እሑድ ፣23 ዲሴምበር 2012

ማኅበረቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ፮ኛውን ፓትርያርያክ ለመምረጥ የወሰነውን ውሳኔ በድጋሜ እንዲያጤነው ጠየቀ


 • ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብትከፈል አያገባኝም።” አቡነ ቀሌምንጦስ
 •  ወነአምን በአሐቲ ቤተክርስቲያን” ማኅበረቅዱሳን
 •  ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ የማይሰጥ ከሆነ ራሳችንን እናገላለን” በአሜሪካ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ምእመናን
 •  ሀራ ተዋህዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” የሚለው መሰረተ ቢስ ወሬ ግብ ምን እንደሆነ እያነጋገረ ነው።
 •  “መንግሥት በካርድ ነው የሚመርጠው ፣ ስለዚህ መንግሥት ኃጥያተኛ ነው? እኛ ማን ሆነን ነው በዕጣ ካልሆነ የምንለው? ከመንግሥት እኛ እንበልጣለን?” አቡነ ጎርጎርዮስ

(አንድ አድርገን ታህሳስ 13 2005 ዓ.ም)፡- ባለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በማበርከት በቅዱስ ሲኖዶስ እና በምእመናን ዘንድ ታማኚነት ያተረፈው ማኅበረ ቅዱሳን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ የቤተክርስቲያን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይ ለጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በደብዳቤ ማሳወቁ፣ በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ልሳኖቹ ማሳወቁ እንዲሁም የማኅበሩ አመራሮች አባቶችንና ምእመናን መደበኛ በሆኑና ባልሆኑ መንገዶች በማወያየት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መጣራቸው ይታወቃል።

ማኅበሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በይፋ በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው ሕገ ቤተክርስቲያን እንዲሻሻል፣ ቋሚ የፖትርያርክ መምረጫ ሕግ እንዲኖር፣ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ማሻሻያ የሚያጠና የቴክኒክ ኮሚቴ በይፋ እንዲቋቋም መጠየቁ ይታወሳል። የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው የማኅበሩ የሕግ ባለሙያዎች በፓትርያርክ መምረጫ ሕግ አርቃቂ ኮሚቴ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ከውስጥም ከውጭ የነበሩትን ተጽእኖዎች በመቋቋም በጎ ሚናዎች ለመጫወት ሞክሯል።

አርቃቂ ኮሚቴው የምርጫ ሂደቱን በዕጣ ይሁን የሚለውን ሃሳብ ባለመቀበሉ ማኅበሩ ቤተክርስቲያን ለፓትርያርክ  መምረጫነት ብትጠቀምበት የተሻለ ነው ብሎ የሚያምንበትን ስድስት ገጽ ረቂቅ ሕግ በደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ለምልዓተ ጉባኤው ሌሎች የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት የማኅበሩን አቋም በሦስት ተወካዮች በኩል አሳውቆአል። ይህም ንግግር  በምልዓተ ጉባኤው ሰፍኖ የነበረውን በድምጽ ብልጫ ይሁን የሚለውን ድባብ ቀይሮታል። ምልዓተ ጉባኤው በዕጣ እንዲሆን ከተስማማ በኋላ ከቅድመ ጵጵስና ጀምሮ የብአዴን አባል የሆኑት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ የኦህዴድ አባል የሆኑት አቡነ ሳዊሮስ፣ የሕወኃት አባል አቡነ ጎርጎርዮስ ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ የተሰጣቸው ተልዕኮ ውሳኔው እንዲያስቀለብሱ በተደራጀ መልኩ በመፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት አጀንዳ እንዲጠለፍ ሆኖአል። ለውሳኔው መቀልበስ የዲያቆን ዓባይነህ ካሴን የቪኦኤ ቃለመጠይቅ የማኅበረ ቅዱሳን አቋም “አቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስ ነው ፣ አታሎናል” በማለት እንደመስፈንጠሪያ እነዚሁ ሊቃነጳጳሳት ተጠቅመውበታል። መጀሪያውኑ ምልዓተ ጉባኤው በዕጣ ምርጫው ይደረግ ብሎ ሲወስን ማኅበሩን በመተማመን የወሰነ አስመሰሎበታል። ማኅበሩ የዲያቆን ዓባይነህ ካሴን መግለጫ በማኅበሩ መካነ ድር እንዲህ በማለት ገልጾታል በማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን ሓላፊነት በመጥቀስ / ዓባይነህ ካሴ ታህሣሥ 6 ቀን 2005 . ምሽት ላይ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ለቃለ ምልልስ ቀርበው በወቅታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሓሳብ መስጠታቸው ይታወሳል። ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫም ሆነ ቃለ ምልልስ መስጠት የሚችሉት የማኅበሩ ሰብሳቢ ወይም ዋና ጸሐፊ ወይም የማኅበሩ ሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ናቸው፡፡ ስለዚህ / ዓባይነህ ካሴ በቃለ ምልልሳቸው የሰጡት አስተያየት የግል አስተያየታቸው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።”

