ዓርብ ፣24 ሜይ 2013

የ‹‹አጥማቂው› መምህር ግርማ ስራ በቤተክርስቲያን ስርዓት እይታ
(አንድ አድርገን ግንቦት 16 2005 ዓ.ም)፡- መምህር ግርማ የማጥመቅ ስራቸውን ከጀመሩ ዓመታት ማስቆጠራቸው  ይታወቃል ፤ በየሄዱበት ብዙ ተከታይ ከማፍራታቸው በተጨማሪም ብዙ ነቃፊ ፤ ትምህርታቸውም ይሁን የማጥመቅ ስርአታቸው ከቤተክርስቲያን ውጪ ነው የሚሉ ሰዎች አልታጡም ፤ ‹‹አጥማቂው›› በተለይ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሲያካሂዱት የነበረው ተግባር 17 ክፍል ያለው ፊልም ወደ ሲዲ በመለወጥ ለህዝበ ክርስቲያኑ ለገበያ አቅርበዋል፡፡ ምዕመኑ ቤተክርስቲያን ሄዶ ከማስቀደስ ይልቅ የእሳቸውን ሲዲ ከፍቶ ቤቱ ቁጭ ብሎ ‹‹ይገርማል›› እያለ የሚያይበት ጊዜም ነበር ፤ ከሀገር ውጪ ያሉ አብያተክርስቲያናት ‹‹አጥማቂውን›› አምጡልን በማለት የቤተክርስቲያኖቻቸው አስተዳዳሪዎች ያስጨነቁበት ጊዜም ነበር ፤ በአሁኑ ሰዓት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በብዙ ምዕመናን ቤት የ‹አጥማቂው›› ፊልሞች ይገኛሉ፡፡ ከቀናት በፊት የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ካገዳቸው በኋላ ቤተክህነቱ እንዲህ በማለት ድጋፉን ገልጾላቸዋል ‹‹መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ /ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡››
 
ይህ በእንዲህ እያለ የ‹አጥማቂው›› የሲዲ ስራዎች በቤተክርስቲያ እይታ ምን ይመስላሉ ? እውን ትምህርታቸውም ሆነ የአጥምቆት ስርዓታቸው የቤተክርስቲያን ስርዓትን የተከተለ ነውን? ምዕመኑ ለምን አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ በ‹‹አጥማቂው›› አማካኝነት ሊገባ ቻለ? ‹‹መምህር›› ግርማስ ማን ናቸው ? እና በ‹‹አጥማቂው›› ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ባሉበት ግንቦት 20 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በአራት ኪሎ ግቢ ገብርኤል አዳራሽ በምዕመናን ታላቅ መልስ የመስጠት ጉባኤ ተዘጋጅቷል፡፡ በ‹‹አጥማቂው›› ግራ ለገባችሁ ፤ ግራ ለተጋባችሁ ፤ ግራም ያጋባችሁ ሁላችሁም በጉባኤው ላይ ተጋብዛችኋል፡፡

69 አስተያየቶች:

 1. tooooooooooooooooooooooooooo late? 17 cd eskitatem yet nebern? this is sign to indicate how much the the current church leaders are careless for us who follow the religion. this is really amazing.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. መናፍቁ በቤተክርስትያናችን ጉዳይ አንተ እዚህ ምን ትሰራለህ? በባለፉት ሲዲዎች ጉዳቹ ስለተጋለጠ ነው?

   ሰርዝ
 2. እውነት ችግር ካለባቼው የቀድሞው አስተዳዳሪ ለምን አልጠተቃወሟቼውም? አዲሱ አስተዳዳሪ- አንድ ወር እንኹዋን ሳይሞላ ለምን ግጭት ፈጠሩ? እውነት ለ..... ወይስ ለጥቅማቼው? ላይፍ መጽሄት የጥር እትሙን ምን እንዳስነበበን ታውቁ ይሆን ?ወይስ አውቃችሁ ነው በwebsitachu ላይ ያላውታችሁት? ብዙ ጊዜ የላይፍ መጽሄት ስለምጣወጡት ብዬ ነው?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 3. ከሀገር ውጪ ያሉ አብያተክርስቲያናት ‹‹አጥማቂውን›› አምጡልን በማለት የቤተክርስቲያኖቻቸው አስተዳዳሪዎች ያስጨነቁበት ጊዜም ነበር ፤

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 4. ከሀገር ውጪ ያሉ አብያተክርስቲያናት ‹‹አጥማቂውን›› አምጡልን በማለት የቤተክርስቲያኖቻቸው አስተዳዳሪዎች ያስጨነቁበት ጊዜም ነበር ፤

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 5. የመምህር ግርማ ወንድሙ እገዳ በተመለከተ የቀድሞው የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ የሰጡት አስተያየት እና ከ እገዳው ጀርባ ያሉ እውነቶች http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=MX-6v7Y-sMM

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 6. ይህ በመምህር ግርማ በኩል የሚካሄደው ye wongel ena የፈውስ ኣገልግሎት በሰይጣን ሃይል መቆም የለበትም

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 7. ፊልሞች....አዎ ለናንተ ፊልም ነው ለኛ ግን ህይወት ነው ብዙ ህይወታቼው የተበላሼባቼው ሰዎች በርሳቼው አገልግሎትና በግዚአብሄር ማዳን ረፍት አግኝተዋል

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. እውነት ነው ብዙ ነገር ያስተማሩን አባት ናቸው በሀይማኖት እንድንበረታ እንድንፀልይ ,እንድንፆም, እንድንሰግድ, ዲያብሎስን እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን ያስተማሩን አባት እግዚአቢሄር ፀጋውን ያብዛሎት ጠላቶችዎን ከእግርዎ ስር ያድርግሎ አባታችን ።እስኪ እውነት እንነጋገር የትኛው የሃይማኖት አባት ነው እንዲህ እንደሳቸው አድርጎ መእምኑን ያስተማረ ህዝቡን ከባእድ አነምልኮ እንዲርቅ ለፈጣሪው እንዲሰግድ ያደረገ በአሁኑ ዘመን በእውቀት የበለጡዋችሁ እንደሆነ ተሀድሶ, መናፍቅ, መተተኛ እያላቹ መተቸት ስራ አድርጋችሁታል ለቦና ይሰታችሁ።ወንድሜ እንዳልከው ለነሱ ፊልም የሆበውን ለኛ ግን ህይወት አግኝተንበታል ማስተዋሉን ይስጠን አሜን።

   ሰርዝ
  2. እግዚአብርሄር የሚሰሩትን አያውቁም እና ይቅርበላቸው ብሏል ይቅር ይበላችሁ፡፡

   ሰርዝ
 8. why dont you invite memher girma “አፕሪል ዘ ፉል” ይች ነገር “አፕሪል ዘ ፉል” ብጤ መሰለችኝ ቂቂቂ..

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 9. Let me say these to my brother “Mahiber Kidusan”, when it comes to the issues of “Memeher Girma’’ you are 100% dead wrong. What really he did wrong ? you guys don’t have anything to point out except . . Blaa blaa blaa. You guys reminds me of that “Tsehaft Ferisawiyan” how they crucified Lord Jesus Christ with the false allegations. I read your entire allegation but nothing holds a water. You (Mahiber Kidusan) should know better than anybody else, that all the works/miracles done by memeher Girma is from the Almighty God. You (Mahiber Kidusan) I respect you! I admire you! What you have been done for our church in last 20 years, I really appreciate that, how quick you guys expose ‘Menafiqans’ But this time you are wrong and sided with ‘Menafiqan’ to attack Memeher Girma. Because he cast out devil from Menefeqan’s? He heals blind woman? He cast devil from peoples? He exposes the devil works? Please tell me what he did wrong? Instead of fighting a man of God, why don’t you fight the so called ‘Bete kihnet’ who is a cancer to our church growth and brought shameful to the church leader? Please open up your Eyes and see what Memher Girma has been done so far for our church, to me he is a precious man who God gave us during our difficulty time. Please stop degrading and baseless allegation, you will be answering for it one day.

  Thank you.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች

  1. I don't want to say any thing more only BIG THANKYOU

   ሰርዝ
  2. አመሰግናለሁ ላስቀመጥከው እውነት።

   ሰርዝ
 10. ያለ እግዚአብሔር ፀጋና ቸርነት ማንም የሃይማት አባት ቄስ ቢሆን ፓትርያርክ እንደ መምህር ግርማ ወንድሙ በሽተኞችን በእግዚአብሔር ፀጋ የሚፈውስ፣በፀበል ሃይል የሚፈውስ፣በደዌና በቁራኛ ተይዘው ለዘመናት ሲማቅቁ ለኖሩት ሰዎች ፈውሰን በእግዚአብሔር ሃይል የሚሰጡ ወዘተ…. መሆን አይቻልም፡፡መምህር ግርማ እግራቸው ሽባ ሆኖ ለዘመናት ቤታቸውን እንደ እስር ቤት በማድረግ ዕለተ ሞታቸውን የሚጠባበቁትን በእግዚአብሔር ሃይልና ፀጋ ፈውሰዋል፡፡ ይህ ዝም ብሎ የሚወራ አይደለም፡፡ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በመቀሌ የሚኖር አንድ መካኒክ እጁን አጣሞት የነበረው የሰይጣን ደባ በእግዚአብሔር ሃይል ተንዷል፡፡የሃይማኖት አባቶች በራሳቸው ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው በመምህር ግርማ ሲፈወሱ አይተናል፡፡ ምነው በእሳቸው ላይ ቁናው በዛ????እኔ ምንጩ ቅናት ይመስለኛል፡፡እንደ እሳቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው የፈውስ ፀጋ የሌላቸው የሃይማት አባቶች ለምን በለጠን፣ለምን በሽተኞችን ፈወሰ፣ለምን ………ለምን…..ለምን…….እያሉ እንቅልፍ አጥተው የኖሩትን አሁን አዲስ ፓትርያርክ ሲመረጡ ጊዜ ጠብቀው ተገበሩት፤አገዷቸው፡፡ ግን አሁንም በእግዚአብሔ ስ ስለሆነ መከራ የደረሰባቸው እግዚአብሔር መከራቸውን ያቀልላቸዋል፡፡ አርቃችሁ ብታስቡ ደህና ነው….እግዚአብሔር የማይወደውን አታድርጉ…….

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 11. እንዲህ፡ዓይነቱን፡ልብ፡ወለድ፡ታሪክ፡ለሆሊውድ፡ብትሸጡት፡ይሻላል፡እንጂ፡እኛን፡የተዋህዶ፡ልጆች፡ግን፡ልታወናብዱን፡አትችሉም፡፡በናንተ፡ከንቱ፡ወሬ፡ለሚነዳው፡ህዝብ፡ግን፡አዝናለሁ፡፡ያልበደለውን፡ከምታሳድዱ፡ለፕፕስና፡የማይመጥነውን፡አፀያፊ፡ስራ፡የሚሰሩትን፡ቤተ፡ክህነት፡ግቢ፡ውስጥ፡የተሰገሰጉትን፡መነኮስ፡ተባዮቹን፡ለማስተካከል፡ሞክሩ፡፡አባታችንን፡ጽናቱን፡ይስጥዎ፡april the fool....april the fool

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. "april the fool....april the fool" በየትኛው፡አገር፡እንተርጉምው፡፡ከኢትዮጵያዊነት፡ጋራ፡ግን፡ግንኙነት፡የለውም፡፡ በሃይማኖት፡ቀልድ፡የለም፡፡እስካሁን፡በጠበጣችሁ፡ስለተፈቀደላችሁ፡መብታችሁ፡እንዳይመስላችሁ፡፡

   ሰርዝ
 12. Who are insulting the work of the Holy Spirit! Ena yenante debteroch yemiserut new tikikilu. Long ago. Memehir has been doing this for 15 years millions could survive from your curse because of him! Lemin yemitayuting lemamen embi tilalachihu. Yemiamin ene yemadergewun yadergal. Besime aganintin tawetalachihu, liyuliyu beshitawochinim tifewusalachew new yemilew. Who really is in the orthodox church today doing that except Memehir and some few at distance places (monasteries and few more). Who are so called Sunday school? Do you think fakes can be true when you shout if so loud. You and like you hooligan intruders named them selves as ‘kahin’ and Sunday school attendees who really are you after to be against the Holly Spirit. Thanks to Memehir who save the generation by exposing your hidden curses and showing us the power of God. Betemeqdesu yante debteran tenqoawoch mefencha hono lezemenat yetesekayenibet yibekal zare teneqaqtenal. Man min endehone hulum siltereda Ezih yemititefawn lerasih wat adrigeh mesheshegiyahin felig. Qenona, fitihan negest minamin, yematawqewun atzelabid. Wey anbib wey teyiq, wey zim bel. What memehir is doing is nothing out of the Qenona. Bihon enkuan, enezih hulu yese enji yeliul amlak higoch meseluh ende? Gin min ayne aemiro yalachihu nachihu ewunetin lalemamen yihenin yahil tigil. ‘Egziabiherin lemawek balfelegut meten yemayigebawun yadergu zend lemayireba aemiro asalifo setachew’. Lemanignawum atichekul, Memehirin yante aynet werobeloch bemifenchubet bota yetsafutin tsafu enji endih bekelalu yemiqerilachew ayemselih! Today, the work of Memehir Girma puts all the religions and flowers under question? Endantena yanten ayenet betekristianin, yetesegesgubat ergimanoch enji, talalak abatoch kememehir Girma gar endalu astewul. መምህር አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቀሚ የሆነው፡፡ አኛ ራሳችን የሚካሄደውን የፈወስና ወንጌል አገልግሎት በአይናችን ስላየን በጆሮአችን ስለሰማን እንጂ፡፡ እሳቸው ከሁላቸው በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው እኔ አገልጋዩ ነኝ ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 13. የመምህር ግርማ የፀሎታቸው በረከት ለእኛም ይድረሰን!!
  መንፈሳዊ ወንድሞቼ እህቶቼ አስተውሉ …..>” መንፈሳዊ እገዳ እኛ የምናውቀው በእግዚአብሔር ስም ነበር ደሞም በፀሎት ፈቃደ እግዚአብሔር ተጠይቆ ሲገለፅ ብቻ ነበር “ :: ይህ የእገዳ ወረቀት ግን አንድም “የልኡል እግዚአብሔር ክቡር ስሙ” የለውም ስለዚህ ምን ትገነዘባላቹህ??? እኔስ እንደምገነዘበው የቢሮ ለፖሊስ እንዲያግዛቸው የተፀፈ ወረቀት እንጂ ሟፋጨትና ማንጎራጎር የለመደ ይህችን ዲያብሎስንና ልጆቹን የምታረካ ወረቀት ይዘህ ኡኡኡ በል ! እኛ ግን ማስተዋል ጀምረናል መንፈሳዊ ወንድሞቼ እህቶቼ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ታማኝ ልጆች ነቅተናል :: ጌታም በሉኡል ቃሉ እንዲህ ብሎናል :-
  (ፊሊጽሲዮስ 1፥ 28-29” በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ”፤)
  አሁንም ዲያብሎስና ልጆቹ ይህ አይነት ማእበል ቢያነሱም አንታወክም ባይሆን ቤተክርስቲያናችንና ሀይማኖታችንን አታውኩብን ህዝበ ክርስትያኑን በጥርጣሬ አታውኩብን ይህን የዲያብሎስ ቅናት አውጡልን አውጡልን አውጡልን “ልኡል እግዚአብሔር የሌለበት አመክሮ እንቅስቃሴችሁን አውጡልን የሌሎችን በክብር ያሉ አባቶቻችንን እናቶቻችን ወንድሞቻችን እህቶቻችንን ስም የዚህ አይነት ቅሌት እያመጣቹሁ ህዝበ ክርስቲያኑን በጥርጣሬ አታውኩብን
  (ፊሊጽሲዮስ 1፥ 28-29 “ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤ “)
  ለዚያውም ትልቅ ክብር ለአባታችን ለመምህር ግርማ ስለሚያመጣልን ደስ ይበለን!!
  አትፍሩ ከዲያብሎስ ጋር በክፉ ምኞታቸውና አላማቸው የመንፈስ ቅዱስን ስራ ለሚቃወሙን በሙሉ ፊት አንሰጥም ልኡል እግዚአብሔር ይቆጣልቸው አሜን

