ረቡዕ ፣12 ዲሴምበር 2012

ዛሬ በአታ ለማርያም ሄጄ ይህን ሰምቼ መጣሁ(አንድ አድርገን ታህሳስ 3 2005 ዓ.ም)፡- የዛሬዋን ቀን ለማክበር እና ከእመቤታችን በረከት ለመቀበል በታእካ ነገሥት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን  አቃቢ መንበር ብጹእ አቡነ ናትናኤል ፤ ብጹእ አቡነ አረጋዊ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ፤ ብጹእ አቡነ ስምኦን የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራ የመጡ  በርካታ ዲያቆናት ቀሳውስት መነኮሳት እና ምዕመናን በአሉን ለማክበር ቦታው ተገኝተዋል፡፡
በግቢው እንደደረስኩኝ አንድ አባት ስለ በአሉ ምንነት ለምን እንደምናከብር በሰፊው ትምህርት ሲሰጡ ደረስኩኝ ፤ በመቀጠልም እመቤታችንን  ተማጽነው እና ለምነው ስለታቸው የደረሰላቸው እምባቸው የደረቀላቸው ፤ ጸሎታቸው የተሰማላቸው የሶስት ምዕመናንን ስለት ለምዕመኑ ተነገረ ፡፡ አንዲት እህታችን እንዲህ በማለት ምስክርነቷ ሰጥታለች “የኤች አይቪ ቫይረስ ተይዤ ነበር ፤፡ ከዶክተሮችም መድሃኒቱን እንድትጀምር ተነግሮኝም ነበር ፡፡ ነገር ግን “መድሀኒቴም ይሁን ሕይወቴ እግዚአብሔር ስለሆነ መድሃኒቱን አልጀምርም በጸሎት በጾምና በስግደት እድናለሁ እፈወስማለሁ” በማለት በርካታ ገዳማት እየሄድኩኝ ከበሽታው እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ ጸሎት አደረኩኝ ፤ ለልጆቼ እንድኖርላቸው ከዚህ በሽታ አድነኝ ብዬ ተማጸንኩኝ ፤ ሞልቶ ከሚተርፍ ተርፎ ከሚቀር እድሜ አትንፈገኝ በማለት ለመንኩኝ   አንገት የማታስጎነብስ ልመናን የምትሰማ ወደ እመቤታችን ጸበል በማምራት ጸበሏን ጠጥቼ እና ተጠምቄ ከበሽታዬ ነጻ ልወጣ ችያለሁ” በማለት በአውደ ምህረት ላይ  ምስክርነቷን ሰጥታለች ፡፡ 


ሁለተኛዋ ምስክር “ከጓደኞቼ ጋር ከስራ በአንድ ላይ ተባረርን ፤ ግራ ገባኝ ጨነቀኝ  ፤ የማደርገው ነገር ጠፋኝ፡፡  ከጓኞቼ ጋር ከስራ ስንባረር እነርሱ ጠበቃ ቀጥረው ፍርድ ቤት ክስ መሰረቱ ፤ እኔ ግን ጠበቃዬን እግዚአብሔርን እና እመቤታችንን አድርጌ ወደ ቤተ መቅደሱ መጥቼ እመቤቴን ተማጸንኩኝ ፤ ለእኔ ግን ጠበቃዬ ሰው ሳይሆን እመቤታችን ናት  በማለት በጸሎት በቤተመቅደስ በመገኝት ለመንኳት ፤ እባክሽን ጠበቃ ሁኝልኝ ፤ እባክሽን ችግሬን ፍቺልኝ ብዬ ተማጸንኳት ፤ ጓደኞቼ ጠበቃ ቀጥረው እስከ አሁን ድረስ ይከራከራሉ እኔ ግን በእናቴ ጠበቃነት ችግሬ ተፈትቶልኛል ፤ በዚህ ጉዳይ ያልተከፈለኝን የ5 ወር ደመወዝ ከእነ ጥቅማ ጥቅሙ በእሷ አማላጅነት ተከፍሎኛል  ፡፡ እኔን የተለመነች እናት እናንተንም ትለመናችሁ፡፡” በማለት የተደረገላትን ነገር በአውደ ምህረት መስክራለች፡፡


 በመቀጠልም   አንድ ወልደ ማርያም የሚባል ወንድማችን” በስራዬ ላይ ከባድ ጥፋት ደርሶብኝ ነበረ ፤ በእመቤቴ በእለተ ቀኗ በቤተክርስትያን በመገኝት አልቅሼ ነገርኳት ፤ የለመንኩት ነገር አንዳች ሳይጓደል ስራዬ እንደ ቀድሞ ተመልሶልኛል ፤ ለክብሯ መግለጫ 5ሺህ ብር ይዤ መጥቻለሁ በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡  ጸሎታቸው የተሰማላቸውን ሰዎች ምስክርነት ቢጻፍ ብዙ ሰዎች ይማሩበታል የደከመም ይበረታበታል ብሎ በማሰብ በማሰብ እናንተ ዘንድ እንዲህ አድርሰናል፡፡