የማኅበሩ አባላት በአሜሪካ የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማመቻቸት፣ የፓል ቶክና የስልክ ውይይቶች በማዘጋጀት ምእመናን ሃሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ የበኩሉን ተወጥቷል።  የሥራ አመራር ጉባኤ አደረገ በተባለው ስብሰባ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔው ደግሞ እንዲያጤነው ጠይቆአል። ለዚህም የማኅበሩ አመራር በተናጥልና በጋራ አባቶችን የማግባበት ሥራ እንደሠሩ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ከዚህ  ጋር በተያያዘ ዜና ትናንት ማምሻውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ተገኝቶ የፓርቲውን ተልዕኮ በታማኝነት እየተወጡ የሚገኙ  ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስና አቡነ ሳዊሮስ ጋር የፓትሪያሪክ ምርጫው በአስቸኳይ ስለሚጀመርበት ሁኔታ መምከራቸው ታውቋል። በውይይቱ ወቅት አቡነ ቀሌምንጦስ “መንግስት ማኅበረ ቅዱሳንን ያስታግስልን፣ አባቶችን የሚከፋፍላቸው እርሱ ነው።” ማለታቸው ተሰምቶአል። ማኅበረ ቅዱሳንን አባ ሰላን የመሰሉ የተሃድሶ መናፍቃን ብሎጎች የሚወሩትን የፈጠራ ወሬዎች በማሰባሰብ ባለው የመንግሥት ሓላፊነት ተጠቅሞ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲከስ የቆየው ሚኒስትሩ ሃሳቡን የሚጋሩት ጳጳሳት በማግኝቱ የልብ ልብ ተሰምቶት ዛሬ ጠዋት የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዻይሬክተር አቶ ትእዛዙ በመላክ ለማስፈራራት መሞከራቸው ተሰምቷል።

ማኅበሩን በመንግሥት ፈርጣማ ክንድ ለማስመታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን የማኅበሩን አመራር አባላትም ለማስፈራራትና ተጽእኖ ለማሳደር የደህንነት ባለስልጣናት ጥረት  እያደረጉ ሲሆን የማኅበሩ አመራር አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል ።  ማኅበሩ ይህንን አቋም በድረ ገጹ ላይ “አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ”  /ማቴ. 524/ በሚል ርእስ ባስነበበው ጽሁፍ ላይ “ ……. ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለሰላሙ መስፈን አስፈላጊ የሆነ ዋጋ እንዲከፈል ግፊት በማድረግ ሊረባረቡ ይገባል፡፡ ምእመናንም ከካህናት አባቶች ጋር በጸሎት በመትጋት ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሔ እግዚአብሔር እንዲሰጠን መማጸን ይገባናል፡፡ የተጀመሩትን ሒደቶች ሁሉ በእውነተኛነትና በሚዛናዊነት እየተከታተሉ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ያለፉት ዓመታት ኣሳዘኝ ሁኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባን ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ለዚህም ይሠራል።”