  የጠመሙትንም ልኡል እግዚአብሔር የልባቸውን ድንጋይ ይናድላቸው!! እኛ ማረግ ያለብን ለበጎ አባታችን ሁሌ መምህር ግርማን በፀሎት እናስብ!!

  እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶ አብዝቶ ለመምህር ግርማ ይስጥልኝ/ ይስጥልን!!! እኛንም ይባርከን!
  ልኡል እግዚአብሔር ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 14. ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፓትሪአርክ)
  እውነት ከሕሊና ፍርድም በላይ እንደሆነች እረዳለሁ፡፡

  ብዙዎች በህሊናቸው ትክክል ሆነው እውነትን ግን ስተዋታልና፡፡ በትክክል አባባሌን ይገልጽ እንደሆነ አላውቅም ግን የሳዖል ኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ ያንን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ እሱ አስቀድሞ ስላወቀው/ስለተማረው ነገር ብቻ የክርስቲያኖች አሳዳጅ ነበርና፡፡ ሳዖል ግን ስለህሊናው ትክክል ነበር ምንም እውነትን ባያገኛትም፡፡ በአንጻሩ ሌሎችን ጨምሮ ራሱ አስተማረኝ የሚለው ገማልያ ሳይቀር እውነትን ቢያውቋትም ሊመሰክሩላት አልፈለጉም ወይም ፈርተው ክደዋታል፡፡ ከህሊና ፍርድ ወጥተዋል፡፡ እኔን እንደሚገባኝ ሕሊናችንን ካልካድን እግዚአብሔር እውነትን ለማወቅ ከፈለግን ይገልጥልናል፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ የተደረገለት ይሄው ይመስለኛል፡፡ የእኛ አቅም ስለሕሊናችን መኖር ነው፡፡ እውነትን ለማወቅ የእግዚአብሔር እገዛ ያስፈልጋል፡፡ እውነትን ግን መናፈቅ ያስፈልገናል፡፡ እውነት እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ደግሞ አብዝተን መፈለግን ይጠበቅብናል፡፡ ማለትም ለሕሊናችን ማደርን፤ ፍጹማን አለመሆናችንን አወቀን ያላወቅንውን ለማወቅ መትጋትን፡፡ በተቃራኒው እግዚአበሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ይላልና፡፡ አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠን ምን ዋጋ አለን?! የማይረባ አእምሮ/ሕሊና ያጣ/ ከባድ ነው!
  የሕሊና ፍረድና የእውነትን መፈለግ/መናፈቅ ለሰው ሁሉ የሚያሰፈልግ ሲሆን በመሪነት ያሉ ሰዎች፣ዳኞች፣ በተለይም ደግሞ የኀይማኖት አባቶች እጅግ የሚጠበቅባቸው ነው፡፡ እነሱ ስለቢዙዎች ይኖራሉና፡፡ በአንዱ የሐማኖት አባት መውደቅ ምክንያት ብዙዎች ሊወድቁ ይችላሉና፡፡ ሥለትሷ የሕሊና ፍርድ ማጓደል ከመኖር በስጋ ቢሞቱ ይሻላቸዋል፤ ስለብዙዎች ሕያዋን ናቸውና፡፡ ይህንን ብዙ የሀይማኖት አባቶች አደርገውት አልፈው ዛሬ ደርሰናል፡፡ አሁን አሁን በሀይማኖት መሪዎች የሚታየው ግን እኛ ተራዎቹ እንኳን የማንደፍረው ከሕሊና የራቀ ድርጊት (ድፍረት ብለው ይመቸኝ ነበር) ነው፡፡ እርሶ በሚመሯት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ሕሊናን የሚያከሱ፣ ምዕመናንን የሚገፉና፣ እንዲህስ ከሆነ ቢቀር ይሻላል በሚል ሕዝቡን ከአምልኮተ እግዚአበሔር እያራቁ የሚገኙ በቤተክርስቲያኗ በመሪነት ቦታ ያሉ ሰዎች የሚፈጽሟቸው ብዙ ድርጊቶች አሉ፡፡ አባ ይህንን ሁሉ የምነግርዎት እርሶን ለማስረዳት አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ ያቁታልና፡፡ ጽሑፌ ለተነሳበት ሀሳብ መንደርደሪያ ይሆነኝ ዘንድ እነጂ፡፡
  ቀደም ብለው ሰዎች ብዙ ስላሉባቸው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጸሙ ግደፈቶች ብዙም ስለማላውቅ እኔ አስተያየት ሰጥቼም አላውቅም፡፡ አንዳንዶቹም ሰዎች ስለተሳሳቱ የሚያወሯቻ እንጂ እውነት ሆነዋል ብዬ ለማመን እቸገርባቸው ስለነበርም፡፡ ሰሞኑን ግን እኔው የማውቀው አንድ እኛ ተራዎቹ የማናደርገው የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችና ደብር አስተዳዳሪ ሆነው በተሾሙ ሰው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አንድ ድርጊት ተፈጽሞ ይሄው ሕዝቡን እያነጋገረ ይጋኛል፡፡ እንደውም ይሕንንው ድርጊት በመደገፍ ከእርሶ ጽ/ቤት ተፈርሞ የወጣውም ደብዳቤም አለ፡፡ ደግነቱ እርሶ አይደሉም የፈረሙት! ይመስለኛ ጉዳዩንም ሰምተውታል፡፡ ይሄውም በደብሩ (ቅ. እስጢፋኖስ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ወንጌል ያስተምሩና በተሰጣቸውም ፀጋ ሰዎችን በርኩሳን መናፍስት ከሚመጡ ልዩልዩ ደዌያትና ሌሎች ውስብስብ የኑሮ ችግሮች ይታደጉ ስለነበሩት መምህር (መልአከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ጉዳይ ነው፡፡ አባ መምህር ግርማ በደብሩ ቅጥር ግቢ እየሰጡ የነበሩትን አገልግሎት ማገድ ሥልጣንና ጉልበት እስካለ ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡ ለቤተክርስቲያንም እውን ከመቅናት የተነሳ ድርጊት ከሆነም ሕሊና ስላሰበው ተደርጓልና ከክፋት አይቆጠርም የቱንም ያህል እውነትን ካለመረዳት ስህተት አንኳን ቢሆን፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ግን ሕሊናንም እውነትንም በመካድ ስለሚመስል አደገኛ ድፍረት ነው በዬ አምናለሁ፡፡ ሒደቱ ሁሉ ውስብስብ ተንኮለኝነት የተቀመሙበት ይመስላልና፡፡ መምህር ግርማን ይሁን እግዚአብሔርን እየተዳፈሩ ያሉት ማንን እንደሆነ ሁላችንንም ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጉዳይ ነበርና፡፡ መምህር ግርማን ስለነኩ ማለቴ አይደለም፡፡ የወንጌል ማስተማሪያ መድረክ አፈረሱ፣ ቅዱሳን ስዕላት ቀደዱ፣ ሌሎችንም ሥጋዊ ኃይልና ሥልጣን የሚችሏቸውን ድርጊቶች ፈፀሙ፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ የሆነው በሰሞነ ሕማማት፣ የክርስቶስ ሕማም በሚታሰብበት ሳምንት መሆኑ ያሳዝናል/ያስገርማልም፡፡ እንዲህ ያለውን ድርጊት ለእኛ ስታስተምሩን ሐጥያት ነው በተለይ ደግሞ በሰሞነ ሕማማት፡፡ የቤተክርስቲያን ሰዎች ነን የሚሉት ግን ሲያደርጉትስ? እውን ስህተትስ ቢኖር እንዲህ ባለ ከመንፈሳዊ ባህሪ በወጣና በጀብደኝነት በሚደረግ ግርግር ለሕዝብ ማስተዋልን በማይሰጥ ሁኔታ ስህተትን ማረም ይቻላል? ደግሞስ ካልጠፋ ጊዜ ያ ጊዜ ለምን ተመረጠ? ....

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 15. .... የሕሊና ጉዳይ ከሆነ እሳቸው ባሉበትስ አይቻልም ነበር? በዚያውም ስህትቱን ተናግሮ ሕዝብንም አሳምኖ? እንኳንስ ለዘመናት ያስተማሩትን መምህር ግርማን ይቅርና በአንድ ጉባዔ የተከሰተ ሕዝብን የሚያሳስት ነገር ከሆነ በተቻለ መጠን ስህተት በፈመው ፊት ስህተቱን ተናግሮ ማረም ይጠበቃል፡፡ አባ ሁሉንም ነገር አርሶ ያዎቁታል ማለቴ ሥርዓቱን ሁሉ፡፡ መምህር ግርማ እየተከሰሱበት ያለውን ሁሉ፡፡
  የተፃፉትን ደብዳቤዎች ስናነብ ግን ማን በምን አስተሳሰብ ደረጃ እንዳለ ስለነገሩን በሕዝብ ዘንድ የፈጠሩት ትዝብትን እንጂ የመምህሩን ስህተት አይደለም፡፡ የደብዳቤዎቹ ቅደም ተከተል፣ይዘትና የቃላት አጠቃቀም ከመውረዱ ጋር ተዳምሮ፡፡ በተለይ ደግሞ ከእርሶ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ ሲጀምር ደብዳቤው ላልተጠየቀበት ጉዳይ ነው የተፃፈው፤ ከተጻፈም ሥርዓትና አግባብ ባላቸው ቃላቶች ቢሆን መልካም ነበር፡፡ ደብዳቤው ጉዳዩችን በስርዓቱ ከማበራራት ይልቅ በስደብ የተጨቀ ነበር፡፡ ሕገ-ወጥ፣ ሥርዐተ-አልበኛና የመሳሰሉት ቃላቶች እውን ከእገዳው ጋር በተያያዘ ሊያውም ከቤተክርስቲያን አስፈላጊ ናቸው? ኋላ በሕግም እኮ ሊያስጠይቁ ይችላሉ፡፡ ግን ሲጀመር በ28/08/2005 በደብሩ አስተዳዳሪ የተጻፋ ደብዳቤ የመምህር ግርማን ማገድ ወስኖ ለእርሶ ጽ/ቤት በግልባጭ አሳወቀ እንጂ እገዳውን እንዲያጸናለት አልጠየቀም፡፡ እና ላልተጠየቀበት ጽ/ቤቱ አፅድቄአለሁ ማለት አለበት? በግልባጭም ቢደርሰው የእርሶ ጽ/ቤት ደብዳቤ ለደብሩ የሚፅፍበት ሁኔታ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ኃላፊነት ስላለበት ግልባጭ የተደረገለት ጉዳይ ስህተት ሆኖ ቢገኝ ለማረም፡፡ ይባስ ብሎ ስንት አመት ሲያስተምሩ ምንም ሳይባሉ ይሄው የእርሶ ጽ/ቤት ደብዳቤ በአሰቸኳይ ከሚል ልዩ ማሳሰቢያ ጋር ነው የተጻፈው፡፡ አባ እንዲህ አይነቱ ነገር ውስጥ የተሸረበ ሴራን ለሕዝብ እያሳበቀ እንደሆነ ጸሐፊዎቹ ቢረዱት እንዴት ጥሩ ነበር፡፡
  ደብዳቤዎቹ በየኢነተርኔቱ ስለተበተኑ ሕዝብ እያቸው ስለሆነ ሌሎች ጉዳዮቹን አላነሳም፡፡ ከደብዳቤዎቹ በተጭማሪም የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አጥንቼ አግኝቼዋለሁ የሚለውንም የመምህር ግርማን ክስ በየኢነተርኔቱ አስነብቦናል፡፡ የሚያሳዝነው ግን አሁንም ጥናት ብለው ባቀረቡት ጽሑፍ የተጠቀሟቸው ቃላቶች በጣም ከግበረ-ገብነት የወጡ መሆናቸው ነው፡፡ ጥናት የመረጃ አቀራረቡ እንዴት እንደሆነ ቢጠይቁ እንሱንም ከትዝብት ያድናቸው ነበር፡፡ አንድ የጥናት ሰነድ ሲቀርብ መጠቀም ያለበት መደበኛ ቃላቶችን እንጂ አንባቢን በሚያስደንቡሩ ስድቦችና አስነዋሪ ቃላቶች ታጅቦ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ አጠኚው ሲጽፍ እራሱን ገለልተኛ አድርጎ በአገኘው ውጤት ላይ ብቻ ተመሥርቶ እንጂ የራሱን ስሜት አጠናሁት በሚለው ጉዳይ ቢያስነብብ ልብወለድ እንኳን ለመሆን አይበቃም ምንአልባት አሉባልታ ከሆነ እንጂ፡፡ ልብወለድም የብዙ ማሕበራዊና ነባራዊ ጉዳዮችን ጥልቅ ግንዛቤ ይጠይቃልና፡፡ በዚህ አጋጣሚ እነዚህ ሰዎች ያደረጉት ለሕዝብ ማንነታቸውን ማሳወቅን እንጂ የጥናታቸውን ማረጋገጫ በመተንተን ጭብጥን ማሳወቅ አይደለም፡፡ ከጥላቻ፣ ከቅናት፣ ከአደመኝነት፣ ከበቀልና ከመሳሰሉት የክፋት በሕሪያት በተወረሱ ቃላቶች የጥናትን ውጤት መዘገብ ከንቱ ነው፡፡ ድርጊቱ አንኳን እነሱ እንደሚሉት ቢሆን እውነታንም የጨልማልና፡፡..

