ሐሙስ ፣22 ኖቬምበር 2012

የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው


 • የእምዬ ሚኒሊክ ሐውልትም ሊፈርስ ይችላል


(አንድ አድርገን ህዳር 13 2005 ዓ.ም)፡-  የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው ተሾሙ።በ1928 ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ አገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ውቅያኖስ አቋርጦ በመምጣት ኢትዮጵያን ሲወርና ሕዝቧን፣ ሊቃውንቷን፣ ገዳማቷንና አድባራቷን በግፍ ሲጨፈጭፍ ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ቆረጡ። የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከአረመኔው ፋሺስት ጦር ጋር በመፋለም ላይ የነበረውን አርበኛ ለማበረታታት ወደ ማይጨው በሔዱ ጊዜ ብፁዕነታቸው ተከትለው ሔዱ። ከዚያ እንደ ተመለሱም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ተሰባስበው የቤተ ክርስቲያን አምላክ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጣውን ችግር እንዲያስታግሥ በጸሎት እየተጉ ወደነበሩት አባቶችና አርበኞች በመሔድ ለአገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ሁሉም እንዲጋደሉ ማሳሰብ እና ማትጋት ጀመሩ። ኋላም የገዳሙ መነኮሳትና የሰላሌ አርበኞች ይባሉ የነበሩት አርበኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሳታፊ ሆኑ። ከዚያም አርበኞቹ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ወደ ሰላሌ ሲመለሱ ብፁዕነታቸው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ በጠላት እጅ ተያዙ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስምንት ጥይት አሁን ሃውልታቸው ከሚገኝበት ቦታ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የአዲስ አበባ የባቡር መንገድ ስራ ከተማዋን ከጊዮርጊስ ፤ በአትክልት ተራ በመርካቶ በኩል አድርጎ በአብነት  ኮካ ኮላ ጋር ይገጥማት ተብሎ የታሰበው የመጀመሪያው ምዕራፍ  የባቡር መንገድ ምክንያት የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ከቦታው እንደሚነሳ ታውቋል ፤ በመሰረቱ የመንገድ እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በማንኛውም ሃገር በሚደረጉበት ጊዜ የእምነት ተቋማትንና እና ለሀገር እና ለህዝብ ትልቅ ውለታ የዋሉትን ለስማቸው መታሰቢያ የተሰየሙ ሃውልቶችን መነካት እንደሌለባቸው ይታወቃል ፤  የአገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ መታሰቢያቸውን ለማንሳት በስመ የባቡር ፕሮጀክት ለዚች ሃገር የዋሉት ውለታ ፤ ለአርበኞች ያሳዩት ተጋድሎ ፤ ህዝቡ በእምነቱ አንድ በመሆን ጠላትን እንዴት መመከለት እንዳለበት ያስተላለፉት መልዕክት ከግምት ውስጥ ሳይገባ እንደ ተራ ሃውልት ለማንሳት ሃውልቱ የቀናት እድሜ በቦታው ላይ እንደሚቀረው የባቡር ስራ ፕሮጀክት ስራን በበላይነት የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በሸገር ሬዲዮ  ተናግሯል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የሚሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የእምነት ተቋማትንና ታሪካዊ ሃውልቶችን በጥናት ወቅት ለምን ግምት ውስጥ አስገብተው እንደማይሰሩ መነጋገሪያ ነጥብ ሆኗል ፤ ባልጠፋ ቦታ ዋልድባ ላይ ስኳር ልማት ማቋቋም እና ባልጠፋ መንገድ ሃውልቶችን እያነሱ መንገድ መስራት የሃገሪቱን ታሪክ ጥላሸት ከመቀባት በላይ ሃገሪቱ አለኝ የምትላቸውን ቅርሶች ከማጥፋት የማይተናነስ ስራ መስሎ ይታየናል፡፡  ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለ ሚኒሊክ ሐውልት ከተማ መስተዳድሩ ያለው ነገር ባይኖር ስለ አጼ ሚኒሊክ ሐውልት ባለሙያዎች እንደሚሉት የባቡር መንገዱ ዲዛይን ካልተቀየረ በቀር የሚኒሊክንም ሐውልት እንደሚነካው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
እኛ እያልን ያለነው ሀገሪቱ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለምን ቅድመ ጥናት ሲካሄድ የእምነትና የሐውልት ቦታዎች ፤ የአባቶቻችን ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሻራቸውን ያስቀመጡበት ቦታ ከግምት ውስጥ አይገባም ? ወይስ ከበስተጀርባ ሌላ ነገር አለ……?..