የማኅበሩ አቋም ይህ ሆኖ እያለ  በቅርቡ ጡመራን የጀመረው  “ሐራ ተዋህዶ” የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” በሚል ያቀረበው ዜና የመረጃ ምንጭ ችግር እንዳለበት ተነግሮአል። ከተሳሳተ የመረጃ ምንጭ ያገኘውን ዜና እንደወረደ ማቅረቡ ከጡመራ መድረኩ አዲስነት የተነሳ በልምድ ማጣት የተከሰተ ከሆነ በሂደት እንደሚስተካከል እናምናለን። በዓላማ ማኅበሩ ቅድስት ቤተክርስቲያን የተጋረጠባትን አደጋ ለማስወገድ እየከፈለው ያለውን ዋጋ መና ለማስቀረት፣ የማኀበሩን አባላት ለመከፋፈል ያለመ ከሆነ “አንድ አድርገን” በጽኑ ትቃወማለች። የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት በጳጳሳቱ ዘንድ “አስፈሪ ግርማው” ርደተ ህሊና የሚፈጥረውን  መንግሥት እያሳደረበት ያለውን ተጽእኖ በመቋቋም እያደረገ ያለው ተጋድሎ ታደንቃለች። የቤተክርስቲያንን ልዕልና ለማረጋገጥ ከሚሰሩ አካላት ጎን ትቆማለች። “ሐራ ተዋህዶ” የጡምራ መድረክ ዓላማዋ በዚህ ሰዓት የቤተክርስቲያንን አንድነት ማስጠበቅ ከሆነ የጡምራ መድረኳ ጦማሪዎች ለግለሰቦች ያላቸውን አመለካከትና እይታ ማዕከል አድርገው ከመጻፍ እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን። ስለ ግለሰቦች ሳይሆን አንድ የምታደርገን ቤተክርስቲያ የቆመችበትን ቦታ አጢነን መረጃዎችን ብናስተላልፍ መልካም ነው ትላለች፡፡ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ቤተክርስቲያን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ተገንዝበው፣ ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ልዕልና ከፍ ለማድረግ የሚደረጉ ሁለንተናዊ ትግል በተቀናጀ መልኩ በመፈጸምና ልዩነት የሚፈጥሩ ጥቃቅን ጉዳዮች በመተው በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋልን።

ቸር ወሬ ያሰማን!

21 አስተያየቶች:

 1. ከቅድመ ጵጵስና ጀምሮ የብአዴን አባል የሆኑት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ የኦህዴድ አባል የሆኑት አቡነ ሳዊሮስ፣ የሕወኃት አባል አቡነ ጎርጎርዮስ ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ የተሰጣቸው ተልዕኮ ውሳኔው እንዲያስቀለብሱ በተደራጀ መልኩ በመፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት አጀንዳ እንዲጠለፍ ሆኖአል።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 2. betam girum tsihuf new. Bezih wekit anid yemiadergenin enji yemikefafilenin anifeligim!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. በእውነት ደስ የሚል መረጃ ነው-እውነታው መንግሥት ከቤተክርስቲያናችን ጉዳይ እጁን ያውጣ ነው-መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ይከበር!!! በማወቅም ይሁን ያለ ማወቅ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ፖለቲካ ውስጥ የሚገኙ አባቶች ከፖለቲካው(መብታቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ) ይልቅ ለእምነታቸው ሊቆሙ ይገባል-እነሱም ቢሆኑ ከቤተክርስቲያን መከፋፈል የሚያገኙት ጥቅም ያለ አይመስለኝም የመክፈል ዓላማ ከሌላቸው በስተቀር-አንድነታችንን እግዚአብሔር ያጽናልን አሜን!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 4. Good Presentation. May God strengthen you .

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 5. እውነት ነው፤ አኹን እየተመካከሩ ተደጋግፎ መሥሪያ ጊዜ ነው። ይኹን እንጂ ኋላ ለመቀልበስ አስቸጋሪ የሚኾን ችግር ሊፈጠር ሲል ግን አስቀድሞ ማስጠንቀቅ ግድ ስለሚኾን ላማበርም ኾነ ለግለሰብ በማሰብ አለባብሶ ማለፍም አያሻም። የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት የማይገነዘብ እውነተኛ የተዋሕዶ ልጅ ያለ አይመስለኝም። ነገር ግን፤ ይልቁንም እንጂ፤ በዚህ ግንዛቤ ምክንያት ማኅበሩ ባኹኑ ሰዓት አንዳች ስሕተት ቢሠራ ብዙ ሰው ይዞ ገደል ሊገባ እንደሚችል የተረዱ ወገኖች አንገት ላንገት እስተመተናነቅ ድረስ ስንኳ ቢታገሉት አይፈረድባቸውም። ዐላማቸው ቤት ክሲያኗን፣ ራሱን ማኅበሩንም ጭምር ለማዳን ነውና። እንዲህ ያለው "ደቂቀ እምየ ተበአሱ በእንቲአየ" (የናቴ ልጆች ስለኔ እኔን ተጣሉኝ) ካለው ይገባል።