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 16. አጥኚ ነን ያሉት ግን ሁከት በሆኑ ቃላቶች እውነት ነው ብለው ሊያሳምኑን የሞከሯቸው ጉዳዮች አንዳቸውም እውነት አለመሆናቸው ነው፡፡ አሁንም ሙሉ ጥናት የተባለውን ከኢነትረኔት ሊነበብ ይችላል ግን አለፍ አለፍ እያልኩ አንዳንድ ጉዳዮችን ለማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ መምህር ግርማ ቢያንስ ካህን ናቸው ከዚህም በላይ ቤተክርስቲያኗ በሰጠቻቸው ማዕረግ በተለምዶ መምህር ግርማ ብንላቸውም መላከ መንክራት ተብለው ተሰየመዋል፡፡ በዚህም ላይ በእድሜያቸው ብቻ እንኳን አንቱ መባል አያንስባቸውም፡፡ ትልቅን ሰው አንተ እያለኩ ባቀል ራሴን ማቅለሌን ማወቅ አለብኝ፡፡ የቤተክርስቲያን ነን የሚሉ ደግሞ ከዚህም በላይ በሆኑ አክበሮቶች ሰዎችን ቢጠሩ መልካም ነው፡፡ ጉዳያቸውንም በትክክሉ ለማስተላለፍ ይረዳ ነበርና፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፡፡ አጥማቂ ነኝ ፈዋሽ ነኝ ባይ ይላል፡፡ እሳቸው ስላሉ ነው ወይስ ሕዝብ ራሱ ስላየ? መምህር ግርማ አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቀሚ የሆነው፡፡ መምህር ግርማ ከብዙዎች በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው! እኔ አገልጋዩ ነኝ (ሁሌም የሚሉት ነው)! ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡
  ለመምህር ግርማ በትክክልም የማዳን ፀጋ እንደተሰጣቸው ሕዝብ በትክክል በተግባር አየ እንጂ በወሬ እንኳን የሰማው ብቻ አይደለም፡፡ ለምን ሕሊናችንን እንምንክድ አልገባኝም፡፡ አይነስውር አላየም?ሽባዎችና አንካሶች አልሮጡም? ሌሎች በሕክምና ተስፋ የተቆረጠባቸው በሽተኞች አልዳኑም? ይህ እውነት አይደለም? ብዙዎቻችንን ለዘመናት የእግዚአበሔርን ሀልዎት እንኳን ረስተን የነበርነውን ኃይሉን በገሃድ አሳይተውን ሳንወድ በግዳችንም ቢሆን እንድናምን አድርግዋል፡፡ ከሌላ እምነት ሳይቀር! ይህ እውነት አይደለም? አኛ አኮ ለዘመናት የተደናገርን ሰዎች ነን? ይህ በእሳቸው እየተካሄደ ያለው ሐዋሪያዊ አይደለም? አባ እርሶ ራስዎ እንዲነግሩን እንፈልጋለን? እውን አሳቸው የሚሰሩት የጥንቆላ ሥራ ነው? ለነገሩ እንደኔ ላለነው የተኛውም ኃይል ይሁን እንዲህ ያለ ነገር እንዳለ ማወቁ ብቻ በቂ ነው፡፡ ምንም አናውቅም ነበርና! የእግዚአበሔር መኖር እነኳን በአፋችን እንጂ በልባችን ወደ ክህደት የተጠጋው ጥርጣሬው ነበረብንና፡፡ ሰይጣን የሚባለው በእኔና መሰሎች ዘንድ ከነጭረሱም የሌለ ነገር እንደሆነ ልባችንን ሞልተን የምንናገረው ነበር፡፡ እግዚአብሔርንም እኮ እንደው ስለፈራን (ምን አለባት ካለ በሚል) እንጂ እንዳለ ስላመነው አልነበረም፡፡ ይሄንን ሁሉ በመምህር ግርማ ምክንያት በገሃድ አይተን እንድናምን ተገደናል፡፡ ከዚህ በኋላ ምርጫችንን ማስተካከል የየራሳችን ነው፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 17. አባ እውን ልንቃወመው የሚችል አንድ ስህተት እንኳን ተሰርቷል?ሰዎችንስ እያዳኑ ያሉት በእግዚአበሔርና በቅዱሳኑ ስም አይደለም? መቁጠሪያውስ አርሶ ሳይቀሩ አባቶቻችን የምትይዙት አይደለም? በዲቁናስ ማዕረግ ሆነው ያጠምቁ የነበረው እውን ስሕተት ነው? እግዚአበሔር ከፈቀደ ደግሞ ከልካዩ ማን ነው?! እንኳንስ የዲቁና ስልጣን የነበራቸውን መምህር ግርማን ይቅርና የእግዚአበሔር ፈቃድ በሌላ ክህነት ከነጭርሱ በሌለው ሰውስ ቢሆን ማን ሊያግደው ይችላል? ረጋሚው በለአም እኮ ነው የክርስቶስን መምጣት ከዘመናት በፊት ያስተዋለው! ክርስቶስን አሳዳጁ ሳኦል እኮ ነው የክርስቶስ ድንቅ ሐዋሪያ የሆነው! ሽፍታው አኮ ነው ገነት በመግባት ቀዳሚ የሆነው! በተቃራኒው ስርዐት አለን የሚሉት ካህናት እኮ ናቸው ክርስቶስን የሰቀሉት፣ ደቀመዘሙሩ የነበረ ይሁዳ እኮ ነው ጌታን አሳልፎ የሰጠ፡፡ ሰዎች ስርዐትንና ቀኖናን እነሱ በሚመቻቸው እየተረጎሙ መጠቀሚያ ካደረጉትስ? እንደምረዳው መምህሩ ከጅምሩ በዲቁናቸው ዘምን ያጠምቁ የነበሩት የተሰጣቸውን ጸጋ (ካልተጠቀሙበት ዕዳ ነውና) ተጠቅመው ወገናቸውን ለመርዳት እንጂ እኔ አጥማቂ ልሁን ብለው እንዳልሆነ ያለፉባቸው ታሪኮች ምስክሮች ይሆኗቸዋል፡፡ ደግሞስ የቅስናውን ማዕረግ ሰጥቶ አገልግሎታቸውን ማጽናት የቤተክርስቲያኗስ ኃላፊነት አይደለም? ይህስ ከባድ ጉዳይ ነበር ዲቁናው እስካላቸው ድረስ? ነው ማውገዝ ተቀዳሚውና ቀላሉ ስለሆነ? አንዳች ከበጎ የወጣ ሥራ እንኳን ሰርተው ቢሆን እሺ ግን አኮ ለዘመናት ስቃይ ውስጥ የነበሩ በሽተኞችን፣ ችግረኞችን ለመታደግ ነው ፀጋቻን የተጠቀሙበት? አባ ለእንደኔ ያለው ብዙ የማይገቡኝ ነገሮች በቤተክርስትያን ቢኖሩም በጎ ነገርን የሚቃወም ሁሉ ግን ከእግዚአበሔር እንዳልሆነ አውቃሉሁ፡፡ እኔ ብቻም ሳልሆን ጤነኛ አእምሮ ያለው ሁሉ ያውቃል፡፡
  የመምህር ግርማ በዲቁና ማጥመቅ አንድ የሰማሁትን ታሪክ ትዝ አስባለኝ፡፡ አባ እርሶ ታርኩን በትክክለ ያውቁታል፡፡ ታሪኩን በትክክል አላስታወስኩት እንሆን ያርሙኛል፡፡ መሠረታዊ ነገሩ ግን እንደዚሁ ነው፡፡ የሆነው በታላቁ የቤተክርስቲያን ሰው በአትናቲዎስ ዘመን ነው ተብዬ የተነገርኩት፡፡ ታላቁ አባት አትናቲዎስ ሕፃኑ ራሱ ይሁን በወቅቱ የሕጻኑን ጥምቀት ያፀቀው ካህን ይሁን በትክክል አላስታውስም፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ አንድ ከክርስቲያን ወገን የሆነ ሕጻን ውሎው ከአሕዛብ ልጆች ጋር ነበርና ለአህዛቦቹ ልጆች ስለክርስቶስ፣ ጥምቀትና ክርስትና እየነገራቸው ሕጻናቱ አምነው ያንን ሕጻን አጥምቀን አምነናል ይሉታል፡፡ እሱም በንጹኅ ሕሊናው ልጆቹን ያጠምቃቸውና ወደ ካህኑ ወስዶ ስለሆነው ነገር ሁሉ ለካህኑ ይነግረዋል፡፡ ያ ካህን ሁለተኛ እነዚያን የአህዛብ ልጆች አላጠመቃቸውም ሕጻኑ በአጠመቃቸው ጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነታቸውን አጸደቀ እንጂ፡፡ ከሌላውም ጥምቀት በላይ ይህ የእግዚአበሔርን ልጅነት የሚያሰጥ ጥምቀት ነው፡፡ ግን እግዘአበሔር ካለ ማን ሊያግድ ይችላል? ይህ ነው የታላላቆቹ አባቶች እምነት፡፡ ዝም ብሎ ተነስቶ ወግና ባሕልን እየደባለቁ ለራስ በሚመች አይነት የእግዚአብሔርን ሥራ መንቀፍ ለሕሊና ዕዳ ከመሆን በቀር ትክክል አይደለም፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 18. ብዙ ሌሎች የተባሉ ነገሮች ጥናት በተባለው ላይ የቀረቡ አሉ፡፡ የሚኖሩበት ቤት ዘመናዊነት ተነስቷል፡፡ እውን መምህሩ ከሕዝብ በሰበሰቡት ገነዘብ ነው ይህን ቤት የገዙት? ለብዙ ዘመናትስ ብዙ ሺ ሕዝብ እያገለገሉ በዚሁ አገልግሎታቸው ከቤተክርስቲያን ሰዎችና ከአንዳንድ ግፍ ተናጋሪዎች ጠንቋይ ናቸው ተብለው የሚያከራያቸው እንኳን አጥተው ሲንከራተቱ የነበሩ ሰው አልነበሩም? በተሰጣቸው ፀጋ ለሚሰጡት አገልግሎት ሳንቲብ ሰጠሁ የሚል አለ? በሚሊዮን ቢያወጣ የመዳን ተስፋ የሌለው በሽተኛና ልዩ ልዩ የኑሮ ውስብስቦች ያሉበት አይደለም እያዳነ ያለው? ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በራሱ ተነሳሽነት ችግራቸውን አስተውሎ ደስ ስላለው ብቻ ሚሊዮን አውጥቶ ቤት ቢገዛላቸው ምን ይገርማል? የእሳቸውስ በዘመናዊ ቤት መኖር ሐጥያት ነው? ደግሞ እግዚአበሔር ፈቀደ! ትዕግስታቸውን ተመለከተ! በደሳሳም ኖሩ በዘመናዊ ቤት እንደማይለወጡ ያውቃልና! መቁጠሪያ ይሸጣሉ? አዎ ግን አኝህ ሰው መኖር የለባቸውም? ቤተክርስቲያኒቷ ደሞዝ ትከፍላቸዋለች? እንደሰማነው የቤተሰብ አስተዳደሪ ናቸው? ደግሞስ መቁጠሪያውን በነጻ ነው የሚሰሩት? በቅጥረ ቤተክርስቲያን መሸጥ መለወጥ አይቻልም! አዎ ትክክል ነው! ግን ምን ዓይነት ዕቃ? መንፈሳዊ መጻሕፍት? መንፈሳዊ መዘሙሮችና ትመህርቶች? ሌሎች መንፈሳዊነት ያላቸው መገልገያዎች? አዎ ሁሉንም ከተባለ ደግሞ እንደዛው መሆን አለበት፡፡ መምህር ግርማ ጋር ብቻ ሲመጣ አይደለም ጥፋት የሚሆነው፡፡ ለሌሎቹም ስህተት ሀኖ ዝም ስለተባሉ መምህር ግርማም ዝም ይባሉ እያልኩ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የንግድ ሳይይሆን የአገልግሎት ነው ብዬ ስለተረዳሁት እንጂ፡፡ ስህተት ከሆንም የመምህር ግርማ አግባብ ባለው እርምት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ይልቁንም ለማስተካከል በሚያስቸግሩ ሁኔታዎች በዚያው ደብርና በሌሎችም እየተካሄዱ ያሉ ንግዶችን እንዴት ማየት አልቻሉም አጥኚዎቹ፡፡ የወይራ ዘይት ግን ሲሸጥ አላየሁም! ሰዎች ገዝተው ያመጡትን ሲባርኩ እንጂ፡፡ ከፋብሪካ የወጣ ዘይት? ታዲያ ከሰማይ የወረደ መሆን አለበት? የወይራ ዘይት በዘይትነቱ ዘይት ነው! ከፋብሪካ መውጣቱ የወይራ ዘይትነቱን ይቀይረዋል? እንደውም ጥራቱን የጠበቀ ያደርገዋል እነጂ፡፡ ቅባ ቅዱስ የሚሆነው በጸሎት ስለሚባረክ ነው? መቁጠሪያ ከወጭ አትግዙ ከእኔ ብቻ ግዙ አላሉም ገዝተውም ሲያመጡ ባርከው ሲሰጧቸው ግን እናያለን? ግን ለምን የምናውቃትን እውነት እንክዳለን? ባለማወቅ ከሆነ በጥርጣሬም ቢሆን ገማልያ ክርስቶሳውያንን ይከሱ የነበሩትን የመከራቸውን አንኳን ምክር ለማደመጥ እንሞክር፡፡
  ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ወደ ኪሳቸው ገብቷል? እኮ ካለም በማስረጃ ቢሆን አይሻልም? በተቃራኒው ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለቤተክርስቲያን አስገብተዋል! በተረጋገጠ ሰነድ! ይልቁንም እሳቸው የሚያስገቡትን ገቢ ለመቀራመት ብዙዎች ሲሞክሩ የእሳቸው ለእግዚአብሔር ቤት የተሰበሰበ የሕዝብ ገንዘብ በምንም ዓይነት በግለሰቦች እጅ አይወድቅም የሚለው ፅንፈኛ አቋማቸው ብዙ የቤተክርስቲያን ሰዎች ነን በሚሉ ሰውች ጥርስ ውስጥ እንዳስገባቸው እንታዘባለን፡፡ ሌሎችንም ደብራት ትተው ሁሉንም የሳምንት ጉባዔያቸውን እስጥፋኖስ ያደረጉበት ምክነያቶች አንዱ እሳቸው ለቤተክርስቲያን የሚያሰገቡትን ገንዘብ አለአግባብ ሲጠቀሙ ስለሚበሳጩ ነው፡፡ እስጥፋኖስ ግን በተለይ ከቀድሞው አስተዳዳሪ ከነበሩት ጋር በነበራቸው የፍቅርና የመተሳሰብ ግንኙነት ጉባዔውም በአግባቡ እየተካሄደ የሚገኘውም ገቢ በትክክል መግባቱን በሰነድ/ካርኒ እየተሰጣቸው ነበር፡፡ እስካሁንም የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት ቀድሞ በነበረው አሰራር ስለቀጠለ የእስጥፋኖስ ጉባዔ ገንዘብ እዛው ተቆጥሮ ካርኒ ይቆረጥባታል፡፡ ይህ ግን በአሁኑ አስተዳደር የተወደደ አይመስልም? የአሁኑ አስተዳደር ሰሞኑን ያደረገው ድርጊትም ብዙዎቻችን እንደምንረዳው ዋነኛው መንሰዔ ከዚሁ የገንዘብ ጉዳይ ጋር ይመስለናል፡፡ ሌላ ሌላውን ሳይጨምር የቀድሞው አስተዳዳሪ በነበሩት ጊዜ መምህር ግርማ የሚያስተምሩበት ጉባዔ ለቤተክርስትያኗ ሕንጻ ማሳደሻ ብቻ ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሺ ብር በላይ በተረጋገጠ ሰነድ አበርክቷል፡፡ በእንዲህ ያለ ሕብረት የተሰራን በጎ ሥራን ለማጥላላት አጥኚ ነኝ ያለው በዛሬው የደብሩ አስተዳዳሪ የሚመራው የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ግን የቀድሞው አሰተዳዳሪ የነበሩትንም በጽኑ ይኮንናል፡፡ ግን ለምን? ሕሊና እያወቀ የሚሸረብ ሴራ ለንስሐ እንኳን ይመቻል? አባ አኛ ተራዎቹ ይሄንን አንደፍረውም! ነው ወይስ ወደ ቤተክርስትያን ጠጋ ብለን ሚስጥሩን ብንረዳ ድፍረትን እናገኝ ይሆን? ነው ወይስ በጎ የሚባለው ነገር እኛ ከምናውቀው ውጭ ነው?አባ ግን አኮ እግዚአበሔር ለእኛም ማስተዋሉን ሰጥቶናል! ሕሊና ከሳሽም ፈራጅም ነው! ሌሎችም ለክስ የቀረቡ ጉዳዮች ተዘርዝረዋል፡፡ አባ እውነትን አለመረዳት ይኖራል ከአወቅናት በኋላ ግን ብንክዳት ከሳሽም መስካሪም ፈራጅም የሆነው ሕሊናችንን እንደበቀው ዘንድ አይቻለንም!
  እንደሰው ስህት እነኳን ቢኖር ሊስተካከል በማይችል ሁኔታ ያለ አለ? አባ እኔ በበኩሌ ይሁዳ ክርስቶስን አሳልፎ ሰጠ ብዬ ለመክሰስ አቅም የለኝም፡፡ እኔም በዘመኑ ብኖር ከይሁዳ ወይም ሌሎች በክርስቶስ ላይ አጃቸውን ከሰነዘሩት እንደ አነዱ አለመሆኔን ማረጋገጥ አልችልምና፡፡ እውነትን ካለመረዳትስ ቢሆን ምህረት አለኝ፡፡ ግን ከሕሊና ክፋት ከሆነ ለመጸጸትም (ለንስሀም) ይከብዳል፡፡ ይሁዳም ሞክሮ ነበር፡፡ ከሕሊናው ክፉ የሆነ ሰይጣንን የሚወክል ባሕሪ እንዳለው አስባለሁና፡፡ ወደ አእምሮ አንዴ የገባች እውቀት በሁለት መንገድ ልትካድ ትችል ይሆናል፡፡ አንድ ከሕሊና ክፋት፣ ሁለት ከስጋ መሰሰት (ለጥቅም ወይም በፈርሀት)፡፡ ከስጋ መሰሰት የምተመጣዋ ክደት የጴጥሮስን አይነት ልትሆን ትችላለች፣ ከሕሊና ክፋት ግን የምትመጣዋ የይሁዳ አይነት ትሆናለች፡፡ በሕሊና ያልበደለ ግን ሁሌም ተስፋ ያለው ይመስለኛል፡፡ እውነትን አንኳን ቢሳሳት ያወቀ ዕለት ሕሊናው የእውነት ምስክር ለመሆን ብቁ ናትና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ እረዳዋለሁ! አባ አባከዎን አውቀቱ ሁሉ እርሶ ጋር አለ ግን እንዲሁ አንዳወቁት ስለሕሊና ፍርድ የዚህንም ሌሎችንም የበቤተክርስቲያንና የሚመሩትን ሕዝብ ነገር ይዳኙ፡፡ ሥለ ሕሊናና ዕውነት ብዙዎች ከእርሶ ጋር እንቆማለን!
  እግዚአብሔር የምናስተውልበትን አእምሮ ይስጠን! ለማይረባ አእምሮም ከመዳረግ ይሰውረን! የሠላም አመላክ ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!
  ከሕሊና ፍርድ ናፋቂው አንዱ

