ቢፈተሽ 000000 ሲባዛ 00000 ናችሁ እራሳችሁን ፈትሹ ጌታ ደግ ዘመን ያምጣል!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 13. Yasazinal beergit hulum yetehadiso aramajoch mefter yemifeligut likawuntin ena betekiristiyanin yemiterater tiwlid mafirat neberina tesaktolachewal. Ato Ashenafim bihon.siketil yeAshenafin diriset anbibo bicha tikikil ena tikikil new malet ayichalim mistirin metsihaftin adeladilo mawek yashalina. Yekidus sinodos wusanen alikawemim aliteraterim gin yetewegezebetina yeteleyebetin mikiniyat mawek degimo mebitachin silehone wede mezgeb bet bemehed meredatina mawek enicilalen. Mahibere Kidusanin lemitinekifu demo zarem negem betekiristiyan eskalech dires amekelawochin kemenkelina kemarem ayibozinim. Manibeb bichawun bado new bemastewal kalhone. tetenkeku. Yemebeteriyaw gize kerboal. Abekahu.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 14. ለጸሎት ተነሡ የሚለውን መጽሐፍ አንብባችሁታል? እና ምንም ኑፋቄ አላገኛችሁበትም? እንግዲያውስ ኦርቶዶክሳዊውን አስተምህሮ አታውቁም ወይም አልተማራችሁትም ማለት ነው። "በጎቼ ድምጼን ያውቁታል ይከተሉኝማል።" እንዲል በጎች ከሆናችሁ በቀላሉ የአቶ አሸናፊን ድምፅ ከተዋሕዶ የተለየ እንደሆነ መረዳት ጭንቅ አይሆንባችሁም። ለጠቅላላ ዕውቀት እንዲሆናችሁና ራሳችሁን እንድታዩበት ግን ፤ ኦርቶዶክሳዊ የጸሎት ሥርዓት ምስጋናን ፣ ምልጃን ፣ ልመናን ፣ ተአምኖ ኃጣውዕን የሚያካትት ነው። የሰውዬው ጽሁፍ ግን በፍጹም ከዚህ የራቀ እና ቅዱሳንን አቃሎ ራስን በማጽደቅ በምንፍቅና እርሾ የተቦካ ሊጥ ሆኖ ነው ያገኘሁት። በዚህም ምክንያት ይህ ጉዳይ በአንድ አድርገን ላይ ከመውጣቱ አስቀድሞም ቢሆን መጻሕፍቶቹ ኦርቶዶክሳውያን እንዳልሆኑ ተረድተን ስለነበረ እንወያይ ነበር። ቅዱስ ሲኖዶስም በስሜት እና በክሽን ቃላት የጣፈቱ ውስጣቸው ግን ክዳትን የተመሉ መጻሕፍቱን መርምሮ ዮን መናፍቅ በማውገዙ ከፍተኛ ክብር ሊቸረው ይገባል። እዚህ ላይ የተንጫጫችሁትም ራሳችሁን መርምሩ። ቃል አሳማሪን ሁሉ የምታምኑ ከሆነ እዚህ ላይ ንግግራችን ያበቃል ያለበለዚያ ግን ከእውነቱ ለመድረስ ኦርቶዶክሳዊ ብርሃን መርቶ ያደርሳችኋል።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