  አኹን እዚህ ባቀረባችኹት ስንኳ እንዲህ ብላችኋል፦

  "...ማኅበሩ ቤተክርስቲያን ለፓትርያርክ መምረጫነት ብትጠቀምበት የተሻለ ነው ብሎ የሚያምንበትን ስድስት ገጽ ረቂቅ ሕግ በደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ለምልዓተ ጉባኤው ሌሎች የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት የማኅበሩን አቋም በሦስት ተወካዮች በኩል አሳውቆአል። ይህም ንግግር በምልዓተ ጉባኤው ሰፍኖ የነበረውን በድምጽ ብልጫ ይሁን የሚለውን ድባብ ቀይሮታል..."

  የኸ ታዲያ ምን ማለት ነው። ማኅበሩ በምርጫው ተስማምቶ በኺደቱ ላይ አስተያየት እየሰጠ ያለ አይመስልም? ወይ ስድስቱንም ገጽ አስነብቡን እንጂ እናንተም ብትኾኑ አራዶች "በጨቡ" የሚሉትን ዐይነት ጨወት አትጫወቱ።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 6. Thank you. You answered my question. We all know who adminster this Hara blog....they are opportunistic. MK is in our blood, we do not follow members in MK, we do implement the vision of MK. So, Go MK and keep up with the god job.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 7. Dear Andadrgen may GOD BLESS U.

  I was expecting such letter from u, because, Hara Tewahedo did get this information from wrong source. They should take care before posting it online. pls give them ur expertise.

  የማኅበሩ አቋም ይህ ሆኖ እያለ በቅርቡ ጡመራን የጀመረው “ሐራ ተዋህዶ” የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” በሚል ያቀረበው ዜና የመረጃ ምንጭ ችግር እንዳለበት ተነግሮአል። ከተሳሳተ የመረጃ ምንጭ ያገኘውን ዜና እንደወረደ ማቅረቡ ከጡመራ መድረኩ አዲስነት የተነሳ በልምድ ማጣት የተከሰተ ከሆነ በሂደት እንደሚስተካከል እናምናለን። በዓላማ ማኅበሩ ቅድስት ቤተክርስቲያን የተጋረጠባትን አደጋ ለማስወገድ እየከፈለው ያለውን ዋጋ መና ለማስቀረት፣ የማኀበሩን አባላት ለመከፋፈል ያለመ ከሆነ “አንድ አድርገን” በጽኑ ትቃወማለች።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 8. ተመስገን!!! እኔም ዜናውን ቅዳሜ ለት አንብቤ በማህበረ ቅዱሳን አመራሮች መካከል መለያየት የተፈጠረ መስሎኝ በጣም አዝኜ ነበር!! እንድነታችንን አምላክ ይጠብቅልን!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 9. i always understand the voice of MK from his blog so please everybody to know the stand of MK it is better to read his web-site or ask by telephone the concerned body only!!!!!!!!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 10. ሁላችንም የቆምንበትን ጊዜ እናስተውል ፤ ስለ ግለሰቦች ማውራት ትተተን ስለ አንዲት ቤተክርስትያን እናስብ ፤ ማህበሩ የቻለውን ሲያደርግ ተመልክተናል ፤ አሁን ግን ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ ለራሱን የያገባኛል ጥያቄ የሚያነሳበት ጊዜ ላይ እንደኛለን ፤ ማንም ያልተጨበጠ መረጃ በድረ ገጽ ላይ ቢለቅ ልንረበሽ አይገባም ፤ ችግር አይኖርም አይባልም ችግር ቢኖርም የማባባስ ስራ ማንም መስራት የለበትም ፤ የተፈጠረው ችግር የሚፈታበት መንገድ ላይ ማተኮሩ የተሻለ ይመስለኛል ፤ ለማንኛውም እኛን የሚጠብቅ አያንቀላፋም ..፣፣፣፣ ተብሏል 10 q FOR UR INFORMATION

