ሰኞ ፣29 ኤፕሪል 2013

ዘሰሙነ ሕማማት(አንድ አድርገን ሚያዚያ 21 2005 ዓ.ም)፡- ሰሙነ ሕማማት በነብዩ ኢሳያስ ‹‹ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ ፤ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ ፤ እኛ ግን እንደተመታ ፤ በእግዚአብሔር እንደተቀሰፈ ቆጠርነው፡፡ እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ ፤ ስለበደላችን ደቀቀ ፤ የደኅንነታችንም ተግሳጽ በእርሱ ላይ ነበረ ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን›› ኢሳያስ 53 ፤4 ተብሎ የተነገረው ቃል ተፈጽሞ ፤ ጌታችን ለድኅነተ ዓለም ሲል በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ ከሆሳህና ማግስት እስከ ትንሳኤ ያለው የጾመ እግዚእነ መዝጊያ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ 


በማኅበረ ቅዱሳን የሚታተመው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ልዩ የ2004 ዓ.ም እትም ስለ ሰሙነ ሕማማት ፤ ሥርዓተ ሰሙነ ሕማማት ፤ ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት ፤ ሕማማተ እግዚእነ በልሳነ አበው ፤ በሰሙነ ሕማማት የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ፤ መጽሐፈ ግብረ ሕማማት እና ፍኖተ መስቀል በሚል አብይ አርዕስቶች የተከፋፈለ ባለ 30 ገጽ ትንሽ መጽሐፍ አሳትሞ ነበር ፡፡ አንድ አድርገን ይህን መጽሐፍ በዚህ ወቅት ማግኝት ላልቻሉ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ምዕመናን ወደ ፒዲፍ በመቀየር አቅርባላችኋለች ፡፡ በርካታ እውቀትን ይገኙበታል ያንብቡት…

የሳምንቱ የአንድ አድርገን ስጦታ

8 አስተያየቶች:

 1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን አንድ አድርገን ግሩም ነው እኔም አንድ ድረ ገጽ ላይ ያገኘሁትን እንካችሁ .. የመስቀሉ መንገድ
  ጌታ ለፍርድ በቀረበበት ዘመን ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ ነበር ። ይሁዳ ከአራቱ የሮም ክፍለ አገሮች አንዷ ናት። ገዥው የሮም ዋና ወኪል ወይም እንደራሴ ገዥ ነው። ሮማዊ ዜጋ ሆኖ ወደ ቄሣር ይግባኝ ካላለ የገዥው ፍርድ የመጨረሻው ነው። ስለዚህም ለጲላጦስ ሥልጣኑ ያልተደላደለ መሠረት ላይ አልነበረምና ይህን ሊፈራ የተገባው አይደለም።(በሌላ አባባል እንደኛው ሃይለማርያም ሳይሆን እንደመለስ አይነት ስልጣን ነበረው) ፍትሕ እንዳይዛባ ቢያደርግ ቢያንስ ሮማዊው የሥልጣን ተዋረድ ይደግፈው ነበር እንጂ አይኮንነውም። ኅሊናውን ለራሱ ትተን ማለት ነው። ጌታ ወደ ጲላጦስ ከመቅረቡ በፊት የአይሁድ ሽማግሎችና የካህናት አለቆች ሊያጠፉት የተደጋገመ ሙከራ ምኞት ተመኝተዋል ሙከራም አድርገዋል። እነዚህ ያለሕግ ሊገድሉት የሞከሩባቸው ናቸው።የመጨረሻውን የተቀነባበረና የተሳካ ግድያ ትተን የቀደሙትን ለማየትእነዚህን ጥቅሶች ተመልከቱ፤ ማር. 12፥12፤ ሉቃ. 4፥29፤ ዮሐ. 5፥16-18፤