መልካም በዓል ይሁንላችሁ

እነርሱን የተለመነች እመቤታችን እኛንም ትለመነን .. አሜን

24 አስተያየቶች:

 1. ye Getachin ye Iyesus Kiristos ye enatu Ye Dingil Mariam tsegana bereket yideribin

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 2. አሜን! ለይኩን ለይኩን! ለይኩን!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. የጌታች መድሃኒታች የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት የእመቤታችን ጸጋና በረከት ይደርብን ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል ይደረግለታልና

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 4. ye Getachin ye Iyesus Kiristos ye enatu Ye Dingil Mariam tsegana bereket yideribin

  Kale Hiywot yasemalin

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 5. እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ሁለት ልጆች አሉ፡፡ መጀመሪያ ስገባ እነሱ ያሉበት ክፍል ዉስጥ ተመደብኩኝ ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ ለስራዉ አዲስ ብሆንም ስራ ባለማሳየት በጣም ጭንቅላት የሚነኩ ንግግሮችን በመናገር እሄዉ አንድ አመት ሙሉ ያሰቃዩኛል፡፡ በነሱ ምክንያት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሁለት ሰዉ እንደወጣ በእርግጠኝነት እናገራለሁ፡፡ እኔን አንድ ቀን በጎ ነገር እንኩዋን ተናግረዉኝ የማያዉቁት እነዚህ ሰዎች የተሻለ ደሞዝ ያለዉ ስራ አገኘንልሽ ብለዉኝ ነበር፡፡ ደግሞ የሚገርመዉ የተሻለ ደሞዝ ብለዉ የነገሩኝ ከነሱም ደሞዝ የሚበልጥ ነዉ፡፡ እናም በዚህ ጉዳይ ቤተክርስቴያንም ሄጄ ይሁን ቤቴ ሆኜ አለቅሳለሁ አሁን ግን በጣም ስለመረረኝ ስራም ባላገኝ በዚህ ወር መጨረሻ ልለቅ ወስኛለሁ፡፡ ለማንኛዉም ሰዉ ለሰዉ ሲጸልይ ጸሎቱ ይሰማልና እግዚአብሄር እንዲያየኝ ወንድሞቼ ሆይ ጸልዩልኝ፡፡ እኔ ምን አልባት በከበደዉ ሃጢያቴ ይሆናል የእግዚአብሄርን ልብ ማሸነፍ ያቃተኝ፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 6. እህቴ ሃዘንሽ ስለተሰማኝ፣ ተሰምቶኝ ዝም እንዳልል እንዲሁ የመሰለኝን ልዘባርቅ….
  ‹‹ረድኦ ለኢአምኖትየ›› በዪ
  ሌላኛው ነጥቤ ደግሞ፣ ስላሴ አለማመናችንን ወደማማን፣ ለውጥልን ብለን መለመን እንችላለን፡፡ ታስታውሺ እንደሆነ አንድ ምስኪን አባት ጌታችንን ብትችልስ ልጄን ከያዘው ጋኔን አድንልኝ ለኔ አንድ ነውና አለው…ጌታችንም ‹‹ ብትችልስ ትላለህን!፣ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል›› ሲል አባትም ‹‹ አምናለሁ! አለማመኔን እርዳው›› አለው…ጌታችንም ብላቴነውን ፈወሰለት ይላል፡፡
  አባትየው ማለት እኔና አንቺ ነን እያመንን ደግሞ የምንጠራጠር …ስለዚህ ጌታችን በወንጌል ‹‹አለማመኔን እርዳው›› ብለን እንድንለምን አስተማረን፡፡ ማር 9፤24
  ስለዚህ አንቺም ስትለምኚ አለማመኔን ከደረሰብኝ ችግር አውጣኝና ወደማመን አድርስልኝ…ማለትና መለመን ትቺያለሽ፡፡