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን ።በጣም የሚገርም ነው እኮ! ማስተዋሉን ይስጣቸው እንግዲህ።

   ሰርዝ
 19. አንድ አድርገኖች ፕሮቴስታንቶች እንኩዋን አገልጋዮቻቸውን ://good-amharic-books.com/images/PDFs/ezmag021.pdf በመጽሃፍ ቅዱስ መንጽር ነው እየገመገሙ ነው ዘግይቶም ቢሆን!! እናንተም መምሀር ግርማን በምን መልኪያ እንደልእካች ንገሩን = ያለ reason ግን የሰው ስም አታጥፉ!!!! እስኪ ይሄን ተመልክእቱት ://good-amharic-books.com/images/PDFs/ezmag021.pdf ....ቲ. ቢ. ጆሹዋ ማን ነው? በሚል የሰውየውን ማንነት፥
  ትምህርቶቹን፥ ትንቢቶቹን፥ ፈውሶቹን ከቃሉ አንጻር እንድናይ የተጻፈ
  ነው። ይህን ሰው አንዳንዶች እንደ ታላቅ የዘመናችን የእግዚአብሔር
  ነቢይ ሲያዩት ሌሎች እየተሳካለት ያለ አሳችና አጭበርባሪ እንደሆነ
  በድፍረት እየገለጡ ይገኛሉ። አንዳንዶች የሚያውቁት ከቴሌቪዥን
  ስርጭቱና ከኢንተርኔት ብቻ ነው። አንዳንዶች የሚያዩትንና የሚሰሙትን
  በቃሉ መፈተን የማይችሉ ወይም የማይወድዱ ደግሞ በግድ የለሽነት
  ወይም በፍርሃትና በይሉኝታ የዝምታ ዝማም ተሽሸብበው እየዘለቁ
  ናቸው። ከየትኞቹ ነን? በዚህ መጣጥፍ የሰውየውን ትምህርቶች
  በተለይም ትንቢቶችና ልምምዶች ከሁለት አቅጣጫ እንመለከታለን።
  አንዱ ከውስጡ የወጡ ሰዎች ምስክርነት ሲሆን ሌላው ዘመን አይሽሬው
  ቅዱስ ቃል ነው።...://good-amharic-books.com/images/PDFs/ezmag021.pdf

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 20. sayetan bago seran yamadenakef serawe tawatolatal.[tassaktolatal] gen yetasseral.andu maderage yakatawen lalawe wandemachawe seyaderg bamayetachawe bakenate yatakatellu sawoch yaderagut yamekagenate sara nawe. yahezebe fawesse enkwane ayassedasetachehume ???

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 21. ብዙ ሌሎች የተባሉ ነገሮች ጥናት በተባለው ላይ የቀረቡ አሉ፡፡ የሚኖሩበት ቤት ዘመናዊነት ተነስቷል፡፡ እውን መምህሩ ከሕዝብ በሰበሰቡት ገነዘብ ነው ይህን ቤት የገዙት? ለብዙ ዘመናትስ ብዙ ሺ ሕዝብ እያገለገሉ በዚሁ አገልግሎታቸው ከቤተክርስቲያን ሰዎችና ከአንዳንድ ግፍ ተናጋሪዎች ጠንቋይ ናቸው ተብለው የሚያከራያቸው እንኳን አጥተው ሲንከራተቱ የነበሩ ሰው አልነበሩም? በተሰጣቸው ፀጋ ለሚሰጡት አገልግሎት ሳንቲብ ሰጠሁ የሚል አለ? በሚሊዮን ቢያወጣ የመዳን ተስፋ የሌለው በሽተኛና ልዩ ልዩ የኑሮ ውስብስቦች ያሉበት አይደለም እያዳነ ያለው? ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በራሱ ተነሳሽነት ችግራቸውን አስተውሎ ደስ ስላለው ብቻ ሚሊዮን አውጥቶ ቤት ቢገዛላቸው ምን ይገርማል? የእሳቸውስ በዘመናዊ ቤት መኖር ሐጥያት ነው?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 22. በተሰጣቸው ፀጋ ለሚሰጡት አገልግሎት ሳንቲብ ሰጠሁ የሚል አለ? በሚሊዮን ቢያወጣ የመዳን ተስፋ የሌለው በሽተኛና ልዩ ልዩ የኑሮ ውስብስቦች ያሉበት አይደለም እያዳነ ያለው? ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በራሱ ተነሳሽነት ችግራቸውን አስተውሎ ደስ ስላለው ብቻ ሚሊዮን አውጥቶ ቤት ቢገዛላቸው ምን ይገርማል?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 23. ለመሆኑ ስራተ ቤተክርስቲያን የጠበቁ የምትሉዋቼውን ካህናት እስኪ ንገሩን? በሰንቤት ትምህርትቤት እያለሁ ባንድ ወቅት ካህናቱና ሰንበት ተማሪው ተጠታላን እኛ ጉዳዩን ልንገፋበት ነበር ግን ሁላ ቤተሰቦቻችንም ድግምት ሊያደርጉባችሁ ይችላሉና አርፋችሁ ተቀመጡ ተባልን ታድያ እንዚህ ይሆኑ ስራት የጠበቁት! የአገራችን ምስኪን ድሃ መታከሚያ የለውም ቢኖረውም እንኩዋ ችግሩ መንፈሳዊ ነውና አይድንም አሜሪካ ያልዳኑ ሁሉ በመምህራችን ተፈውሰዋል!እግዚአብሔር ይፈርዳል አይፈርድም አትበሉ !እግዚአብሔር ይፈርዳል አይፈርድም አትበሉ ! ለዚህ እረኛ ለሌለው ምስኪን ደሃ ህዝብ ይፈርዳል!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 24. ከደብዳቤዎቹ በተጭማሪም የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አጥንቼ አግኝቼዋለሁ የሚለውንም የመምህር ግርማን ክስ በየኢነተርኔቱ አስነብቦናል፡፡ የሚያሳዝነው ግን አሁንም ጥናት ብለው ባቀረቡት ጽሑፍ የተጠቀሟቸው ቃላቶች በጣም ከግበረ-ገብነት የወጡ መሆናቸው ነው፡፡ ጥናት የመረጃ አቀራረቡ እንዴት እንደሆነ ቢጠይቁ እንሱንም ከትዝብት ያድናቸው ነበር፡፡ አንድ የጥናት ሰነድ ሲቀርብ መጠቀም ያለበት መደበኛ ቃላቶችን እንጂ አንባቢን በሚያስደንቡሩ ስድቦችና አስነዋሪ ቃላቶች ታጅቦ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ አጠኚው ሲጽፍ እራሱን ገለልተኛ አድርጎ በአገኘው ውጤት ላይ ብቻ ተመሥርቶ እንጂ የራሱን ስሜት አጠናሁት በሚለው ጉዳይ ቢያስነብብ ልብወለድ እንኳን ለመሆን አይበቃም ምንአልባት አሉባልታ ከሆነ እንጂ፡፡ ልብወለድም የብዙ ማሕበራዊና ነባራዊ ጉዳዮችን ጥልቅ ግንዛቤ ይጠይቃልና፡፡ በዚህ አጋጣሚ እነዚህ ሰዎች ያደረጉት ለሕዝብ ማንነታቸውን ማሳወቅን እንጂ የጥናታቸውን ማረጋገጫ በመተንተን ጭብጥን ማሳወቅ አይደለም፡፡ ከጥላቻ፣ ከቅናት፣ ከአደመኝነት፣ ከበቀልና ከመሳሰሉት የክፋት በሕሪያት በተወረሱ ቃላቶች የጥናትን ውጤት መዘገብ ከንቱ ነው፡፡ ድርጊቱ አንኳን እነሱ እንደሚሉት ቢሆን እውነታንም የጨልማልና፡፡..