“አይጥ ለሞቷ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች” ይላል ያገሬ ሰው


የታሪክ ምንጭ፡- ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

35 አስተያየቶች:

 1. አሁንም ሀገር የሚለውጥ ሃይማኖትን የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና....
  https://www.facebook.com/photo.php?fbid=391880110888910&set=a.108834425860148.14334.100002007731323&type=1&relevant_count=1

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 2. All is deliberately done and part of weakening Ethiopian Orthodox Church. Do not be kid

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. fiyel kemedresua kitel mebetesua hone negeru!!! aye mengist albawa hager wedet yihon fird yemigegnew?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. men meheja ale beleh new zem belo mayet enje
   ewunet gin Egziyabehier silemen tewon????

   ሰርዝ
 4. As long as they safely take it to another place, I don't c any kind of problem.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. ሲጀመር ለምን ይነሳል?ወያኔ የፈረንጅ ተላላኪ ስለሆነ ታሪካችንን አጥፍቶ በነጭ ታሪክ መተካት እንደሚፈለግ ተናገሯል ይህንንም ከ ኅርማን ኮል ከተባለ አሜሪካዊ አይሁድ ጋር በ 1982 ዓ ም እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ ሲመክሩ እንደነበር የታሪክ ትዉስታ ነዉ ::እንኩአን ይህንን ያህል ታሪክ የሰራ አይደለም የአንተ አይነቱ ደደብ ቤት ከቦታው ቢነሳ የምትሆነዉን አንተ ታዉቃለህ በለመድከው ጉቦ ቢሆንም እንዳይነሳ መጣርህ የማይቀር ነዉ:: ፈሳም

   ሰርዝ
  2. Are you an idiot boy?

   ሰርዝ
 5. As long as they safely move it to another place, I don't c the problem.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. you are not an ethiopian.pleas try to read the history of his holines abun petros.then write again.stupidddddddd

   ሰርዝ
 6. ለምን ስለማታውቀው ታሪክ ትዘባርቃለህ ተረት መስማትና ማውራት የተለያዩ ናቸው አንተም ያደረከው ይሄን ነው ስለዚህ እንደ መናፍቅነትህ ቀጥልበት ይሄ ግን የኛ የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ታሪክ እና ቅርስ ነው ያንተ አይደለም

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 7. በመሰረቱ የመንገድ እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በማንኛውም ሃገር በሚደረጉበት ጊዜ የእምነት ተቋማትንና እና ለሀገር እና ለህዝብ ትልቅ ውለታ የዋሉትን ለስማቸው መታሰቢያ የተሰየሙ ሃውልቶችን መነካት እንደሌለባቸው ይታወቃል ፤ የአገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ መታሰቢያቸውን ለማንሳት በስመ የባቡር ፕሮጀክት ለዚች ሃገር የዋሉት ውለታ ፤ ለአርበኞች ያሳዩት ተጋድሎ ፤ ህዝቡ በእምነቱ አንድ በመሆን ጠላትን እንዴት መመከለት እንዳለበት ያስተላለፉት መልዕክት ከግምት ውስጥ ሳይገባ እንደ ተራ ሃውልት ለማንሳት ሃውልቱ የቀናት እድሜ በቦታው ላይ እንደሚቀረው የባቡር ስራ ፕሮጀክት ስራን በበላይነት የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በሸገር ሬዲዮ ተናግሯል፡፡