  7፥1 እና 25፤ 11፥53፤ ወዘተ። ጲላጦስ የይሁዳ ጠቅላላ ገዥ ሆኖ በኢየሩሳሌም ፕራይቶሪዮን የሚባል የገዥው መኖሪያ ግቢ ቢኖረውም ዋና መቀመጫው የነበረው በኢየሩሳሌም ሳይሆን በቂሣርያ ነበረ። ሆኖም እንደ ገዢ በክልሉ ሁሉ የመገኘት ኃላፊነት አለበት። ይህ ጌታ የተሰቀለበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ወቅት ነው። በአይሁድ ዘንድ ከታላላቅ በዓላት አንዱ ነው፤ ብዙም አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገቡ አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሚገኙበት ጊዜ በመሆኑ እንደ ገዥ በዚያ የመገኘት ግዴታ አለበት። ጲላጦስ ስለ ኢየሱስ ጥልቅ እውቀት ያለው ሰው ባይሆንም በጊዜው ስለሆነው ነገር በቂ ግንዛቤ ያለው ሰው ነው። የጲላጦስ ፍርድ በጥቂቱ ጥቅም ከመጠበቅ ጋር ይቆራኛል ብለን ማሰብ እንችላን። ተወዳጅ ሆኖለመገኘት። ለገዥው መንግሥት ጥቅም ነውም ማለት ያስችላል፤ ኢየሱስ ሌላ ተደራቢ ምድራዊ ንጉሥ ተደርጎ ከተወሰደ ማለት ነው። ጥንትም በዘመናችንም ፍትሕ ቦታውን ልቅቆ ያውቃል ይለቅቃልም።
  አስለቃቂዎቹ ግን ምክንያታቸው ይለያያል። ብዙ ጊዜ ለራስ፥ ማለትም፥
  ፍትሑን አቅመ ቢስ ለሚያደርጉት ሰዎች ጥቅም ተብሎ የሚደረግ ሲሆን
  ሌላው ግፊት ደግሞ በቀል ነው።... ምንጭ ዕዝራ ስነ ጽሑፍ፥ ዘላለም መንግሥቱ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 2. ......ብዙ ምስክሮችና ፍርደ-ገምድል ዳኛ
  ጳላጦስ ወደ ገዥነት የመጣው ምንም የገዥነት፥ የጦር ስልት፥ የገንዘብ
  አስተዳደር እውቀት ሳይኖረው አይደለም። ይህ የዳኝነትና የፍትሕ
  እውቀትንም ይጨምራል። ከምርመራውና ከወሰዳቸው ስርዓቶች ይህንን
  መረዳት ይቻላል። በቂ ምስክሮችን አድምጦአል። ከራሱ ኅሊና እስከ
  ሚስቱ መልእክት፥ እስከ ሌላ ገዥ ምስክርነት ሰምቶአል። እነዚህን
  አሻፈረኝ ያላቸውን ምስክሮች እንስማ።
  1. ጲላጦስ ኢየሱስን እንኳን የሚያስገድለው የሚያሳስረውም በደል
  እንደሌለበት አውቋል። ስለዚህ ሊለቅቀው የሚያስችለውን አማራጭ
  ሊጠቀም ሞከረ። ማቴ. 27፥ 17-18 እንዲህ ይላል፤ እንግዲህ እነርሱ
  ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ፥ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን
  ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ በቅንዓት አሳልፈው እንደ
  ሰጡት ያውቅ ነበርና። እዚህ ላይ ባለፈው እንደተመለከትነው የሕዝብ
  ሰው እንደ ሳኦል ይህም ሰው በውስጡ የእርስ በርስ ጦርነት
  የሚካሄድበት ሜዳ ይመስላል። በቅንዓት እንደሰጡት እያወቀ ግን
  በተቃራኒው መንገድ አልሄደም።
  በሉቃ. 23፥2 ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ
  ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው
  ይከሱት ጀመር ተብሎ ተጽፎአል። ግብር እንዳይሰጥ አልከለከለም፤
  ምድራዊ ንጉሥ እንደሆነም አልተናገረም። እርግጥ ቀራጮችን ጠርቶአል
  እንዲከተሉት፤ ሌዊ ቀራጭ ነበረ። ዘኬዎስም የተለወጠ ሰው ሆኖአል።
  የኃጢአተኞችና የቀራጮች ወዳጅ ተብሎም ተጠርቶአል። ግን ይህ
  የመክሰሻ አቅም የለውም።
  2. የጲላጦስ ልማዱና ቸርነቱ አንድ ሰው በዚህ በዓላቸው መፍታቱ
  ነበር። በዚህ በዓል ኢየሱስን ሊፈታ ያቀረበውን አሳብ በሁከትና ነፍሰ
  ገዳይነት የታሰረውን በርባንን እንዲፈታላቸው ጠየቁ። የካህናት አለቆች
  ሕዝቡን ያባበሉት ይህ ሰው እንዲፈታላቸው ነው። ጲላጦስ ይህ ሰው
  የታሰረበትን ምክንያት ያውቀዋል። በካህናቱ አሳሳቢነት ይህ ሰው
  እንዲፈታ መጠየቃቸው ራሱ እንቢ እንዲል ወይም የኢየሱስን ንጽህና
  ሊያሳየው ይችላል። ይህንንም ገፋው።
  3. ከቤተ ሰቡ ውስጥ የገዛ ሚስቱ የሆነባትን አስረድታ ላከችበት። ማቴ.