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 25. እውነትን ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!ስቀሏት!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 26. አባ መምህር ግርማ በደብሩ ቅጥር ግቢ እየሰጡ የነበሩትን አገልግሎት ማገድ ሥልጣንና ጉልበት እስካለ ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡ ለቤተክርስቲያንም እውን ከመቅናት የተነሳ ድርጊት ከሆነም ሕሊና ስላሰበው ተደርጓልና ከክፋት አይቆጠርም የቱንም ያህል እውነትን ካለመረዳት ስህተት አንኳን ቢሆን፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ግን ሕሊናንም እውነትንም በመካድ ስለሚመስል አደገኛ ድፍረት ነው በዬ አምናለሁ፡፡ ሒደቱ ሁሉ ውስብስብ ተንኮለኝነት የተቀመሙበት ይመስላልና፡፡

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 27. አባ መምህር ግርማ በደብሩ ቅጥር ግቢ እየሰጡ የነበሩትን አገልግሎት ማገድ ሥልጣንና ጉልበት እስካለ ብዙም ላያስገርም ይችላል፡፡ ለቤተክርስቲያንም እውን ከመቅናት የተነሳ ድርጊት ከሆነም ሕሊና ስላሰበው ተደርጓልና ከክፋት አይቆጠርም የቱንም ያህል እውነትን ካለመረዳት ስህተት አንኳን ቢሆን፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ ግን ሕሊናንም እውነትንም በመካድ ስለሚመስል አደገኛ ድፍረት ነው በዬ አምናለሁ፡፡ ሒደቱ ሁሉ ውስብስብ ተንኮለኝነት የተቀመሙበት ይመስላልና፡፡ እውነት ችግር ካለባቼው @የቀድሞው አስተዳዳሪ ለምን @አልጠተቃወሟቼውም? @አዲሱ አስተዳዳሪ@- አንድ ወር@ እንኹዋን ሳይሞላ ለምን ግጭት ፈጠሩ? እውነት ለ..... ወይስ ለጥቅማቼው?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 28. Because he cast out devil from Menefeqan’s? He heals blind woman? He cast devil from peoples? He exposes the devil works? Please tell me what he did wrong? Instead of fighting a man of God, why don’t you fight the so called ‘Bete kihnet’ who is a cancer to our church growth and brought shameful to the church leader?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 29. ከሕዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ወደ ኪሳቸው ገብቷል? እኮ ካለም በማስረጃ ቢሆን አይሻልም? በተቃራኒው ግን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ @ለቤተክርስቲያን@ አስገብተዋል! በተረጋገጠ ሰነድ! ይልቁንም እሳቸው የሚያስገቡትን ገቢ ለመቀራመት ብዙዎች ሲሞክሩ የእሳቸው ለእግዚአብሔር ቤት የተሰበሰበ የሕዝብ ገንዘብ በምንም ዓይነት በግለሰቦች እጅ አይወድቅም የሚለው ፅንፈኛ አቋማቸው ብዙ የቤተክርስቲያን ሰዎች ነን በሚሉ ሰውች ጥርስ ውስጥ እንዳስገባቸው እንታዘባለን፡፡ ም እመናን ከግቢ በማባረራቼው አንድ ህጻን ልጅ በጅብ ተበልቶ መሞቱን አታውቁ ይሆን ለመሆኑ አዲሱ አስተዳዳሪ- ሳምንት ሳይሞላቼው መምህሩንም ሳያነጋግሩ ሊጸበሉ ምእመናን ከግቢ በማባረራቼው በዚህ ሰው በላ አስተዳዳሪ ምክንያት ከግቢው ተባረው አንድ ህጻን ልጅ ማደሪያ አጥቶ በጅብ ተበልቶ መሞቱን ለልጆ ፈውስ ሽታ ከድሬዳዋ ድረስ እናቱ እንባዋን እያረገፈች ለ ላይፍ መጽሄት የሰጠችውን አንብባችሁስ ይሆንአታውቁ ይሆን??????

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 30. ለመሆኑ ቤትክርስቲያን ለናንተ ህዝብ አይመስላችሁም አይደል ለናንተ የ ህዝቡ ስቃይ ግድ አይሰታችሁምአገር የሚባለው ህዝብ ነው መሬቱ አይደለም በሚባልበት ዘመን ለናንተ ግን ቢተክርስትያን ማለት..... አየ፣ ምነው እመ ብርሃን?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 31. በተላያዩ ብዙ ፈተናዎች መሀከል አልፈው መምህሩ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ደረሱ፡፡ ዛሬ እንደድሮው የሚታለል ሕዝብ እያነሰ በእሳቸው ትምህርሕርት ራሱን እያወቀ ለእግዚአብሔር የሚንበረከክ ሕዝብ እየበዛ መጣ፡፡ ፈታኞቹ ግን ዛሬም ተስፋ አልቆረጡም፡፡ ፈተናው ግን የአንዱ የመምህር ግርማ ሳይሆን የሕዝብ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላም ፈተናውን መወጣት የሕዝብ ድርሻ ነው፡፡ እስከዛሬ ሕዝብ እስከሚገባው በሚል መምህሩ ብቻቸውን ፈተናዎችን ሁሉ በመጋፈጥ መስዋዕት ሆነው ሕዝቡን ለዚህ አብቀተውታል፡፡ ይሄው ሰሞኑን በሰማንው ድርጊታቸው በገሃድ ማንነታቸውን ነገሩን፡፡ እሳቸው ባሉበት ቢሆን ጥሩ ነበር አስለፍልፈው ውደ ሲኦል ይሸኙላቸው ነበርና፡፡ በእስጥፋኖስ ቤተክርስቲያን መምህር ያስተምሩበትን የነበረውን መድረክ አፈረሱ፣ በመደረኩ ላይ ተደርድረው የነበሩ የቅዱሳን ስቀላትን ቀዳደዱ፣ አላማቸው ነበርና የእግዚአበሔር ቃል የሚነገርበትን አጋንንት የሚነዱበትን ጉባዔ አስታጎሉ፡፡ እና እነዚህ “ሰዎች” ማን ናቸው? በመጨረሻም ደብዳቤ ፅፈው ቤተክርስቲያኒቷ ግድግዳ ላይ ለጠፉ፡፡ መምህር የነበሩት በቅድስት አገር እየሩሳሌም ነበር፡፡
  የተጻፉት ደብዳቤዎችና ይዘታቸው
  የመጀመሪያው ደብዳቤ በ28/08/2005 የተጻፈ በቅዱስ እስጥፋኖስ የደብሩ አስተዳዳሪ በአባ ሚካኤል ታደሰ የተፈረመ ነው፡፡ ለመምህር ግርማ ወንድሙ ይላል፡፡ የዚያን ያህል ባይካበድም እንደ እንድ ማህተብ ያለው ደብዳቤ ሥህተቱ እዚሁ ይጀምራል፡፡ ደብዳቤው ሕጋዊ ፕሮቶኮል እስከጠበቀ ድረስ ስማቸውና ማዕረጋቸው በትክክል መጻፍ አለበት፡፡ እኔም አዚህ መምህር እያልኩ የሚጸፈው የተለመደውንና በሕዝብ የታወቀውን ብዬ እንጂ የመምህሩ የአሁኑ ማዕረግ ከላይ የጠቆምኩት መለአከ መንክራት ነው፡፡ ይዘቱ በ2003 ዓ.ም. በአቡነ ቀውስጦስ በተጻፈ ደብዳቤ መምህር መታገዳቸውን ያትትና በአለታወቀ ምክነያት ግን እስከዛሬም መምህር እያስተማሩ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሆኖም ብዙዎቻችሁ ከቀድሞው የደብሩ አስተዳዳሪ መለአከ ሰላም ዘላለም አሴይ እንደሰማችሁት መምህር እዛ ቦታ ላይ የሚያስተምሩት ሕጋዊ በሆነ ደብዳቤ ተጋብዘው ነው፡፡ ከቀድሞው የቤተክርስቲያኒቷ ፓትሪአርክ ብፁዕ አቡነ ጰውሎስም ሕጋዊ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የደብዳቤውም ቀጅ በእጃቸው እንደሚገኝ መልአከ ሰላም ዘላለም እሴይ ተናገረዋል፡፡ እንደው እሳቸውን ማጣቀሱ አግባብ ስለሆ እንጂ እኔ ራሴ ያ ደብዳቤ መድረክ ላይ ሲነበብ ሰምቻለሁ፡፡ ደብዳቤው የተጻፈውም በሕዝብ ጥያቄ እንጂ መምህር ጠይቀው አይደለም፡፡ ደብዳቤውም የትም ሄደው ማስተማር የሚያስችላቸውን ፍቃድ የሚገልፅ ነበር፡፡ የተጻፈውም አቡነ ቀውስጦስ እገዳ ጻፉ በጸባለበጽ በ2003 ዓ.ም፡፡ እውን የተባለው የአቡነ ቀውስጦስ ደብዳቤ አለ? ከአለስ በምን አግባብ ነው? ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ ይህ የደብሩ አስተዳዳሪ የጻፉት ደብዳቤ ተጨባጭ ምክነያትን ከማቅረብ ይልቅ በተደጋጋሚ ሕገ-ወጥ በሚል ቃል ታጭቋል፡፡ በአጻጻፍ ቀርጹና ሥርዓቱ ግን ከዚህ በታች ከምገጸው ከመንበረ ፓትሪአርክ ጸ/ቤት ተጻፈ ከተባለው ደብዳቤ የተሻለ ነው፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጸ/ቤትና ለሌሎችም አካላት ግልባጭ ይላል፡፡
  ሁለተኛው ደብዳቤ በ08/09/2005 የመንበረ ፓትሪአርእ ራስጌ (heading paper)ወረቀት የተጻፈ፣ የመንበረ ፓትሪአረኩ ጽ/ቤት የሚል ማህትም ያለበት፣ ፊርማ ያለበት ግን የፈራሚው ሥም የሌለበት ነው፡፡ ይዘቱ በብዛት ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ይወጣል ተብሎ ለማመን የሚያዳግት፡፡ ቃላቶቹ ያለታረሙና በየተኛውም ሕጋዊ ደብዳቤ መታየት የሌለባቸው፤ ለምሳሌ ሥርዓተ-አለበኛ፣ ሕገ-ወጥ፣ የመሳሰሉት፡፡ ሲጀምር ጉዳዩ ይልና በአስቸኳይ በደብሩ በተባለው ቀን፣ የደብዳቤው ቁጥር ተጠቅሶ የተደረገው አገዳ የጸደቀ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ የጻፈው ለደብሩ ነው፡፡ ለመምህሩ ግልባጭ የለውም፡፡ ባለጉዳይ እሰከሆኑ ድረስ በግልባጭ እንዲያውቁት መደረግ ነበረበት፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያው ደብዳቤ የተጻፈው ለመምህር ግርማ ነው፡፡ በሌላላ የተለየ ደብዳቤ ካልሆነ በስተቀር የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የላኛው ደብዳቤ የደረሰው በግልባጭ ነው፡፡ እንደ ደብዳቤዎች አጻጻፍ ሥርዓት ከላይ የተጻፈውን ደብዳቤ ለማጽደቅ የፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ሌላ ደብዳቤ መጻፍ የለበትም፡፡ ከደብዳቤው ጋር የሚቃረንና እርምት የሚያስፈልገው ነገር ኖሮ ኃላፊነቱን ካለበት እንጂ፡፡ ውሳኔው ቀድሞውኑ ተወስኗል፡፡ ለመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የተደረገው እንዲያውቀው ግልባጭ ነው፡፡ እዚህ ላይ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ደብዳቤ አጽፍም አይደለም ግን የሚጽፈው ኃላፊነት ስላለበት ማስተካከያ/እርምት ነው እንጂ ድጋፍ ሊሆን አይገባም፡፡ እንዲህ ያሉ ውሳኔውች ሌሎች ከውሰኑ በኋላ ማጽደቅ ሳይሆን ባይሆን ራሱ ወስኖ ለሌሎች ማስተላለፍ ነውና የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ድርሻ፡፡ ደግሞ ስንት ዘመን በግልፅ የነበረውን መድረክ አስቸኳይነቱ ለምን? ይዘት በዋናው ንባብ አጥማቂና ፈዋሽ ነኝ በማለት (መምህርን መሆኑ ነው) ይላል፡፡ መምህር አጥማቂም ፈዋሽም ነኝ ብለው አይደለም ሰው የአገልግሎቱ ተጠቀሚ የሆነው፡፡ አኛ ራሳችን የሚካሄደውን የፈወስና ወንጌል አገልግሎት በአይናችን ስላየን በጆሮአችን ስለሰማን እንጂ፡፡ እሳቸው ከሁላቸው በተሻለ የአምላካቸውን ክብር ያውቁታል፡፡ የሚያድነው የእግዚአበሔር የስሙ ኃይል ነው እኔ አገልጋዩ ነኝ ከማለት በቀር እኔ ፈዋሽ ነኝ ሲሉ ሰምተናቸው አናውቅም፡፡ ደብዳቤው እንደምንም ተንገዳግዶ ሌላ ፖለቲካ የሚመስል ነገር ለመጥቅስ የሞክራል ቤተክርስቲያናችን ከተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ ትላልቅ ሌሎች ተቋማት አቀሪያቢያ መሆኑንና በአካባቢውም የመምህር ጉባዔ የጸጥታ ችግር እንደፈጠረ የከሳል፡፡ በመጨረሻም ለፖሊስና ለጸጥታ ኃይሎች ትብብርን ይጠይቃል፡፡ እንዚህ ኃይሎች ግን እንዲያወቁበት የተደረገ ነገር የለም፡፡ ይህን ምንአልባትም አዛው በደብሩ አስተዳዳሪ የተፈበረከ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ባላወቀው መልኩ በሥሙ ወንጀል እየተሰራ ሊሆን ስለሚችል ማጣራቱ ወሳኝነት አለው፡፡ ከመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤትም እውን የወጣ ከሆነ ፈራሚው ማነው? ይዘቱስ የዚህን ያክል ጽ/ቤቱን በሚያስገሚት ሁኔታ እንዴት ሊወርድ ቻለ፡፡ አግባብነቱስ እንዴት ይታያል? በመጀመሪያ ላለተጠየቀው መልስ መስጠቱ (የመጀመሪያው ደብዳቤ የመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት ለመጠየቅ ሳይሆን ለማሳወቅ ነበርና)፣ ለመምህሩ ግን እንዲያወቁት አልተደረገም፡፡ የሕዝብስ ጉዳይ በመንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤት የሚታየው እንዴት ነው?ሕዝብን ወይም ተወካዩቻቸውን ሳያናግሩ?
  ምን ይሁን፡በየትኛው ደረጃ ያለ የቤተክርስቲያኒቷ መሪም ይሁን አካል የምዕመንን እንጂ የተሿሚዎችን ብቻ ድምጽ እሰማ በቤተክርስቲያኒቱ እንደፈለገው የመሆን መብት ሊኖረው አይገባም ማንም ቢሆን አግባብ ያሌለው ነገር ሰርቶ እነደሆነ በሕግ እንዲጠየቅ፣ መንበረ ፓትሪአርኩ ጽ/ቤቱ በእዚህ ነገር እውን ካለበት በሕዝብና በሕግ አግባብ ሊጠየቅ ይገባዋል መምህር ግርማ ለሕዝብ ጠቃሚ ናቸው እስከተባለ ድረስ ጉባዔያቸውን የሚያውኩ ግለሰቦች በሕግም በቤተክርስቲያኗ ደንብም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡
  እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያሳስበን!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 32. Please watch (tekulaw manew?) የኘሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የመምህር ግርማን ስም ለማጥፋት ያዘጋጁትን ባለ አራት ክፍል ፊልም ተመልከቱያዘጋጁት ፕሮተስታንቶች መሆናቼውን ያዙልኝ!!!ፊልሙ ላይ ግርማን ሰዉ አስደበደቡ ሲሉ ሰምቻለሁ::መምህር ዘበነንም እንዲሁ ያዉ ጉዳቸዉን እያዎጣ ስላስችግራቸዉ ይምሰለናል ፎቶዉን በምስሉ በፖሊስ እንደሚፈለግ ዎንጀለና ሲያመለሱት ነበር:: ከላይ ያነበባችሁት እግድ ደግሞ የዚያ ቀጣይ ክፍል መስለኝ አይመስላችሁም???