  Lenegeru, Protestantu Hailemariam weyis Muslimu Demeke, le like Papasachin endikorekoru enitebikalen!?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 8. የባቡር መስመር ዝርጋታውን ጥናት ያካሄዱት ጣሊያኖች መሆን አለባቸው አሊያም በወረራው ወቅት ሀገራችንን በባንዳነት ከጠላት ጋር አብረው ሲወጎት ከነበሩት መከካል በጣሊያን ሽንፈት ቁጭት ያደረባቸው ርዝራዦች መሆን አለባቸው፡፡ እ/ር ህዝቡና ሀገራችንን ይጠብቅ፡፡
  ልማታዊ ጥፋት፡፡  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 9. ፖለቲካ እና እምነት እየቀላቀላችሁ መከራችን አየን እኮ… ኦርቶዶክስ ፍጹም ጸረ ልማት እያስመሰላችሁ አትጉዷት… በሸገር የተነገረ እንደገና አድጡና ተናገሩ.. ነገር ፈላጊ…

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 10. የባቡር መስመር ዝርጋታውን ጥናት ያካሄዱት ጣሊያኖች መሆን አለባቸው አሊያም በወረራው ወቅት ሀገራችንን በባንዳነት ከጠላት ጋር አብረው ሲወጎት ከነበሩት መከካል በጣሊያን ሽንፈት ቁጭት ያደረባቸው ርዝራዦች መሆን አለባቸው፡፡ እ/ር ህዝቡና ሀገራችንን ይጠብቅ፡፡
  ልማታዊ ጥፋት፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 11. የባቡር መስመር ዝርጋታውን ጥናት ያካሄዱት ጣሊያኖች መሆን አለባቸው አሊያም በወረራው ወቅት ሀገራችንን በባንዳነት ከጠላት ጋር አብረው ሲወጎት ከነበሩት መከካል በጣሊያን ሽንፈት ቁጭት ያደረባቸው ርዝራዦች መሆን አለባቸው፡፡ እ/ር ህዝቡና ሀገራችንን ይጠብቅ፡፡
  ልማታዊ ጥፋት፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 12. ende ene yihe tilik project sikerets tinat yelewum ende?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 13. በመጀመሪያ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ እንደሚኖር ሰው እናስብ፤ ቀጥሎ ፍጹም ክርስቲያን ነን ካልን የአቡነ ጰጥሮስ ሀውልት ሰማያዊ እንደሆ እንመን::

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 14. kirstna bezemen ayikeyrm yehagerunm tark yemyafers mengst alsemanm,

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 15. የባቡር መስመር ዝርጋታውን ጥናት ያካሄዱት ጣሊያኖች መሆን አለባቸው አሊያም በወረራው ወቅት ሀገራችንን በባንዳነት ከጠላት ጋር አብረው ሲወጎት ከነበሩት መከካል በጣሊያን ሽንፈት ቁጭት ያደረባቸው ርዝራዦች መሆን አለባቸው፡፡ ፈጣሪ ህዝቡና ሀገራችንን ይጠብቅ።
  ልማታዊ ጥፋት፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 16. alamaw betikikil gilts lihonling alchalem,,,yih kirs eko ye orthodox bicha adel endene ehone abunu yetagelut le hagerachew netsanet new, yagerachew degmo ke orthodox wuchi lela haymanot teketayoch endalat aytefachewm, ena please kom blo maseb yashawal meseleng yihe guda,,,babur mezergatu eseyew new lageritu edget gin ewnet lela menged tefa? Yane

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 17. Ene Endemasibew, yehagerachin zemenawi tarik kegemerebet ke Atse Tewodros Zemen jemiro Ethiopia wist yetekesetu abzangotu mahberawi, poleticawi endihum limatawi tiyakewochna ena melsochachew( malete dirgitoch)ketwilid lewtoch balefe;ye"legacy"woch gichit ena fitchit hidetochna wutetoch nachew.

  enezihim:Yemirabawiyan kegn geshiwoch, (yegazur geshiwoch "neo liberalists" endihum yenesu agelgayoch yehonu Arab dictators and sheik states ena yenesu Baroch(slaves) yehonu Ethiopiawi Bandoch bandengaw wogn honew yaltemetatene"disproportionate" gulbet
  (ye fasisist Italian yemerz gas mtekem ena ye yekatit 12 tun jimla chicheffa yastwisual) genzeb (yihen "legasi" lemastebek eyewota yalewin ena yemiwotawn