  27፥19 ይህን ይላል፤ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፥ ስለ
  እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም
  አታድርግ ብላ ላከችበት። ምናልባት ሊያድነው ለመጣሩ ግፊት
  አሳድሮበት ካልሆነ በቀር ለዚህም የሰጠው ግልጥ ምላሽ የለም።
  4. ጲላጦስ ኢየሱስን በመረመረበት ምርመራው የገሊላ ሰው መሆኑን
  ባወቀ ጊዜ የገሊላ ገዥ የነበረው ሄሮድስ በኢየሩሳሌም ነበረና ወደ እርሱ
  ላከው፤ ሉቃ. 23፥6-15። ሄሮድስም መርምሮ ምንም አላገኘበትምና
  ምንም በደል አለማግኘቱን አረጋግጦ መልሶ ላከው። በዚህ ጊዜም
  ንጹሕነቱን አረጋግጦ፥ ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህን ሰው ወደ እኔ
  አመጣችሁት፤ እነሆም፥ በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ
  በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም። ሄሮድስም ደግሞ ምንም
  አላገኘም፤ ወደ እኛ መልሶታልና፤ እነሆም፥ ለሞት የሚያደርሰው ምንም
  አላደረገም፤ እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አለ፤ ሉቃ. 23፥ 14-16። ቀጥቼ
  ሲል እንዲያውም አካላዊ ቅጣት ምናልባት ምናልባት ቢኖርበት እንጂ
  ቀጥቼው የሚለው ቃል (παιδεύσας αὐτὸν) አካላዊ ቅጣትን
  አያመለክትም፤ አስጠንቅቄ፥ አስተምሬ፥ አስረድቼ ማለቱ ነው። በሁለት
  የተቀመሙ ሮማዊ ገዦች ተመርምሮ በደል አልተገኘበትም። ንጹሕ ነው
  ግን ነጻ አልሆነም...ዕዝራ ስነ ጽሑፍ፥ ዘላለም መንግሥቱ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. ....የሕዝቡን ፈቃድ አገልጋይ መሪ
  ጲላጦስ እነዚህን ሁሉ ምስክሮች ይስማ እንጂ ኢየሱስን እንዲሰቀል
  አሳልፎ ሰጠው። ስለምን አሳልፎ ሰጠው? እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ
  ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል
  በረታ። ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት። ያንን
  የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን
  አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው። ሉቃ.
  23፥23-25።
  ጲላጦስ ጌታን አሳልፎ የሰጠው ሕዝቡን ለማስደሰት ብቻ ሲል ነው።
  የሕዝቡ ጩኸትና የካህናት አለቆቹ ቃል በረታ። ምንም ቢበረታ ያ
  ጩኸትና ቃል የአንድ ጎራ ጩኸትና ቃል እንጂ የገዢ ወይም የፍትሕ
  ቃል አይደለም። ጲላጦስ የተሸነፈው ልመናቸው እንዲሆንላቸው፥
  የተንበረከከውም ለፈቃዳቸው ነው። ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ እጁን
  ታጠበ። ይህ የንጽሕናው ምልክታዊ ድርጊት ነው ወይስ ንጹህ ደም
  አሳልፎ የመስጠቱ፥ የድካሙ፥ የወንጀሉ ስስ መሸፈኛ ሻሽ ነው?
  የሕዝብ ፈቃድ በጲላጦስ አገዛዝም ሲሠለጥን ይታያል። ጲላጦስም
  የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ
  እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ፤ ማር. 15፥15። ምን ሊያደርግ ወዶ? የሕዝቡን
  ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ! በመጨረሻ ፍርድ ቢገመደል ወይም ከስፍራው
  ቢወገድ ግድ አጣ። አንድ ሰው ሞቶ አንድ ጎራ ሕዝብ ከተደሰተ ምንም
  አይደለም አለ። ይህ ግን አንድ ሰው ብቻ አልነበረም። ይህ የተፈረደበት
  ሰው እግዚአብሔር ወልድ ነው። እውነት ነው። ይህን እውነት ሊያውቅ
  ጥቂት ቀርቦ ነበር። ሊያውቀው እድል አግኝቶ ነበር፤ ነገር ግን እውነት
  ምንድርነው? ብሎ ጠየቀ እንጂ መልሱንም የፈለገ አይመስልም፤ ዮሐ. 18፥38። የምንመለከተው ጲላጦስና ለሕዝብ ስሜት ሲባል እውነት ሲሰቀል ቢሆንም የጌታን ፍርድ
  ፈራጁ፥ ወይም ቀዳጁ አድርገን ጲላጦስ
  እንዳንወስደው እፈልጋለሁ። ጲላጦስ በመስቀሉ ታሪክ ውስጥ አንድ
  መሣሪያና ተዋናይ እንጂ ሌላ አይደለም። ዋናው ባለ ታሪክ ጌታችንና
  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ገድሉም መስቀሉ ነው። ቀድሞም
  የመጣው ለዚያ ጊዜ ነው፤ በመስቀል መሞቱና ኃጢአታችንን መሸከሙ
  ከዓለም መሠረት ጀምሮ እቅድ የተያዘለት ነው (ራእ፣ 13፥8) እንጂ
  ከመቶዎች ዓመታት በፊት በነቢያት የተነገረ ብቻ አይደለም። ነፍሱን
  ሊያኖራት፥ ሊያነሣትም ሥልጣን ያለው እርሱ ራሱን ወድዶ ነው ስለ
  ኃጢአታችን አሳልፎ የሰጠው። ስለ ኢየሱስ ስናስብ ፍትሕ ተጓድሎበት