  http://www.youtube.com/watch?v=o0I1QCs1ZkA
  http://www.youtube.com/watch?v=jTdi5_gsINU
  http://www.youtube.com/watch?v=pvqrz68xnuc
  http://www.youtube.com/watch?v=SkMC7MAz4_M

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 33. Please watch (tekulaw manew?) የኘሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የመምህር ግርማን ስም ለማጥፋት ያዘጋጁትን ባለ አራት ክፍል ፊልም ተመልከቱያዘጋጁት ፕሮተስታንቶች መሆናቼውን ያዙልኝ!!!ፊልሙ ላይ ግርማን ሰዉ አስደበደቡ ሲሉ ሰምቻለሁ::መምህር ዘበነንም እንዲሁ ያዉ ጉዳቸዉን እያዎጣ ስላስችግራቸዉ ይምሰለናል ፎቶዉን በምስሉ በፖሊስ እንደሚፈለግ ዎንጀለና ሲያመለሱት ነበር:: ከላይ ያነበባችሁት እግድ ደግሞ የዚያ ቀጣይ ክፍል መስለኝ አይመስላችሁም???
  http://www.youtube.com/watch?v=o0I1QCs1ZkA
  http://www.youtube.com/watch?v=jTdi5_gsINU
  http://www.youtube.com/watch?v=pvqrz68xnuc
  http://www.youtube.com/watch?v=SkMC7MAz4_M

  ምላሽ ይስጡሰርዝ

 34. “ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው። ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ። ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው። እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም። ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል። እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል። ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።” ማቴ 12 : 22-32

  ጥያቄዎቼ ይከተላሉ ፡-
  1- እንዲህ ጌታችን ካስተማረን ቃል ውጭ የሆነ ፣ ሰይጣን ሰይጣንን ያስወጣል ፣ አጋንንት አጋንንትን ያስለቅቃል ፣ ዲያብሎስም የመፈወስ ችሎታ አለው የሚለው ትምህርት ከየት ወገን የመጣ ነው ?

  2- የቤተ ክርስቲያን ክህነትን በእርግጥ ከተቀበሉ ፣ ምስጢረ ንስሐ ማለት ስለሌሎች በደል ወይንስ ስለራስ ድክመት መናዘዝና ይቅርታን መጠየቅ የሚያስተምረን ? ምናልባት አዲሱ አስተዳዳሪ በደብተራነትዎ የአባይ ጠንቋይን ሙያ ተገልግለውበት ከሆነ የሠሩበትን ሥፍራና ያገለገሉትን ህዝብ ጠቅሰው ይቅር በሉኝ ማለት እንጅ እነ እገሌ መኪና ገዙ ፣ ፎቅ ገነቡ ማለትዎ ንስሐ ሆኖ ስላልተሰማኝ ነው የምስጢረ ንስሐ ጥያቄዬ ወይንስ በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያን የንስሐ ትምህርቱም ተቀይሮ ይሆን ?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 35. Who are insulting the work of the Holy Spirit! Memehir has been doing this for 15 years millions could survive from your curse because of him! ከቤተ ክርስቲያናችን ኑ ትድናላችሁ ተብለው በሃሰት ስብከት የተነዱትን መንጋዎች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን በመመለሳቸው?በሰውኛ ሲታሰብ በጣም ከባዱ ተአምር የሞተ ሰው ማስነሳት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ያሉ አባቶቻችን የሞቱ ሰዎችን አስነስተዋል።በእነሱ ላይ ይሰራ የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬም እንደሚሰራ ካመንን ዛሬም አባቶቻችን ከሙታን ቢያስነሱ የታመሙ ቢፈውሱ ከፋቱ ምን ይሆን::መቼም እናዉቃለን ሰይጣን ሰዉ ሲታሰር እንጂ ሰዉ ሲፈታ አይዎድም:: አባ ግርማያን ያሁሉ ጉድ በክርስቶስ ስም ለዚያዉም የሰይጣንን ሴራ ከምጽሃፍ ቅዱስ እያጣቀሱ ቢፈዉሱ ምን ይሆን ክፋቱ:: ለምንስ ይገርመናል? እስቲ ከመጽሃፍ ቅዱስ አባቶች የስሩትን ልዩ ልዩ ተአምር እንመልከት በሐዲስ ኪዳን

  ==>ጴጥሮስ ጣቢታን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ.9፣40) ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።
  ==>ጴጥሮስ ሃናንያና ሰጲራ እንዲሞቱ አድርጓል።(ሐዋ.5፣5-10) ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም…. ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም
  ==>ጴጥሮስና ዮሐንስ ሽባውን ተርትረዋል/ፈውሰዋል/።(ሐዋ 3፣2-11)
  ==>ጳውሎስም አውጤኪስን ከሞት አስነስቷል።(ሐዋ20፣9) ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው።
  ==>ጳውሎስ እባቢቱ እንዳልጎዳቸው ምንም ሳይሆን እዳራገፋት ይናገራል።(ሐዋ.28፣5) እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም፤
  ==>የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ይፈውሳቸው ዘንድ ድውያንን ያሰልፉ ነበር።(ሐዋ 5፣ 15) ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።እንግዲህ ከላይ በጥቂቱ የተመለከትነው በብሉይም በሐዲስ ኪዳንም የነበሩ አባቶቻችን ታላላቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ሲያደርጉ ነው። ታዲያ በእነዚያ ዘመናት ሁሉ ታላለቅ ድንቅ ተአምራትን እንዲያደርጉ ሲያደርጋቸው የነበረ መንፈስ ቅዱስ ዛሬ እየሰራ መሆኑን የምናምን ከሆነ ለምን የገብረመንፈስ ቅዱስ ፣የአቡነተክለሃይማኖት ፣የእነ ቂርቆስ ኢየሉጣን ድንቅ ተአምራት መቀበል አቃተን?ሰለስቱ ደቂቅ ከእሳት ምንም ሳይሆኑ መውጣታቸውን ካመኑ ለምን የቂርቆስ እና ኢየሉጣ ከፈላ ውሃ ምንም ሳይሆኑ መውጣት ይጎረብጣቸዋል? ለኢያሱ ግዑዝ ፍጥረት ጸሐይ ታዝዛ ከቆመች ለአቡነገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብርቱ አናብስቱ መታዘዛቸው ምን ያስገርማል? የኤልሳዕ አጽም ሙት ካስነሳ ፤በሕይወት የነበሩ አባቶቻችን ሙት ማስነሳታቸው ምን ያስገርማል?1ኛ ቆሮ.12:4-10 “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው………ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ….”ይሰጠዋል:: ስለሚል የደመላሻችን አባ ግርማም ጸጋም ስጦታ ይህ መሆኑ ነዉ::ከዘህ አካያም ሳየዉ የደም መላሻችን አባ ግርማ በጣም ቀላሉ ተአምር በእግዚአብሔር እርዳታ ሰሩ እላለሁ::ቢቀናችሁ እና ጽጋዉን ቢያድላችሁ እናንተም ሰይጣንን ታስራላችሁና እባካችሁ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንጋጭ እላለሁኝ::ሃይሌ ገ/ስላሴ እንኩአን ይቻላል ሲል አልሰማችሁም::እየቀልድሁ አይደለም ክርስትና ደግሞ ከዚህ በላይ እምናምነዉ ስለሆነ ነዉ::እናንተ ደግሞ መጽሃፍ ታዉቃላችሁ አማኝ ተብላችሁ የምትጠሩ ናችሁና እባካችሁ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ከዲያቢሎስ ለዩ:: ለመለየት ድንግል ትርዳችሁ ነዉ የምለዉ::መቼም ብታቃልላትም እርሱ አተዋችሁምና::

  ጌታችንም እኮ ያለው(ዮሐ.14፤ 12) እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።
  ታዲያአባ ግርማ ካመኑ ምን ማድረግ ይሳናቸዋል? እኛም እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ታሪክ እንድንተርክ ሳይሆን እንድንኖረው ነው የሚጠበቅብን። ቅዱስ ጴጥሮስ ሙት ካስነሳ ፣እኛም ሕይወታችንን ብናስተካክል ፍጹም ክርስቲያኖች ብንሆን በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ የሰራ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ ይሰራልና ሙታን ማስነሳት እንችላለን።ስለዚህ አባቶቻችን ምንም ዓይነት ተአምራት ቢፈጽሙ በእነርሱ አድሮ ስራ የሚሰራ መንፈስ ቅዱስ ነውና ሊሆን አይችልም የሚስብል ነገር አይኖርም።

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 36. Please be there to see the drama. In the meantime you will learn who are intoxicating the church. I really feel sorry that I just have understood millions are against the good would like to witness for their father Devil. Enante Yabatachihun Yediabiolosin Sira Tadergalachihu. Manim Ke Egziabiher Kalhone Bezimu Aganintin Liyaweta Aychlim. Tenqwayochu Yeliul Amlakin Sira Tinkola new bilu aygermim. Christosinim aganint yaderebih bilewut neberina. Ena bedebdabena silitanina gulbet bemetekem new yemitasqomut. Eski kidus paulos ketenqwayua set aganintin endaweta lemin tadia almokerachihum! Christina menfesawi hail enji sigawi hail aydelem yemitekemew. Police, security minamin ayidelem.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 37. jeb kehede wesha chohe malet legna betekerstian astedader nw!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 38. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን። ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ ህያው አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ፣ ቅዱስ አማኑኤል፣ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ክብርና ምስጋና ይድረሰው። አምላካችን እንደኛ አይደለም ስንጠፋ ይፈልገናል፣ ሁሉም እንደማይሳነውም ለጠላታችን ዲያቢሎስም ሆነ ችላ ላልነው ልጆቹ ያሳየናል። እኔ የመምህር ግርማን ጸጋ ከዚህ በተለየ ባየው "አይን እያላችሁ አታዩም፣ ጆሮ እያላችሁ አትሰሙም" ለተባለው ምሳሌ መሆኔን ከማረጋገጤ ባሻገር በእሳቸው በኩል የአምላክን በረከት መቋደስ ለሚፈልጉ መሰናክል በመሆን ጠላታችን ዲያቢሎስን ማገልገል ሊሆን ይችላልና፣ የእመ ብርሃን ወዳጆች፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጆች እባካችሁን የጠፋነው እኛ ልጆቹ ወደ አባታችን ቤት እንመለስበት፣ መምህር ግርማ የጠፋዉንና እየጠፋ ያለዉን ትውልድ ከመመለስ ውጭ ያደረጉት ነገር የለም። እባካችሁን መምህር የሚሰሩትን ስራ ካላመናችሁ ለእኛ ተወት አድርጓቸው፣ እኛ እንኮነን፣ ካጠፋንም በጸሎታችሁ እርዱን እንጂ እንደ አሕዛቦች በየቄሳሩ አደባባይ አንጓተት። ከእሳቸው ጋር ፊት ለፊት መነጋገር ካስቸገራችሁ፣ በሃያሉ አንድ አምላክ፣ በድንግል ማርያም ልጅ በቅዱስ መድሃኒተ አለም አምናችሁ በንጹህ ልብ ከጸለያችሁ ለተቀደሰችዋ አገራችንም ሆነ ለመላው የተዋሕዶ ልጆች እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል። አምላካችን ህያው ነው!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 39. ሽፍታው አኮ ነው ገነት በመግባት ቀዳሚ የሆነው! በተቃራኒው ስርዐት አለን የሚሉት ካህናት እኮ ናቸው ክርስቶስን የሰቀሉት፣ ደቀመዘሙሩ የነበረ ይሁዳ እኮ ነው ጌታን አሳልፎ የሰጠ፡፡ ሰዎች ስርዐትንና ቀኖናን እነሱ በሚመቻቸው እየተረጎሙ መጠቀሚያ ካደረጉትስ?