  American " print dollar" and Arab shik states "Petro dollar" libyilual
  )endihum propaganda( ye Ethiopiawianin yehager fiker simet and kurat lematfat yemirabawian media "empire" , acadamia yehageachinin misil endet tilashet endemikebu lemayet; it is enough to find and see the dictionary meaning of famine...all other nations including the colonial"chauvinists" have had encountered repeated episodes of famine in their history but it is hidden. this one of the major areas of psychological warfare waged on us) beantsaru degmo hager wodad
  ethiopiawi arbengoch yihen ye amist tiwlid yemitega zemen yefege regim ena atakach tigil sayakuaritu eskahun dersewal.Tiglu lemiketilut tiwldochim yitelatal engi Ethiopiawi egi Aysetim bayihon "egi yinesal".

  Kemachu Legese Zenawi erefit mesemat behuala mierabawian ena yenesu Ethiopian baroch( barinet ye mentality guday new) sile worsina kirsu abzitew eyetecheneku,eyetetebebu endihum eyeteteramesu yalut (hawltochun lemafires enkisikase megemeru berasu hidetu yemeteramesu megemeria phase lay megbatun yaregagital);merabawinan kehulet meto shi belay eskafinchaw yetetek zemenawi tor yizew le amist amet talianoch leasir amet engilizoch Ethiopian yizew matenakek yalchalutine belelaw alem kegn geshinetachew siker kebrew yehedut agerochin be economy be poletika ena be sinelibona egir teworch asro ena tenkol kebro yemewtat zede enesu "exit stategy" yilutal bemifeligut meten sayadergu kertew yenesu baria yehonew legesse Zenawi yihenin lemasakat agerituan bezer silekefafelat esun lemasketel yalechewn kishet lemaualate new.Neger gin Galemotawa Americam honech,yeauropa kesarawian endihum Arab dictators and sheki states enesu kedimew yiferarisuatal enji ayisakalechewm;meteramesunm gemirewal mechereshachewn yasayegn.

  Egiziabher Ethiopian yastinatal!

  )  ,ge
  ' nachew.
  y


  )
  yemiatenetinu

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 18. where are Orthdox followers? You have to be united and this is the crucial moment

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 19. አተንጫጩ መዳኒአለም ያለው ነው የሚሆነው

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 20. We can't tolerate Wayne leaders any more and lets unit and stand on the side of church!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 21. We can't tolerate Wayne leaders any more,so lets stand by on the side of our church!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 22. ለልማት በመሆኑ መነሳት ያለባቸው ነገሮች መነሳት አለባቸው የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትም ቢሆን የሚነሳው ስራው እስኪጠናቀቅ መሆኑን መንግስት ገልጻል በመሆኑም ይሕን በተመለከተ በጊዜው የምናየው ይሆናል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ ፕላን የሌላት የቤትና የመንገድ አሰራሯ ወጥነት የሌለው ነው ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የእከሌን ቤት ላለመንካት መንገዶች ተለውጠው መሰራታቸው ነው ይህም ችግር አሁን መደገም የሌለበት በመሆኑ መነሳት ያለባቸው ታሪካዊም ሆኑ መንፈሳዊ ነገሮች በአግባቡ ተነስተው ከተቻለ በቦታው ካልሆነም በተለዋጭ ቦታ መቀመጥ አለባቸው እንጂ እንዳይነኩ በማለት ስራዎች መቆም ያለባቸው አይመስለኝም፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 23. ayeeeeeeeeeeeee yasew neger sew zem bilo lemen lemetechet yerotal haweltu majameria mulu mereja eneyaz kaza hasab metechet anta kristian kahonk atekeraker egzabehar yaweka tselot arege ena endasemahut gen ka aserew ewenatawe haweltu tenaseto legezawe muziem yekamatal kaza babyru ba ground selamehad gerawendu ketesera behuala betashala bamara hunetu endagena kalaye yeseral ya minilik hawelte cherashe ayenakam ka baburu 11m yerekal endapleticagna sayehon endasew enaseb EGZEABEHAR ETHIOPIAN YEBARK!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