  በስሕተት እንደተገደለ ከቶም ማሰብ የለብንም። ይህ ዘላለማዊ መለኮታዊ
  ንድፍ ግን ጲላጦስን የሳተ መሪ ከመሆን ነፃ አያደርገውም። http://good-amharic-books.com/images/PDFs/ezra13.pdf

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 4. መቅረዝ Mekrezzetewahdo-Blog
  † የዳንነው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ስለሰጠው ነውን? †
  ይሁዳ ጌታን አሳልፎ እንደሚሰጥ ትንቢት የተነገረበት እግዚአብሔር እንደዚያ ክፉ እንደሚሆን አስቀድሞ ስለሚያውቅ እንጂ አስቀድሞ ለዚያ ነገር ስለወሰነው አይደለም፡፡ እንደዚህማ ካልሆነ ሰይጣንም አስቀድሞ ለዚያ የተወሰነ ነበርና አይፈረድበትም ልንል ነው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ ሰይጣንም ይሁን ይሁዳ ከራሳቸው ክፋት የተነሣ እንጂ እግዚአብሔር ለዚያ ስለወሰናቸው ከእግዚአብሔር አንድነት አልተለዩም፡፡ ጌታችን የሞተው፣ እኛም የዳንነው ይሁዳ አሳልፎ ስለሰጠው አይደለም፡፡ የዳንነው የክፉዎችን ክፋት በጥበቡ ለእኛ ጥቅም በሚያደርግ በጥበበኛው እግዚአብሔር ነው፡፡
  ይሁዳ ቢፈጠርም ባይፈጠርም ጌታችን መሞቱ አይቀርም፡፡ እንዴት ለሞት ተላልፎ እንደሚሰጥ ግን የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው፡፡ጥበቡ ከሕሊናት በላይ ስለሆነ አይመረመርም፡፡ ስለዚህ ማንም ቢሆን ይሁዳ ክርስቶስን አሳልፎ ይሰጥ ዘንድ የተዘጋጀ ሰው ነው ብሎ በስንፍና የሚናገር አይኑር፡፡
  *** ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ማቴ.26፡17-18ን ሲተጉም ከተናገረው የተወሰደ፡፡ ***ከጴጥሮስ ደሮ እስኪጮህ ድረስ ሦስት ጊዜ መካድ፣ ከይሁዳም ከክፋት አለመመለስ ምን እንማራለን? †
  ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና” ባለ ጊዜ ጴጥሮስ ግን “ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም” ይል ነበር። ሐዋርያው በጸጋ እግዚአብሔር ከመተማመን ይልቅ በራሱ ጕልበት ይመካ ነበር ማለት ነው፡፡
  ይሁዳ ደግሞ ከክፋቱ እንዲመለስ በጣም ብዙ ጊዜ ተመክሮአል፡፡ “ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል”፤ “ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው”፤ “የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት”፤ “ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር”፤ “አንተ አልህ” ቢባልም በፍጹም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይኸን ያህል ጌታ እንዲመለስ ቢረዳውም ሊመለስ አልቻለም፡፡
  ከዚህ መማር እንደምንችለው ኃይልና ጸጋ ከላይ ካልተሰጠው በቀር ሰው በራሱ ጥረትና ብርታት ሊድን አይችልም፡፡ ልክ እንደዚሁ ምንም ያህል ኃይልና ጸጋ ከላይ ቢሰጠውም አንድ ሰው ፈቃድ ከሌለው እንዲሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ መዳን አይችልም፡፡ ከጴጥሮስና ከይሁዳ የምንማረው ይህን ነው፡፡ ሰው በስንፍና አልጋ ላይ ለጥ ብሎ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ሊድን አይችልም፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያን በምግባርሩና በትሩፋቱ ብቻ ሊድን አይችልም፡፡ እግዚአብሔር በኃጢአት እየተመላለስን እርሱን ብቻ ተስፋ እንድናደርግ ፈቃዱ አይደለም፡፡ ልክ እንደዚሁ ትምክሕተኞች እንድንሆንም ሁሉንም እኛ እንድንወጣው አልፈቀደም፡፡ ከዚህ መረዳት እንደምንችለው በሁለቱም በኩል እኛን ሊጐዱ የሚችሉ ነገሮችን ነው ያስወገደልን ማለት ነው፡፡
  ***ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ማቴ.26፡30-33ን ሲተረጕም ከተናገረው የተወሰደ***

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 5. ሰሙነ ሕማማት

  በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁ ወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተ ትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታይበት ጊዜ ነው፡፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς, Hagia kai Megale Hebdomas ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት፡፡
  የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ክርስቲያኖች ያከብሩት እንደነበር የሚያሳዩ ጥንታውያን መዛግብት አሉ፡፡ በሕግ ደረጃ ክርስቲያኖች በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም ሥራ ነጻ ሆነው፣ ፍርድ ቤቶችም ተዘግተው እንዲከበሩ የወሰነው ደግሞ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡
  እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዳዲስ ክርስቲያኖች ለመጠመቅ ይመርጡት የነበረው ጊዜ የትንሣኤን ቀን ነበር፡፡ ለዚህም ሁለት ዓይነት ምክንያቶች ነበሯቸው፡፡ የመጀመርያው ሰሙነ ሕማማትን በልዩ ሁኔታ ጾመው በትንሣኤው ቀን መጠመቁ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ኃይል ስለሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት መጠመቅ ከክርስቶስ ጋር ሞቶ ከክርስቶስ ጋር መነሳት ነውና ጥምቀቱን ከትንሣኤው ጋር አያይዘውት ነበር፡፡
  የሕማማት ሰሞን የኦሪት ጊዜን የሚያስታውስ ሰሞን ነው፡፡ አዳዲስ ክርስቲያኖቸም ይህንን ሰሞን ያለፈ ሕይወታቸውን ለማስታወስ እና ለማልቀስ ብሎም ራሳቸውን ወደ ሐዲስ ዘመን ለመለወጥ ይጠቀሙበት ነበር፡፡
  በመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ከዓርብ ጀምሮ ሰሙነ ሕማማትን ማክበር የተዘወተረ ነበር፡፡ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግን ስድስቱንም ቀን ማክበር የክርስቲያኖች ሥርዓት እየሆነ መጣ፡፡ ለዚሀም መነሻ የሆነው የአባቶቻችን ቀኖና የተሰኘው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የተደነገጉ ቀኖናት መዝገብ በቦታው መዳረስ ነው፡፡ በዚህ መዝገብ ዐንቀጽ 5 ቁጥር 19 ላይ «በሰሞነ ሕማማት ከሳምንቱ ሁለተኛ ቀን (ሰኞ) እስከ ቅዳሜ የሰንበት መዘጋጃ ቀን ድረስ ጹሙ፡፡ በእነዚህም ጊዜያት ከእንጀራ እና ከጨው፣ ከማባያም በቀር ሌላ ነገር አትብሉ፡፡ ለመጠጥም ውኃ ብቻ ይሁንላችሁ» ይላል፡፡
  የኛም ግብረ ሕማማት ይህንኑ የሐዋርያት ቀኖና በመጥቀስ በክፍል አንድ ሠላሳ አንደኛ ትእዛዝ በሚለው ርእስ ሥር «በሕማማት ሰሞን ከእንጀራ፣ ከጨው እና ከውኃ በቀር ምንም ምንም አትብሉ» ይላል፡፡
  በ260 ዓም ለባሲሊደስ በጻፈው ደብዳቤ እያንዳንዷን የሰሞነ ሕማማት ቀን እና ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር በማያያዝ ገልጾ ነበር፡፡ በ2ኛው ወይንም በ3ኛው መክዘ ተሰባስቦ መጠረዙ የሚነገርለት የሶርያው ዲድስቅልያም ሰሙነ ሕማማት እንዴት መጾም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ አቡሊዲስ ዘሮም በጻፈው የሐዋርያት ትውፊት (215 ዓም) ስለ ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ይደነግጋል፡፡ እያንዳንዷንም ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር ያገናኛታል፡፡
  ሰሙነ ሕማማት አሁን ያለውን መልክ የያዘው በ4ኛው መክዘ በኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ በቄርሎስ ዘመን ነው፡፡ ፓትርያርክ ቄርሎስ በመጨረሻዎቹ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ በፊት ያለውን ሰሙነ ሕማማት እያንዳንዱን ቀን በማሰብ የሚከበርበትን ሥርዓት ሠርቶ ነበር፡፡ ከ381 እስከ 385 ወደ ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሄደችው ኤገርያ የተባለች ስፔናዊ በኢየሩሳሌም እንዴት ሰሙነ ሕማማት ይከበር እንደነበር የታሪክ መዝገብ ትታልናለች፡፡
  ኤገርያ በጉዞ ማስታወሻዋ እንዲህ ትተርክልናለች
  «በዓሉ የሚጀምረው በዕለተ እሑድ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ስለ ዓልዓዛር ትንሣኤ የሚገልጠው የወንጌል ክፍል ጠዋት ይነበባል፡፡ በሆሳዕና ዕለት ከሰዓት በኋላ ሁሉም ሰው ወደ ደብረ ዘይት ይወጣል፡፡ ከዚያም በጸጥታ የዘንባባ ዛፍ ተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል፡፡ ይህንንም በመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይፈጽማሉ፡፡ ይህም ጌታችን ማታ ማታ ከከተማዋ ወጥቶ በደብረ ዘይት ያደረገውን ጸሎት ለማስታወስ ነው፡፡
  በጸሎተ ኀሙስ ጠዋት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ (ይህም በዓመቱ ውስጥ በመስቀሉ መቅደስ ላይ የሚደረግ ቅዳሴ ነው)፡፡ ከሰዓት በኋላ ሌላ ቅዳሴ ተቀድሶ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ቆስጠንጢኖስ ባሠራው በኤሊዎና ቤተ ክርስቲያን ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መብራት ያበራሉ፡፡ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ደግሞ ወደ ጌቴ ሴማኒ ይጓዛሉ፡፡ በዚያም እስከ ንጋት ቆይተው የዓርብ ማለዳውን ወንጌል ለማንበብ ወደ ጎልጎታ ይመለሳሉ፡፡