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 40. ፈሪሳውያን ማለት ከአይሁድ የሃይማኖት ወገኞች አንዱ ክፍል ሲሆኑ ሰው የሚጸድቀው ሕግን በመጠበቅና በመፈጸም ነው በማለት አጥብቀው የሚያምኑና ወግ ሲያጠብቁ ምሕረት፣ ሕይወትንና ደህንነትን ያመለጣቸው፤ ቢከፈት ከአጥንት በቀር ሌላ የማይገኝበት ካማረና ከተዋበ መቃብር ጋር አመሳስሎ የሚገልጻቸው እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ አነጋገር ግብዞች ሰዎች ነበሩ። በተጨማሪ ፈሪሳውያን ማለት -
  Ø ሥራቸው ሁሉ ግራ
  Ø መንገዳቸው ሁሉ ሸፍጥ የሞላበት
  Ø ለክፋት የማይተኙ ርህራሄ የሌላቸው አመጸኞች
  Ø ወግ አጥባዊዎች
  Ø የሚበጃቸው፣ የሚረባቸውና የሚሆናቸውን ለይተው የማያውቁ …
  Ø ደግ ደጉን ከማሰብና ከማየት ይልቅም ሴረኝነትና ጥመት የሚቀናቸው
  Ø ነፍስ ለመጣል የንጹሕ ሰው ደምም ለማፍሰስ ተማምለው የሚወጡ
  Ø ከሳሶች
  Ø መሰረት የሌለውና ያልበሰለ ነቀፋ ለመሰንዘር፣ መልካሙን ሁሉ ለማብጠልጠል ነፋስ “ሮጦ” የማይቀድማቸው
  Ø የተናቁት በእምነታቸው ሲድኑ ከትዕቢታቸው የተነሳ የተኮነኑ ትምክህተኞችም ነበሩ ፈሪሳውያን ማለት።እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ናቸው ኢየሱስን በዕለተ ሰንበት ለምጻምን ታነጻ ዘንድ: የዕውሩንም ዓይን ታበራ ዘንድ እንዴት ብትደፍር ነው? የለም! የለም! ጎበዝ እንደው ይህማ “እንገት ቆርጠህ ጸጉርን እንደ ማስተካከል” ነው ሲሉ አምጸው ሕዝብን ሲቀሰቅሱበትና ሲያሳሙጽበት የምናገኛቸው:: በዚህም አልረኩም /አልተመለሱም ነገሩን ሲያስቡት የዚህ “ሰው” (የኢየሱስ) መልካምነት፣ ደግነት፣ ቸርነትና ባለጠግነት እንዲህ ባለ መልኩ የቀጠለ እንደሆነ “ነገ የእኛ ነገር …” ሲሉ ገቢያቸው ክፉኛ ሲያሽቆለቁልና ኪሳቸው ሲራቆት እየታያቸው “በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ “በማለትም ይገድሉት ዘንድ ተመካከሩበት::ፈሪሳውያን የሰው ልጅ መዳን፣ መፈወስ፣ ከእስራትና ከበሽታ ነጻ ወጥቶና ተላቆ በነፃነት ንጹሕ አየር ሲተነፍስ በአጠቃላይ የሰው ደስታ ከማየት ይልቅ የሰው ልጅ በስቃይ: የነፍስ እረፍት ከማጣት የተነሳም ሲናጥናበ ኃጢአት ባርነትም ሲማቅቅ፣ ሲጮህ እያዩ ሰንበት ግን በሰንበትነትዋ ተጠብቃና ተከብራከ ማየት በላይ የሚያስደስታቸው ነገር የለም:: ከሰው ልጅ ይልቅ ሳምንታዊው ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛው ቀን በልጦባቸው ለምን ጋኔን ያደረበት ነጻ ወጣ፣ ለምን ዕውር ያያል፣ ለምን የዲዳ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፣ ለምንስ ለምጻም ከለምጹ ነጻ? ሲሉ በውናቸው ቀርቶ በህልማቸው ያደርጉት ዘንድ የማይቻላቸው መልካም ሥራ ሲቃወሙና አቧራውን ሲያስጨሱት ከቅድሳት መጻህፍት የምናነበው።አንድ ጊዜ መቃወም ስለጀምሩ ብቻ ሁሉ ጊዜ መቃወም እንዳለባቸው አድርገው ራሳቸው ያሳመኑ ፈሪሳውያን ትልቁ ስህተታቸው ይህ ነበር። ነገሩ እማኮ ሲውል ሲያድር ሕመሙ አድጎባቸው የተጸናወታቸው በሽታ ለራሳቸው ተመልሶ ሲበላቸውና ሲያስቸግራቸው ነገር ሁሉ ተቀላቅሎባቸውም አንዱን ከሌላውን መለየት አቅቶአቸው ሁሉን በአልማሚት ሲቃወሙ የምናገኛቸው። በመጨረሻም ኢየሱስ በእጃቸው የያዙትን፣ ተሸክመውትም የሚዘሩትን መጽሐፍ ቃል ጠቅሶ እናውቃለን ሲሉ ስለሚናገሩት ነገር እንኳን ሳይቀር ይቅር ለሌላ ሊተርፉ ለራሳቸውም ቢሆን ምንም ዓይነት ግንዛቤ እንደሌላቸውና በባዶ ራሳቸውን የሞሉ በትዕቢት የተወጠሩ አላዋቂዎች ለመሆናቸው “አላነበባችሁምን?” ሲል ሲጠይቃቸው የሚገቡበት አጥተው ሲሽቆጠቆጡ የምንመለከታቸው። ዛሬም እርማቸው ያልቆረጡ: ዘገምተኞች: የሰው ደስታ ደም ለሚያስቀምጣቸው ደቂቀ ፈሪሳውያን እአምሮ ያላቸው እንደሆነ ከስህተታቸው ታርመው እንዲመለሱ እንቢ ለሚል ደንዳና ልብ ደግሞ ያለ እውቀት ምክርን ለሚያጨልሙ ጨለምተኞች ሁሉ ቃለ-ወልደ እግዚአብሔር የሚሰራ ህያው ቃል ነውና ለፍርድ ዛሬም ሕያው ነው

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 41. ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁ !!! “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል አለፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር ፈሪሳውያንም አይተው እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን? ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን? ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር። የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።
  “ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ” ይልና ነገር ያልበረደላቸው ፊሪሳውያንም ተከትለውት እንደገቡ ወይንም ደግሞ በሙክራቡ ውስጥም እንደጠበቁት አውስቶ ከቀደመ ስህተታቸውም ትምህርት ወስደውና ተምረው ራሳቸውን ለመልካም ነገር ከማዘጋጀት ይልቅ “እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት እርሱ ግን ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው? እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው ከዚያም በኋላ ሰውየውን እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች” ይህን ጊዜ “ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት” ይላል (የማቴዎስ ወንጌል 12፣1-14)። ፈሪሳውያን ማለት ከአይሁድ የሃይማኖት ወገኞች አንዱ ክፍል ሲሆኑ ሕግን ወግ ሲያጠብቁ ምሕረት፣ ሕይወትንና ደህንነትን ያመለጣቸው፤ ቢከፈት ከአጥንት በቀር ሌላ የማይገኝበት ካማረና ከተዋበ መቃብር ጋር አመሳስሎ የሚገልጻቸው እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ አነጋገር ግብዞች ሰዎች ነበሩ። በተጨማሪ ፈሪሳውያን ማለት -
  Ø ሥራቸው ሁሉ ግራ
  Ø መንገዳቸው ሁሉ ሸፍጥ የሞላበት
  Ø ለክፋት የማይተኙ ርህራሄ የሌላቸው አመጸኞች
  Ø ወግ አጥባዊዎች
  Ø የሚበጃቸው፣ የሚረባቸውና የሚሆናቸውን ለይተው የማያውቁ …
  Ø ደግ ደጉን ከማሰብና ከማየት ይልቅም ሴረኝነትና ጥመት የሚቀናቸው
  Ø ነፍስ ለመጣል የንጹሕ ሰው ደምም ለማፍሰስ ተማምለው የሚወጡ
  Ø ከሳሶች
  Ø መሰረት የሌለውና ያልበሰለ ነቀፋ ለመሰንዘር፣ መልካሙን ሁሉ ለማብጠልጠል ነፋስ “ሮጦ” የማይቀድማቸው
  Ø የተናቁት በእምነታቸው ሲድኑ ከትዕቢታቸው የተነሳ የተኮነኑ ትምክህተኞችም ነበሩ ፈሪሳውያን ማለት። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ናቸው ኢየሱስን በዕለተ ሰንበት ለምጻምን ታነጻ ዘንድ: የዕውሩንም ዓይን ታበራ ዘንድ እንዴት ብትደፍር ነው? የለም! የለም! ጎበዝ እንደው ይህማ “እንገት ቆርጠህ ጸጉርን እንደ ማስተካከል” ነው ሲሉ አምጸው ሕዝብን ሲቀሰቅሱበትና ሲያሳሙጽበት የምናገኛቸው:: በዚህም አልረኩም /አልተመለሱም ነገሩን ሲያስቡት የኢየሱስ መልካምነት፣ ደግነት፣ ቸርነትና ባለጠግነት እንዲህ ባለ መልኩ የቀጠለ እንደሆነ “ነገ የእኛ ነገር …” ሲሉ ገቢያቸው ክፉኛ ሲያሽቆለቁልና ኪሳቸው ሲራቆት እየታያቸው “በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ “በማለትም ይገድሉት ዘንድ ተመካከሩበት:: ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ዮሐ. 11፣47- 57 ያንብቡ:: ፈሪሳውያን የሰው ልጅ መዳን፣ መፈወስ፣ ከእስራትና ከበሽታ ነጻ ወጥቶና ተላቆ በነፃነት ንጹሕ አየር ሲተነፍስ በአጠቃላይ የሰው ደስታ ከማየት ይልቅ የሰው ልጅ በስቃይ: የነፍስ እረፍት ከማጣት የተነሳም ሲናጥናበ ኃጢአት ባርነትም ሲማቅቅ፣ ሲጮህ እያዩ ሰንበት ግን በሰንበትነትዋ ተጠብቃና ተከብራከ ማየት በላይ የሚያስደስታቸው ነገር የለም:: ከሰው ልጅ ይልቅ ሳምንታዊው ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛው ቀን በልጦባቸው ለምን ጋኔን ያደረበት ነጻ ወጣ፣ ለምን ዕውር ያያል፣ ለምን የዲዳ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፣ ለምንስ ለምጻም ከለምጹ ነጻ? ሲሉ በውናቸው ቀርቶ በህልማቸው ያደርጉት ዘንድ የማይቻላቸው መልካም ሥራ ሲቃወሙና አቧራውን ሲያስጨሱት ከቅድሳት መጻህፍት የምናነበው። ከዚህ የፈሪሳውያን አጉልና ጭንጋፍ እውቀት የተማርኩት ቁም ነገር ቢኖር ግን ሰው እግዚአብሔር ዓይኑን ካልከፈተና ልቡም ካላበራለት በስተቀር ሰው ሲባል እንደው የሚሰራውን የማያውቅ ምስኪን ፍጥረት መሆኑን ነው።...