  ‹‹እራስሽ ለምኚ!››
  አንዱ ስላንዱ ብጸልይ ጥሩ ነው…ስለዚህ እራሱን የቻለ የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ግን እኔ የምመክርሽ በጠሎት እርዱኝ ብለሽ በዚህ ዐለም በሚመላለሱ ወንድሞችሽ እና እህቶችሽ ብዙም አትደገፊ….ለራስሽ እንደራስሽ የሚሆን የለምና ፡፡ ስለዚህ መደገፍ ና መታገዝ ካስፈለገሽ ደግሞ እንደ ቅዱሳን የሚሆንልሽ አታገኚምና እነሱን ተደገፊ፣ ለምኚ፣ ተማፀኚ፣ አልቅሺና ንገሪያቸው፡፡
  ‹‹እኔ ፣ አንተ አምላኬ ቅድስት ስላሴ ፊት ቆሜ የተበደልኩትን ለማውራት በደሌ ይከለክለኛል (ልክ እንደመቶ አለቃው ማቴ 8፤5ንና ሉቃ 7፤1 )፣ ግን ያንተን ፈቃድ ለመፈጸም በተጋደሉት ስለ ቅዱስ ጊዎርጊስ፣ ስለ ተክለሃይማኖት፣ ስለ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ስለ መጥምቀ መለኮት፣ ስተ ቅዱሳን እሳታውያን አገልጋዮችህ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ቅዱስ ገብርኤል …››በዪና ለምኚ…
  ጥቂት ለለመነ ብዙ መስጠት ያውቅበታልና የለመንሺው ይደረግልሻል፡፡ ይህን ከምትጠራጠሪ ህልውናሽን ብትጠራጠሪ ይቀላል፡፡ እነዚህ ብቻ ያልሆኑት ደግሞም ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑት ቅዱሳን እንኳን ያንቺን የዚህን አለም ታሪክ በአማላጅነታቸው ፍጹም መቀየር ይችላሉ፡፡ እንደሚደረግልሽ ደግሞ ሌላው ቀርቶ እኔ አምናለሁ…ግን ሲደረግልሽ እንደተደረገልሽ አስተውዪ፡፡ አመስግኚም፡፡
  መጽ ነገሥት ቀዳ.17 እንዲሁም እንደኔና አንቺ ጉልበት የሌለን ሃዘንተኞች፣ ችግራችንን ሰው የማይረዳን ስንሆን…ሃዘንና ችግራችንን ለእግዚአብሄር ሰዎች ቅዱሳን እንናገራለን እነሱም አንድ ጊዜ በተቀበሉት ቃልኪዳን ያማልዱንና መልስ ያሰጡናል፡፡

  ‹‹አምስቱ ሃዘናት››
  እንደኔ ሃጢአትሽ በስላሴና በቅዱሳን ፊት አንገትሽን እንዳያስደፋሽ በእመቤታችን ቃልቂዳን ቀና እንላለን፡፡ ተዓምረ ማርያም ላይ እነዚህን አምስቱን ታላላቅ ሃዘናቶችሽን አሳስቦ የለመነ ሃጢአቱን አላስብበትም የልመናውንም ቃል እሰማለሁ፡፡ ብሎ ለጇ ቃል ኪዳን ገብቷልና የኔና ያንቺን ሃጢአት ከሚያዘክር የእመቤታችንን ቅዱስ ቃልኪዳን ቢያዘክር ይቀለዋልና ልመናሽን በአምስቱ ሃዘናት ከተማጸንሽ በኋላ ብታቀርቢ ይለመንሻል፡፡
  ከሆነልሽ እንደመጽሃፉ ቃል ካልሆነልሽ ግን በራስሽ ኃዘናቶቿን አሳስቢ
  1)ስምዖን አረጋዊው‹‹ አይሁድ ልጅሽን ጠልተው፣ጸፍተው፣ገርፈው፣ ሰቅለው ይገድሉታል›› ብሎ ትንቢት በተናገረ ጊዜ ስላዘንሽው ሃዘን
  2) ልጅሽ በ 12አመቱ በቤተመቅደስ ጠፍቶብሽ 3ቀን ፈልገሽ ባጣሽው ጊዜ ስላዘንሽው ሃዘን
  3) አይሁድ ልባቸውን አጽንተው በጭካኔ ልጅሽን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር እንደገረፉት ባየሽና ባሰብሽ ጊዜ ስላዘንሽው ሃዘን
  4) አይሁድ ልጅሽን በቀራንዮ ሰቅለው እንደገደሉት ባየሽ ጊዜ ስላዘንሽው ሃዘንና
  5) ዮሴፍና ኒቆዲሞስ የልሽን ሥጋ ከመስቀል አውርደው ባአዲስ መቃብር እንዳወረዱት በየሽና ባሰብሽ ጊዜ ስላዘንሽው ሃዘን
  በዪና ልመናሽን አስከትዪ፡፡
  በነዚኅ ኀዘናት እንኳን ሩኅሩኅ ስላሴ እንኳን የጌታችን እናት እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ይቅሩና ጨካኝ ሰው እንኳ ይራራል፡፡ ይለመና፡፡
  ስለዚህ በርትተሸ ተግተሽ ጸልዪ!

  የቅዱሳን አምላክ ቅድስት ስላሴ ይለመኑሽ፡፡
  እህቴ ፣ የጌታዬ እናት ትድረስልሽ፡፡  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. it is really very teaching advise, just from your heart. May GOD bless every of your life!!

   ሰርዝ
 7. From the moment I finish reading what you wrote I know everything will be ok in the future, not only ok but will be perfect.Now I know God will listen my prayers in her name.And again, you have no idea how much it helped me, your writing. Thank you very much, I will never forget what I got from you. I will implement everything you say. Egziabher yistilign, Emebete keante/ Keanchi gar tihun.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 8. ye orthodox tewahido mimenan hulie Emebetie Kidest Dengel Mariam tselotyen tsemagn zend, beswa emnetm tsenchie endnor zend betseletwo yasbugn!!!!.....

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 9. ም ስ ጋ ና ነ ው ሌ ላ ም ን እ ላ ለ ሁ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