  ዓርብ ማለዳ ሁሉም መስቀሉን (በኢየሩሳሌም የነበረውን የጌታን መስቀል ነው) ቤተ ክርስቲያን አልባሳት ያስጌጡታል፡፡ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በጎልጎታ በተሰቀለበት ላይ ሁሉም ተሰብስቦ ጸሎት ያደርሳል፣ ያለቅሳል፣ ያዝናል፡፡ በሠርክ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ወደ ስቅለቱ ቦታ በመጓዝ በዚያ ስለ ስቅለቱ እና መቃብሩ የሚገልጠው ወንጌል ይነበባል፡፡ ቅዳሜ ዕለት በየቤተ ክርስቲያኑ መብራት ይበራል፡፡». read the rest....http://www.danielkibret.com/2012/04/v-behaviorurldefaultvmlo.html?spref=fb

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 6. “አይሁድ በጌታ ላይ ሲሳለቁበት ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን አሉት፡፡ እርሱም ከመውረድ በላይ የሆነ ተአምር ያሳያቸው ነበር፡፡ በዓለም ታሪክ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ ካልሆነ በስተቀር ተደርጐ የማያውቅ ምልክት አሳያቸው፡፡ ከስድስት እስከ ዘጠየእግዚአብሔርን ልጅ የኋሊት አሠሩት፡፡ እነርሱ በቁጣ ጐተቱት፤ እርሱ ግን በፍቅር ተከተላቸው፡፡ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግም አፉን ሳይከፍት ተከተላቸው፡፡
  ሊቃነ መላእክት በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን እርሱን በፍርድ አደባባይ አቆሙት፤
  ኃጢአትን ለሚያስተሠርይ እርሱን “ኃጢአተኛ ነህ” አሉት፤
  በመኳንንቱ ላይ የሚፈርድ እርሱን “ይሙት በቃ” ብለው ፈረዱበት፤
  ለሱራፌል ዘውድን በሚደፋላቸው በእርሱ የእሾኽ አክሊል ደፉበት፤
  ለኪሩቤል ግርማን ለሚያለብሳቸው ለእርሱ ለመዘበት ቀይ ግምጃን አለበሱት፤
  ኪሩቤል በእሳት ክንፋቸው ተሸፍነው ለሚሰወሩለት ለእርሱ ክፉ ባርያ እጁን አክርሮ ፊቱን በጥፊ መታው፤ ሠራዊተ መላእክት እየፈሩ በፊቱ ለሚሰግዱለት ለእርሱ እያፌዙ በፊቱ ተንበረከኩ::
  እንዲህ ያለ ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው?
  እንዲህ ያለ ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው?
  ይህን ያህል አርምሞስ እንደምን ያለ አርምሞ ነው?
  ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው?
  ይህን ያህል ሰውን መውደድስ እንደምን ያለ ፍቅር ነው ?
  ፍቅር ለወልድ ከመንበሩ ሳበው፤ እስከ ሞትም ድረስም አደረሰው፡፡
  ኃጢአት የሌለበት ጌታን “ኃጢአተኛ ነህ” ብለው ሰቀሉት፡፡
  ሕይወትን የሚሰጥ እርሱ ከወንበዴዎች ጋር ሰቀሉት፡፡
  አቤት! አዳምን የፈጠሩ እጆች በችንካር ተቸነከሩ፡፡
  በገነት የተመላለሱት እግሮች በሚስማር በመስቀል ላይ ተቸነከሩ፡፡
  በአዳም ላይ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ያለች አፍ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ ሆምጣጤ ጠጣች፡፡
  አቤት! የጌታን መከራ ሊናገር የሚችል ምን አፍ ነው? ምንስ ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የተወደደውን የወልድ መከራ ሲነገር ልብ በሐዘን ይከፈላል፤ ናላ ይዞራል፤ ነፍስ ትርዳለች ትንቀጠቀትማለች፤ ሥጋም ትደክማለች፡፡
  ሞት የማገባው እርሱ ሞተ!
  ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ!
  ሙታንን ያድን ዘንድ ሞተ!

  (ምንጭ፡ ቅዳሴ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)ኝ ሰዓት ድረስ ፀሐይ ብርሃኗን እንዳትሰጥ አደረጋት፡፡ እነርሱ ግን ይህን አይተውም ከማመን ዘገዩ፡፡” ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 7. ኢየሱስ” የሚለውን ስም ----- ይከለክሉት ዘንድ፣ ይሸሽጉት ዘንድ፣ ስሙም እንዳይነገር፣ በስሙም እንዳይሰበክ ይደክሙ የነበሩ በዘመናት ሁሉ ብዙ የሐይማኖት አክራሪዎች ተነስተዋል፡፡ የቱንም ያህል ይሸሽጉት ይደበቁት ዘንድ ቢሞክሩም እንኳ ስሙ አሁን ድረስ በሐይልና በስልጣን በእውነት ሁሉ ሲጠራ አለ!!! ስለእውነት ሳይሆን ስለባህል ስለወጋቸውና ስለአስተምሮህቸው ዘብ የሚቆሙ አክራሪዎች----- ኢየሱስ የሚለውን ስም የሚቃወሙት ለምን ይሆን???