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 42. በመጨረሻም ኢየሱስ በእጃቸው የያዙትን፣ ተሸክመውትም የሚዘሩትን መጽሐፍ ቃል ጠቅሶ እናውቃለን ሲሉ ስለሚናገሩት ነገር እንኳን ሳይቀር ይቅር ለሌላ ሊተርፉ ለራሳቸውም ቢሆን ምንም ዓይነት ግንዛቤ እንደሌላቸውና በባዶ ራሳቸውን የሞሉ በትዕቢት የተወጠሩ አላዋቂዎች ለመሆናቸው= ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለውን“አላነበባችሁምን?” ሲል ሲጠይቃቸው የሚገቡበት አጥተው ሲሽቆጠቆጡ የምንመለከታቸው። ሰንበትን ማክበር፣ ሰንበትን መጠበቅ፣ መንካበካብ፣ ማወደስ፣ መቀደስና ከዚህም አልፎ ስለ ሰንበት እሪ ማለትና ስለ ሰንበት አለሁ ማለት፣ መቆምና መከራከር ጥሩ ነው! ጥጉ ግን እፍ ብሎ እስትንፋስን የዘራበት የሰው ልጅ መዳን፣ መንጻት፣ ከመንፏቀቅ መረማመድ መቻል፣ ከእስራት መፈታት፣ ከዘወትር ሕጻንነት ወደ ማደግ መምጣት፣ መለወጥ፣ መጠቀም፣ አልፍ ማለትና ዕረፍትን ማግኘት ደግሞ ሰንበትን ከመጠበቅ፣ ከነገር ሁሉም የሚበልጥ ከሁሉም በላይ ምነው። ስለ ሰንበት ተብሎ ደቀ-መዛሙርት የሚራብበት፣ ዳዊት በረሃብ አለንጋ የሚገረፍበት፣ ልጅ እጁ ሰልቦ ለቤተሰቡና ለሀገሩ ሸክም የሚሆንበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም!! ለዚህም ነው ኢየሱስ ፈሪሳውያንን በእውነቱ ነገር እንዲህ ሽንጣችሁን ገትራችሁ በአደባባይ ስትከራከሩ ያዬ ሰው እኮ እውነት ይመስለው ይሆናል እውቀት ያላችሁም ትመስሉትም ይሆናል እውነቱ ግን ሲል – እናያለን ትላላችሁ እንጂ ዕውሮች ናችሁ! በማለት የሚገስጻቸው (የዮሐንስ ወንጌል 9)::

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 43. Please yemiyaden hulu tekikil new bilen mamen yelebinm? le bezu gize yene teyake yeneberew Memher Girma manachew?? yemil new! andi be chat sus yesekaye yeneberew orthodox Protestant join kaderege susun ketew tekikil new malet new? yemibeltewun menfes tekebele enji! degmo endaneresa ene beneberkubet be betakiristian hizbun eyatemeku buhala gn erasachew yemenfesu maderya honew yetegegnu alu. Endihum awurew be betamekdes eskemikemet seltan tesetotal selemil enddaygermen, gn menfesun enmermir.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 44. Enante asmesayoch, eskahun yet neberachu!!! Hulu gize atrafi sira bicha new yemitfeligut! Negadewoch!!! Enanten bilo melis sechi! Asafariwoch! tehadiso gele melie eyalachu bebado meda kemalazen be aynachu fit yeneberew yih chiger endifeta minew alrotachu???????????? Hul gize ye dil atbiya JEGNOCH NACHU!!! Ere bizu Tazebnachu!!! Nisha Gibu!!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 45. ሁለት ሰዓት ለማይሞላ ቅዳሴ ወገባቸው አስረው ቁጭ ብድግ የሚል ማህበረሰብ አጥማቂ ነኝ ባዩ ሲመጡ .. ከ4-11 ሰዓት ቆሞ ፊልም መሳይ ነገር ይከታተላል… እንኳን ታገዱ እኛም አረፍን

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
  ምላሾች
  1. ENANTE ENEMAN NACHIHU AGANINTOCH, DEBTERA, TENKUAY WYES BUDA EWINET NEW ENANTE AREFACHIHU AKATELKEN SITILU NEBER EKO

   ሰርዝ
 46. "እንኳን ታገዱ እኛም አረፍን???????" this is what our enemy setan desire!!!!!!!! this is not what is expected from who say i am orthodox.either our prevailing gift father is right or wrong let we our self pray ...every hidden will expose let God help us to see front,back&side by side our enemy diabolism examine our blessed fathers since Adam he will continue.What makes me wonder!!!!! if father girma's act is not from God i think diabolism is becoming good for us! but it is from God .do u remember our previous fathers life abune tekle haimanot passed such challenges even collide from other blessed fathers so let us try to not frustrating our self from sextant threat it will calm dawn !!!!!!!! it will dawn fall it will dis appear for ever but not buy giving suggestion just by pray

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 47. የእርግማን ዘሮች!!

  ብዙ ጥፋት ጠፍቷል ማስተዋልን አጥተን፣
  ሰው ለሰው ጠላቱ መሆኑን ዘንግተን፣
  ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው እየተባልን፣
  ዘመናት ባክነዋል ከዕውቀት/ከጥበብ ተጋርደን፡፡
  በሮሃና አክሱም የቀሩ አሻራዎች፣
  የቀደምት ጠቢባን የአእምሮ ጉልበቶች፣
  እምን እንደገቡ ምድሪቱን ጠይቄ፣
  መልስ ስጠባበቅ ሚስጢሩን ናፍቄ፣
  ይህች አዲስ ዕውቀት የእንቆቅልሽ መፍቻ፣
  ከብልሆች ሰፈር ከጥበብ ዳርቻ፣
  መጥታ ሹክ አለችኝ ፍፁም በለሆሳስ፣
  የእኩያንን ደባ ለዚች አገር መፍረስ፡፡
  ብሩሕ አእምሮዎች ምድሪቱ እንዳታበቅል፣
  ድንገት በቅሎም ቢገኝ እንደ አረም ሊነቀል፣
  ለካ ጥበበኛው ተበይኖበታል!!
  እና ምን ይገርማል ይህች አገር ብትደኸይ፣
  ይህች አገር ብትራብ ሰቆቃዋን ብታይ፣
  ትጉሀን ልጆቿ ለግዞት ተዳርገው፣
  ሟርትና ሟርተኞች ቦታውን ተክተው፣
  ቃላቸው ተከብሮ ደብተራና ጠንቋይ፣
  ጠለስን ጠላሾች የሚያበሉ ሥራይ፣
  ከአባታቸው ሰይጣን አንድነት መሥርተው፣
  መታች አስመታቾች ሲሰሩ እንቅልፍ አጥተው'
  መልካም ነገር ጠፍቶ ጠቢባን ተኝተው፣
  ሰው እየመከነ ዛርውላጅ ተወልዶ፣
  አምላክ ተዘንግቶ ለጣዖት ተሰግዶ፣
  ጨሌ ቦሮንቲቻ አዳል ሞቲ ጠቋር ፣
  አስገባሪ ሆነው ነግሰው በዚች አገር፣
  አእምሮአችን ቢነጥፍ ክብራችን ቢዋረድ፣
  ጥበብ ብትሸሸን ጥላን ብትሰደድ፣
  ብንፈዝ ብንባዝን ኑሮ ቢሰናከል፣
  ባናስተውል እንጂ እስኪ ምን ይገረማል?!
  አዎ እርግማን ነው እጅግ ክፉ እርግማን!፣
  እንዳይሆን ፈልገን ያዕቆብ አባታችን፣
  ከጣዖት አምላኪው ልጅ ከራሔል ተወልደን፣
  የአያታችን ላባ አብራክ ውጤት ሆነን፣
  የክፉ ሰው ዘሮች የእርግማን ፅንሸቶች፣
  የእናታቸው ገዳይ እኩይ የሙት ልጆች፣
  የቢኒዖኒ ደም/ዘር ነጣቂ ተኩላዎች፡፡
  አቤቱ አምላክ ሆይ ይሄን ዘር አቋርጠው!
  መንገዱን ዝጋበት አይኑን አሳውረው!
  ከሐናንያ ላከው ሌላ ዓይን ይቀበል!
  እርግማኑ ይብቃ አዲስ ትውልድ ይብቀል!!
  አሜን!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 48. ለመሆኑ አጥማቂው!አጥማቂው!አጥማቂው!!!!!! የምትሉት ማጥመቅ በቤተክርስቲያን ውግዝ ነው??? መምህር ግርማ እኮ በእግዚአብሔር ፀጋና በረከት እንጂ እናንተ እንደምትዘባርቁት የዕቃ ዕቃ ጨዋታ አይደለም…..ሰውዬው (ቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ) ባለ ሁለት ክፍል ግዙልኝ ብሏቸው አይደለም ውዝግብ ውስጥ የገቡት…… መምህር ግርማ ባይገርማችሁ ለብዙ ሰዎች ፈውስን አምጥተዋል፤በእግዚአብሔር ሃይል ፈውሰዋል፤ሀዘንና ሰቆቃ የደረሰባቸውን ቤተሰቦች ወደ ደስታ ህይወታቸው መልሰዋል…እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን……………እናንተ ሌቦች ግን ለጥቅም ብላችሁ ምዕመናን ከችግራቸው ጋር የኑሩ፣የሰይጣን ዲብሎስ መጫወቻ ይሁኑ ብላችሁ አገዳችኋቸው፡፡ ጥቅም ፈላጊዎች ናችሁ!!!!1…..ለስጋችሁ ያደራችሁ ስግብግቦች……የሃይማኖት አባቶች ሳትሆኑ ከሃዲዎች…….በቤተክርስቲን ውስጥ ያለው የዘመድ አዝማድ ስራ፣ሙስና፣ጉቦ ስር የሰደደ ነው…ለምሳሌ አንድ ካህን የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኖ ለመመደብ ብር 80,000.000 ጉቦ ይፍላል፡፡ አንድ ዲቆን ወደ አዲስ አበባ ከተማ መሃል ለመመደብ ብር 40,000.000 ይፍላል …..ወዘተ.ለማንኛውም ግራ የገባችሁስ እናንተ ናችሁና የእናንተን መድረክ አንሳተፍም……..ባለጌዎች!!!!!!!!መደዴዎች……..ፑፑፑ አላየንም !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 49. "ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትይዙ ሁሉ የሰይጣንንም ጥልቅ@ ነገር እነርሱ እንደሚሉት ለማታውቁ ለእናንተ በትያጥሮን ለቀራችሁት እላለሁ፤ ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም፥" የዮሐንስ ራእይ ፥ምዕራፍ 2 ቁር 24 god bless you abba  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 50. ለምን እግዝሐብሄር እነዚህን ሰዎች አያጠፋቸውም

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 51. Atmaki negn bayu lemehonu sint bet new yaferesew? Enat yelij lij lay , amat kemirat gar, guadegnamoch, gorebetamoch...medhanit aderegachihu eyetebale Christian mekakel telatnet yefetere new.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 52. E/r amlak yikir yibelachihu YESEW DIHINET YEMIASTEKIZACHIHU HULU enante ANDADIRIGEN mindin new yihe yesefer alubalta yemimesil were 80 million kezia belay hizib yemiketatelew site lay makireb yenantenim yeastesaseb derega yastezazibal M/r Girma sew nachew neger gin tsega yalachew sew andim ken ene adagn ene fewise esetalehu bilewim ayawikum aylumim kedimo neger yihe eko kefetari new yemisetew Kenante College yemiset bihon noro man lesachew yiset neber asafari zegeba new kemawtatachihu befit batsinihot eyut AHUNIM BIHON ESACHEW AYGODUM Yealem fetari ayalikibetim Libona yistachihu enante esachewin yasatachihu meslowachu new gin mayet mamen new Yegetan madan aytenal

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 53. እኔ የሚገርመኝ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ስራ ለይቶ አለማወቅ ወይም ለአንዱ ቀርቦ ወይም ተመሳስሎ መኖር አለበለዚያ አስፈጻሚ መሆን ነዉ እንጅ አባታችን
  የሚሰሩት ስራሁሉ በቤተክርስቲያን ቦታ ተሰጥቶት ትምህርት ያልተደረገበት
  መንፈሳዊ ትምህርታቸዉም ሆነ ጥምቀተ ስርአታቸዉ ለተቸገረ መፍትሄ ላልቸገረዉ ድራማ ላላወቀ ጥንካሬ ሲሆን በቤተክህነትም ቢሆን ሲኖዶሱ
  የያዘዉ መስቀል ፤ የተማረዉ ትምህርት ፤የሚያረገዉ ጸሎት እሳቸዉን ማስቆም
  አልችል ብሎ ነወይ በስልጣናቸዉ ስ ማገዳቸዉ ይህስ ሐይማኖታዊ ስርአት ነዉ
  እግዚአብሔር ከላካቸዉስ የሱንፈቃድ መጣስ አደለም ወይ


  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 54. በመጽሐፉም እንደተፃፈው፣ ፈውስ በገንዘብ አይሰጥም.........

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 55. FEWS KE EGZIABHER KALHONE BESTEKER KEMANIM AYGEGNIM ENA ENDE XEHAFT FERISAWYAN ENA SEDUKAWYAN ATHUNU EBAKACHUH BEKNAT KE EGZIABHER GAR ENDATTALU ADERACHUH ABATACHIN MELAKE MENKRAT MEMHIR GIRMA WONDIMUN BEXELOT MAGEZ YGEBACHUH NEBER (ETHIOPIA EJOCHWAN WEDE EGZIABHER TZEREGALECH) YETEBALECHBET YHE YEABATACHIN KESU ANDU ENDAYHON SLEZIH ENDATATFUT TETENKEKU ADERACHUH

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 56. ጥላችን ከማን ጋር እንደሆነ ያሳዩ አባት ናቸዉ ከሰው ሳይሆን ከመናፍስት ጋር !!

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 57. I do not know why some individuals become jealous of the miracle with Memehere Girma's deeds on behalf of God and saints.. What is wrong with him. He does everything with the name of God and saints. This is what the Apostles were doing. Of course, we may feel that things have been changed in a way that God's spirit does not work in this Satan''s world. However, who knows? our God does not have time and destiny of limit in its patience and blessing. To me, what is important is to question whether every deed of Memehere Girma has got something to do with biblical stories. We need to focus on the process, the things M. Girma doing during while healing people, not the product, i.e. what the healed person said or acted. Another important point is what if you accept the power given to saints for healing people, not the power Mr. Girma is given, and make your religious life strong. God bless Ethiopia.

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 58. እውነት ለምን ይሻራል? እኚ አባታችን እኮ እምነታችን በተግባር ያሳዩን፤ ከክፋት እንድንርቅ ያስተማሩን፤ብዙ ህዝብ ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሱ፤ ሥጋውን-ደሙን እንድንቀበል ያስተማሩን፤ የዲብሎስ ጥልቅ ሴራ በተግባር ያሳዩን የብዙ ቤተ-ሰብ የዘመናት አልጋ ቁራኝነት፤እስራት፤ ስቆቃ ወድ ብርሃን የለወጡ... በ እምነትም በምግባርም ምርጥ የዘመናችን የእምነት አርበኛ ናቸው ... ነገር ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው። ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ። ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው።.. እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች ..ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም (ማቴ 12:22-32)

  ምላሽ ይስጡሰርዝ
 59. poletica new haymanot eyetesera yalew ?ehziyabhare mels alew! endanbet atawkun!
  behaymanot hzb yewededew ybeltal.haymanote lhzb sibal yeminor enji lseltan aydelem

  ምላሽ ይስጡሰርዝ