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. ሁላችንም የቆምንበትን ጊዜ እናስተውል ፤ ስለ ግለሰቦች ማውራት ትተተን ስለ አንዲት ቤተክርስትያን እናስብ ፤ ማህበሩ የቻለውን ሲያደርግ ተመልክተናል ፤ አሁን ግን ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ ለራሱን የያገባኛል ጥያቄ የሚያነሳበት ጊዜ ላይ እንደኛለን ፤ ማንም ያልተጨበጠ መረጃ በድረ ገጽ ላይ ቢለቅ ልንረበሽ አይገባም ፤ ችግር አይኖርም አይባልም ችግር ቢኖርም የማባባስ ስራ ማንም መስራት የለበትም ፤ የተፈጠረው ችግር የሚፈታበት መንገድ ላይ ማተኮሩ የተሻለ ይመስለኛል ፤ ለማንኛውም እኛን የሚጠብቅ አያንቀላፋም ..፣፣፣፣ ተብሏል 10 q FOR UR INFORMATION

   ሰርዝ
 11. mahiberu sew medibo ke menigist gar mesiratun mine tilalachihu.....

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 12. ስለ ግለሰቦች ሳይሆን አንድ የምታደርገን ቤተክርስቲያ የቆመችበትን ቦታ አጢነን መረጃዎችን ብናስተላልፍ መልካም ነው ትላለች፡፡ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ቤተክርስቲያን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ተገንዝበው፣ ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ልዕልና ከፍ ለማድረግ የሚደረጉ ሁለንተናዊ ትግል በተቀናጀ መልኩ በመፈጸምና ልዩነት የሚፈጥሩ ጥቃቅን ጉዳዮች በመተው በአንድነት እንድንቆም

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 13. I think we all are matured and we don't take up all information rather we refine before reaching whatever conclusion. Hence, no need to defend Hara Tewahidos news as the truth will be uncovered finally what eve time it takes. I agree with your saying that we need to defend the church than an individual or an association. But you also contradict with this saying by defending the MK. We all know that MK have done a lot to the church. But at this critical time if it stands against the will of the church and the believers, we we definitely will stand with the church. An association will come and go but our church prevails for ever.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. በዚህ ዘመን የሚፈለገው እንደዚህ አይነት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ ምክንያቱም በሰማነውና ባየነው መረጃ ሁሉ ወደነፈሰበት የምንጓዝ ሳይሆን መረጃን በደንብ ፊልተር የምናደርግ መሆን መቻል አለብን፡፡ እርባና የሚኖረው የሰው ወይም የማህበር ቲፎዞ መሆን ሳይሆን ስለአንዲት ቤተ ክርስቲያንና ስለአንዲት ሃይማኖት ተቆርቋሪና ባለድርሻ መሆን ነው፡፡ ይህም ሲባል እግዚአብሔር አምላክ በደሙ የዋጃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንድትጠፋ የሚተዋት ሆኖ ሳይሆን እኛ ለራሳችን እግዚአብሔር የሰጠንን ሃላፊነት መወጣት እንድንችልና ለበረከቱ መዘጋጀት እንችል ዘንድ ነው፡፡ ለዚህም የልዑል እግዚአብሔር ቸርነቱ ትርዳን አሜን፡፡

   ሰርዝ
 14. What a nice piece of information, longlive for MK...(we all know MK is doing good works),may GOD give u strength & unity for our church.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 15. እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ መቼም ቢሆን እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን አይተዋትም፡፡ እኛ ግን ጸንተና በመቆም በጸሎት ወደ አምላካችን እግዚአብሔርን መጠየቅ ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 16. የማኅበሩ አቋም ይህ ሆኖ እያለ በቅርቡ ጡመራን የጀመረው “ሐራ ተዋህዶ” የተሰኘው የጡመራ መድረክ
  i am also strongly accept this idea
  “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” በሚል ያቀረበው ዜና የመረጃ ምንጭ ችግር እንዳለበት ተነግሮአል። ከተሳሳተ የመረጃ ምንጭ ያገኘውን ዜና እንደወረደ ማቅረቡ ከጡመራ መድረኩ አዲስነት የተነሳ በልምድ ማጣት የተከሰተ ከሆነ በሂደት እንደሚስተካከል እናምናለን። በዓላማ ማኅበሩ ቅድስት ቤተክርስቲያን የተጋረጠባትን አደጋ ለማስወገድ እየከፈለው ያለውን ዋጋ መና ለማስቀረት፣ የማኀበሩን አባላት ለመከፋፈል ያለመ ከሆነ “አንድ አድርገን” በጽኑ ትቃወማለች።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 17. betam dese yemile brogram new eyeteketatelekut new fetsamiyachewen yasamerew.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