  የስሙ ስያሜና ትርጓሜ፡- መላኩ ገብረኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ በተላከ ጊዜ ለማርያም እጮኛ ለነበረው ለዮሴፍ ስለሚወለደው ህጻን እንድህ አለው “ሕዝቡን ከኃጢያተቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” ማቴ1፡-21 ሕዝቡን ከኃጢያታቸው የሚያድናቸቀው ስለሆነ ስሙ ኢየሱስ ተባለ፡፡ ሲጀመር ገና ከጅምሩ ኢየሱስ የሚለው ስም አዳኝና መድሐኒት ነው፡፡ አዳኛነቱና መድሃኒትነቱም በወንጌል፡ በሐዋሪያት ሕይወት፡ ዛሬም ስሙን አምነን የእግዚአብሔ ልጆች በሆንን ሁሉ እንዳየነው ከኃጢያት፣ ከዲያብሎስ፣ ከህግ እርግማን፣ ከዘላለም ሞት፣ ከደዌና ከበሽታ፤ ከልዩልዩ ጉስቁልና…. ወዘተ ነው!!! ታድያ ይሸሽጉት ይደብቁት ዘንድ ለምን ይናፍቃሉ አክራሪዎቹ???
  በስሙ ያገኘነው በረከት፡- ኢየሱስ የሚለውን ስም አምነንና ተቀብለን የሕያው የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል ዮሐ1፡-12 “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው” አሜን!!! እኛ “ኢየሱስ” የሚለውን ስም ተቀብለንና አምነን ወደ እግዚአብሔር አባታችን አባ አባ እያልን እንጮህ ዘንድ በቃን ሮሜ8፡-15፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ በዮሐ16፡-23 “እውነት እውነት እላእኃለሁ፡- አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኃል” ሐዋሪያው በቁላ3፡-17 “በቃልም ቢሆን ወይም በስራ የምታድርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት” ብሎናል፡፡ እንግዲህ የአዳኝ የኢየሱስ ስም ያልተጠራ የማን ስም ይጠራ??? የሐይማኖት ጥገኞቹ ግን ይቃወሙታል ለምን???
  የስሙ ኃይልና ስልጣን፡- በሉቃ10፡-1 ላይ ኢየሱስ ለወንጌል አገልግሎት ሁለት ሁለት እያደረገ የላካቸው ሌሎቹ ሰባዎቹ ከአገልግሎታቸው ተመልስ ስለሆነው ነገር ለኢየሱስ ሲነግሩት “ጌታ ሆይ አጋንትስ እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት” ሉቃ10፡-17 ሰባዎቹ እንደመሰከሩት አጋንት እንዴት ተገዙላቸው እንዴትስ ተንበረከከላቸው የኃይሉ ምንጭ ምንድን ነው ብለን ስንጠይቅ “አጋንትስ እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል” ነው ያሉት፡፡ ኢየሱስም በዮሐ15፡-5 “ያለኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” እንዳለ ከዚህ ታላቅና ገናና ኢየሱስ ከሚለው ስም ውጭ በራሳቸው ከራሳቸው አንዳች እንዳማያደሩጉ ሊያደርጉም ከቶ እንደማይችሉ ግልጽ አድርጎታል እነርሱም ይህን ሐቅ መስክረዋል፡፡ በማር16፡-17 ላይ ”ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ የሚገድል ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እርሱም ይፈወሳሉ” በማለት ኢየሱስ የሰጣቸው ለ12ቱ ሐዋሪያቶች ብቻ እንዳይደለ ነገር ግን ከሐዋሪያት በኃላ፣ ዛሬም፣ ነገም በስሙ ለሚያምኑት ሁሉ የስሙ ኃይልና ስልጣን እንደሚሰራባቸው ነው፡፡ ወረድ ብሎም በማር16 ቁጥር 20 ላይ “እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፡፡ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሰራ ነበር፡፡ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር” ከዚህ ቃል እንደምንረዳው፡- ከሐዋሪያቱ ጋር ይሰራ የነበረው እርሱ እራሱ ኡየሱስ እንደሆነና፤ በተናገራቸውም ምልክቶች ሁሉ እየተከተለ ቃሉን ያጸናው እርሱ እራሱ ኢየሱስ እንደነበር ነው!!! ኢየሱስ በስሙ የሚያደርጉት አግልግሎት ብቻ አልሰጠም፡- በማቴ10፡-22 “በሁሉም ስለስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” ማቴ24፡-9 “ስለ ስሜ በአህዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” ስለስሙ የሚቀበሉትን መከራ፣ መጠላት፣ መሰደድ አመልክቷቸዋል፡፡ ሐዋሪያቶችም በስሙ ወንጌልን ሰብከዋል፣ በስሙ አጋንትን አውጠዋል፣ በስሙ ብዙ ታምራትን አድርገዋል፣ ስለ ስሙ ተነቅፈዋል፣ ስለ ስሙ ተሰደዋል፤ ስለ ስሙ መከናን ተቀብለዋል፣ በስሙም ከተቀበሉት መከራ ሁሉ እያመለጡ ምርኮን በዝብዘዋል!!!
  የአዳኙን የኢየሱስ ስም እንዳይጠራ ይተጉ ይቃወሙ የነበሩት የዘመኑ የሐይማኖት ጥገኞች አክራሪ አይሁዳውያን “ኢየሱስ” ስለሚለው ስም እንዲህ አሉ ሐዋ4፡-17 “…በዝህ ስም እንዳይናገሩ እንዳያስተምሩ እየዛትን እንዘዛቸው ብለው እርስ በእርሳቸው ተማከሩ፡፡ ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩ እንዳያስተምሩ አዘዧቸው” ተመልከቱ እንግዲህ የአክራሪዎቹ ምናሉ እንደውም “…እንሸሽገው ዘንድ አንችልም” ነበር ያሉት ነገር ግን እየዛቱ በስሙ እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው፡፡ ጠላት ስሙን ይሸሽገው ይደብቀው ዘንድ እንዳማይችል ያውቃል ግን በአገኛቸው ምርኮኞቹ በቀንበሩ ስር በሚያስተዳድራቸው የሐይማኖት አክራሪዎች ይቃወማል፡፡ በሐዋ5፡-16 ላይ “ድውያንና በርኩሳን መናፍስት የተሰቃዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎችን ይሰበስቡ ነበር ሁሉም ይፈወስ ነበር” ይላል፡፡ ኢየሱስ በሚለው ስሙ ያለውን ፈውስና መድሓኒትነት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ሰይጣን የኢየሱስ ስም እንዳይጠራ በአክራሪዎች ጀርባ ብዙ ትግልን ታግሎአል፡፡ ጠላት የታገለውን ሁሉ በልጆቹ ቢታገል እንኳ በኢየሱስ ስም ወንጌል እስከ ዓለም ዳር ተሰበከ፤ ብዙዎች ከስራታቸው ተፈቱ፤ ብርሃን በጨለማ ለነበረው ሕዝብም በራ፤ በስሙ ያመኑ ሕይወትን ተቀዳጁ የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ፤ በአጋንትም ቀንበር ስር የነበሩ ብዙ ሰዎች በስሙ ነጻ ወጠው አምነው ስለስሙ ዘመሩ….. አሜን!!! ሰይጣን በዚህ ተጋድሎው የሚጠቀምባቸው የሐይማኖት አክራሪዎች በዚህ ዘመን ያሉ እነርሱ ኢየሱስን እንደሚያሳዱት፣ እንደሚሰቅሉት፣ እንደሚገድሉት አያውቁም፡፡ ለአክራሪ የሐይማኖት ጥገኞች መልዕክት የጌታ ቃል አለው፡- ኢየሱስ ስትቃወሙት--- አዳኝነቱን የሚያምኑ ምርኮኞች እንደሚበዙ፤ ስትገድሉት--- እንደሚነሳ፤ ስሙ እንዳይጠራ ስታምጹ--- ስሙ በዓለም ዳር እስከዳር እንዲሚነገር እወቁ!!!
  አክራሪ አይሁዳውያን ከአዳኙ ከኢየሱስ ይልቅ የዲያብሎስ ግብር ያለበትን ነፍሰ ገዳዩን፤ ከተማ አማሹን በርባንን ነው የመረጡት፡፡ አይሁዳውያን በውሸት ከኢየሱስ ይልቅ በርባንን የመረጡት በቅናት ተነሳስተው ነው ሉቃ23፡-18-19፤ ማቴ 27፡-15፤ ማር15፡-6-15 ፡፡ ዛሬም ለባህላቸው ቅናት የበላቸው፤ ለወገቸው የቆሞ፤ ለሐይማኖታቸው ሲሉ ወንጌል የቀለለባቸው ከአዳኙ ኢየሱስ ይልቅ ነፍሰ ገዳዩን ሲመርጡ ይታያሉ፡፡ ነፍሰ ጋዳዩ በርባን እየዘለለ ወደ ከተማ የገባው ሊዘርፍ ሊቀማ ነፍስም ሊያጠፋ ነው፡፡ እናንተ የሐይማኖት አክራሪዎች የበርባን ወዳጆች የኢየሱስ ተቃዋሚዎች የመረጣችሁትን ማወቅ ያለባችሁ፡- ከኢየሱስ ስም ሌላ የመረጣችሁት እርሱ የሚገላችሁ ዲያብሎስ ነው!!!
  እህቶችና ወንድሞች እናንተ የምትቃወሙት ኢየሱስ የሚለው ስም ለብዙዎች እረፍት መውጣት፤ ከስራታቸው መፈታት፤ ለታሪካቸው መቀየር፤ ለቀንበራቸው መሰበር ምክንያት ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ ዲያብሎስ የሚቃወመው ኢየሱስ የሚለውን ስም ለዚህ ነው፡፡ አሁንም በቤተ ክርስቲያኗ ስር ተጠግተው ያሉ ጥገኞች የዲያብሎስ ትጉ ስራተኞች ስሙን ይቃወሙትል የሚገርመው ግን፤ ኢየሱስ የሚለውን ስም ልብ በተነካ አጠራር የሚጠሩ በየግዜው እየበዙ እንጅ እየጠፉ አልመጡም!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